Author Archives: ናትናኤል ፈ. አበራ

ነፃነት እና ዳቦ

በሚሰሩበት ቦታ፣ በሚኖሩበት ሰፈር ወይም አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብለው አጠገብዎ የተቀመጡ ወጣቶች ስለ እንድ ፖለቲካ ነክ ጉዳይ አንስተው ሲወያዩ ይሰማሉ እንበል፡፡ የሚወያዩበት ጉዳይ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት የሚያስከፋ እንደሚሆን ከገመቱ፤ ወጣቶቹን ‹የቀበጡ ለት› በሚል ዕይታ ገርመም ያደርጓቸዋል ወይም እራስዎትን ከቦታው ‹አልሰማሁም› በሚል እንድምታ ያሸሻሉ አልያም የሚራራ ልብ ካልዎት ለልጆቹ ይፈሩላቸዋል – እርስዎ እንደሰሟቸው የመንግስት ሰው (‹‹ጆሮ ጠቢ››) ቢሰማቸው ሊደርስባቸው የሚችለውን እያሰቡ፡፡ ፖለቲካ ነክ አይነት ውይይቶች ላይ የሚሳተፍ የቅርብ የሆነ ሰው ካልዎት ይመክራሉ፣ ይገስፃሉ፡፡ ምክርዎትን ለማጠናከር ምሳሌ አያጡም፡፡ በሀገሪቱ ጉዳይ ያገባናል ብለው የመንግስትን ውሳኔ ተቃውመው፣ የልዩነት ሃሳባቸውን በማሰማታቸው ብቻ ለእንግልት፣ ከኢኮኖሚ ዕድሎች የመገለል እና ግፋም ሲል ለእስራት የተዳረጉ ዜጎች ብዙ ናቸው፡፡ ‹ምን አጥተሽ ነው?› ሲሉ ይጠይቋታል በሀገሪቱ ፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ (informed active participant) የሆነች ወዳጅዎትን፡፡ ‹ስራ አለሽ፤ በልተሽ ካደርሽ እና ከእኛ ጋር ማሕበራዊ ግንኙነት እንዳታደርጊ ማንም ካልከለከለሽ፤ ምን ይሁን ብለሽ ነው ከማትችይው ጋር የምትጋፊው? ደሞ ብቻሽን ለውጥ ላታመጪ! ለኛ ጭንቀት ነው ትርፉ› በማለት አርፋ ብትቀመጥ የተሻለ መሆኑን ይነግሯታል፡፡

በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ (ወይም የሌላ አይነት ነፃነት) እጦት እራሱን ከሚያሳይባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን የሚያስከፍላቸው ዋጋ ከፍተኛ እንደሆነ ተገንዝበው፥ ግላዊ የሆነ ጭቆና እስካላጋጠማቸው ድረስ የተፈቀደላቸውን ብቻ እየተናገሩ/እየፃፉ/እያደረጉ ተቆጥበው መኖርን መምረጣቸው ነው፡፡

አከራካሪውን የቅደም ተከተል ጉዳይ ወደ ጎን ትተን ነፃነትንና ብልፅግና ሁለቱም እንደሚያስፈልጉን ግልፅ ነው፡፡ የነፃነት ጫፍ የተረጋገጥባት ነገር ግን ሰዎች ከዕለት ጉርሻ እጦት በየዕለቱ የሚረግፉባት ሀገር እንዲኖረን የማንመኘውን ያክል ዜጎች ችጋር የሚባል ነገር ሲነገር ብቻ የሚሰሙባት ነገር ግን መንግስት የሚናገሩትን፣ መስራት የሚችሉትን ወይንም ለአጠቃላይ እንቅስቃሴያቸው ልኬት አበጅቶ ጥሩ ከሚቀለብ የቤት እንስሳ የማይለዩበት ሀገር እንዲኖረን ፈዕሞ አንፈልግም፡፡

መጀመሪያ ራሴን ልቻል ወይስ መጀመሪያ ራሴን ልሁን? Read the rest of this entry