Author Archives: abel wabella

Opportunism (ዝንደዳ?)

ጥንት

ከሰው ልጆች የስልጣኔ ታሪክ ጋር እኩል የሚጠቀስ ረጅም ታሪክ አለው፡፡ ከክርስቶስ ልደት አምስት መቶ አመታት በፊት አቴና የብዙ ሰዎች መመላለሻ በመሆኗ የከተማው ኑሮ የበረታ ወድድርን ፈጠረ፡፡ በዚህም ምክንያት ከተለመደው የተመጠነ ጤናማ አካልና መንፈስን የሚያጎለብት ትምህርት በላይ የሆነ ነገር ያስፈልግ ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩ (sophist)  ሶፊስት የተሰኙ ሊቃውንት  ሰባት የትምህርት ስልቶች (grammar, dialectics, Rhetoric, mathematics, geometry, astronomy and music) በደንብ አቀናብረው የከተማውን መላ ወጣቶች በተለይ የሀብታሞቹን ልጆች ደሞዝ እየተቀበሉ በመዘዋወር (አንድ ቦታ ሳይረጉ) ያሰተምሩ ነበር፡፡ ዋናው ዓላማቸውም እንዴት የወቅቱን ሁኔታ ተጠቅሞ መክበር እንደሚቻል ማሳየት ወይም አላግባብ ለመበልጸግ የሚረዳ ዕውቀት ማቀበል ነበር፡፡ ፖለቲከኛውን ለስልጣን፣ ነጋዴውን ወደሀብት በሌላም የኑሮ ዘርፍ ለተሰለፈው ለሥራው አስፈላጊውን ነገር ብቻ ይሰጡ ነበር፡፡

ይህ ነገርን ሁሉ ለግል ጥቀም ማበጃጀት ለዓለማችን ስልጣኔ እንደምሶሶ የሚቆጠሩት ቀደምት ፈላስፎች  (ሶቅራጠስ፣ ፕላቶና አሪስጣጣሊስ) በአጽንኦት የተቃወሙት ዐሳብ ነው፡፡ ትምህርት መታሰብ ያለበት ከጥቅም ባሻገር ነው፤ ከፍ ያሉ በሰውነት (ሰው በመሆን) በሚገኙ የስነምግባር ሕግጋትን በማስቀደም ነው፡፡ በተለይ ትልቁ የአውሮጳ መምህር ሶቅራጠስ ሰው እያንዳንዱን አጋጣሚ ለመመዝበር (to exploit) ወደወጭ ከማየቱ በፊት ‘ራስን ማወቅ’ን ፣ ወደውስጥ ማየትን ማስቀደም እንዳለበት አስተምሯል፡፡ ከእርሱ በወጉ የተማረው ፕላቶ ደግሞ ጉዳዩን አስፋፍቶ አስተምሯል፡፡ ይህ የትምህርት መሰረታዊ የአቅጣጫ ለውጥ በዘመናችን በምዕራባውያን መሪነት ዓለማችን ለደረሰችበት ቁሳዊም ሆነ ሌሎች ከፍታዎች እንደ መሰረትነት አገልግሏል፡፡የሶፊስቶችን ህጸጽ በቅጡ የተረዳው  ጀርመናዊ ባለቅኔ  “ዕውቀት ለአንዱ ለሁልጊዜ የሚያከብራት ወደላይ ወደአርያም የምትመራው ሰማያዊት ነብይት ናት፡፡ ለሌላው ግን በወተትና በቅቤ የምታገለግለው አንድ ወፍራም ላም ናት” ሲል የተናገረው ምነኛ! ድንቅ ነው፡፡ Read the rest of this entry

“የቃሊቲው መንግስት” እኔ እንዳነበብኩት

ባህር ማዶ ካለች አንዲት  ወዳጄ ጋር ስለአንዳንድ  ጉዳዮች (ስለሀገር ፣ ስለቤተክርስቲያን ፣ ስለወገን ወዘተ…) በምናወራበት የአዘቦት ወጋችን መሐል የፓስታ ሳጥን ቁጥሬን እንድነገራት ጠየቀችኝ፡፡ በሆዴ ‘ለዲያስፖራዎች የወገብ እና የጫማ ቁጥርን መስጠት ፋሽን ካለፈበት ሰንብቷል፤ ለምን ጠየቀችኝ? ያውም ጶስጣዬን ሆሆ!!’ እያልኩኝ አቀበልኳት፡፡ ከቀናት በኃላ ሳጥኔን ከፍቼ አዲስ የመጣ ነገር እንዳለ እንዳረጋግጥ ነገረችኝ፡፡ በፖስታዬ ምንም ነገር አለማግኘቴን ነግሬያት ጉዳዩን በዚሁ ልቋጨው ስንደረደር የኖረችበት የዲያስፖራ ዴሞክራሲያዊ ባህል ፣ መብትን የመጠየቅ ልማድ ግድ ብሏት በዚያው ካለው ከአገልግሎት ሰጪ ተቋም የመልዕክቱን ልዩ ቁጥር (tracking number) ጠይቃ  ሰጠችኝና በአንድ የፖስታ ቤቱ ሰራተኛ ርዳታ ዳጎስ ያለው መጽሐፍ በእጄ ገባ፡፡ እኔም በከፊል ለኪሴ ሳስቼ በከፊል ደግሞ ለሙስናው መስፋፋት የግሌን አስተዋጽኦ ላለማበርከት ብዬ  እርዳታ   የለገሱኝን ሰው  በእግዚአብሔር ይስጥልኝ ተሰናብቼ ከታላቅ የንባብ ዐራራ ጋር ወደጎጆዬ አመራሁ፡፡

ርዕስ – የቃሊቲው መንግስት

 ዝግጅት ፣ጥንቅር ፣ ጸሐፊ  – ሲሳይ አጌና

 የገጽ ብዛት – 443

 አሳታሚ – Netsanet publishing and distributing agency

 ዋጋውና  እና የት እንደታተመ አይገልጽም Read the rest of this entry

እንኳን ወደዞን ዘጠኝ በደህና መጡ!

ይህ ዞን ዘጠኝ ነው! በዞን ዘጠኝ ኢትዮጵያ ሐሳቦች በጽሁፍ ይንሸራሸራሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚበጁ ምክረ ሐሳቦች ይነሳሉ፤ ይጣላሉ፡፡ መንግስት ይወቀሳል፣ ይተቻል፣ ይከሰሳል፡፡ ለታላቂቷ ኢትዮጵያ የሚበጅ መልካም ሐሳብ ካልዎት – እባክዎ ከኛ ጋር በዞን ዘጠኝ ላይ ይጻፉ፡፡