Monthly Archives: June 2012

የኢትዮጵያ ጦማሮች ምን ጻፉ?

አጥናፉ ብ

ሰሞኑን በኢንተርኔት ተጠቃሚ ዘንድ እያወዛገበ ያለው የቴሌኮም አዋጅ አቶ ሽመልስ ከማል በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው ስካይፒን መጠቀም ይቻላል ካሉ በሗላ ጋብ ብሎ ቢቆይም አቶ በረከት ሰጡት በተባለው መግለጫ ደግሞ ስካይፒን እንዘጋለን ወይም “ስካይፕም ሆነ ሌሎች የቴሌን ገቢ የሚቀንሱ እና ለደህንነት ስጋት የሚሆኑ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እንዘጋለን” የሚል ግራ የሚያጋባ ንግግር በትነዋል፡፡

ለዚህም ይመስላል አቤ ቶክቻው ‹‹ሰዎቻችን ቋንቋቸው የተደበላለቀው ምን ተንኮል ቢያሴሩነው›› የሚል ሽሙጥ ከጦማሩ ያኖረልን፡፡

የሁለቱን ባለስልጣናት ግራ የሚያጋባ መግለጫ  ግራ ያጋባው አቤ ቶክቻው ህጻን እያለን የተነገረንን አፈታሪክ ገላጭ ሆኖ አግኝቶታል ‹‹…ድሮ ድሮ አሉ የሰው ልጆች ቋንቋ ሁሉ አንድ ነበር። ታድያ ከእለታት በአንዱ ቀን ትልቅ ግንብ ገንብተው ፈጣሪያቸው ያለበት ሰባተኛው ሰማይ ላይ ደርሰው ምን እያደረገ እንደሆን ሊሰልሉት አሴሩ።

የሀሳባቸውን ለመሙላትም፤ አንድም የሰው ልጅ ሳይቀር ተሰባስበው በዚህ እኩይ ስራ ላይ ተጠመዱ። እግዜርም ይህ የማይሆን የቂል ሀሳባቸው እንደማይሳካ ያውቃልና፤ በሌሎች መልካም ስራዎች ላይጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ፣ እንዲሁም በዚህ የተነሳ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመታደግ ብሎ ይህንን ስራ ሊያቋርጥባቸው ፈለገ። ከዛም ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ከዛስ…?

ከዛማ አንዱ ብሎኬት አምጣ ሲል ውሃ ሲያቀብለው፣ ሙገር ሲሚንቶን አቀብለኝ ሲል የቀበና አሸዋ ሲያመጣ ግንቡ በየት በኩል ይግባቡ በየት በኩልስ ይገንቡ!? ሀሳባቸው ከንቱ ሆኖ ቀረ።…››

ከዚህ ቀደም ‹‹ቪኦኤን ጃም ታደርጋላችሁ?›› ተብለው የተጠየቁት አቶ ሽመልስ ከማል ‹‹የለም የኢትዮጵያ መንግስት ቪኦኤን ጃም አያደርግም›› ብለው ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ምን ታመጣላችሁ በሚል ድምጽ ‹‹አዎ! ጃም እናደርጋለን፡፡›› ብለው አምነዋል፡፡

ይህ የአቶ  ሸመልስ ክህደትና የልሎቹ ባለስልጣናት እምነት ያናደደው አቤ ‹‹..እኔ የምለው አቶ ሽመልስ፤ የመንግስት ቃል አቃባይ ሆነው ሳለ ለምን ቃላባይ ሲያደርጉዎት ዝም ይላሉ!?…›› ብሎ ለሌላኛው አዛዥ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ሙሉ ሽሙጡን ለማንበብ እዚህይጫኑ፡፡

በሌላ ጦማር አቤ ‹‹ኢጃበና ወሬ ኢጃበና ወሬ፤ በእውቀቱ ስዩም ወደእንግሊዝ ተሸኘ!›› ይለናል፡፡ ሲቀጥል ‹‹ኢጃበና›› ማለት ኢንዲህ ሲል ምን ማለት እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ‹‹ቃሉ ኦሮሚፋ ሲሆን የዓይን መክፈቻ! ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ቃሚዎች ዋናውን ጫት “ቂማህ” ከመጀመራቸው በፊት ትንሽ ነከስ ነከስ የሚያደርጓትን ዓይን መክፈቻ ወይም ኢጃበና! ይሏታል።›› ይህ ርእስ አቤ በውቀቱ ስዩምን ወደ ሎንዶን ኦሎምፒክ ለሚያደርገው ጉዞ የተደረገለትን ሽኝት ቃኝቶበታል፡፡

በዚህ ዝግችት ላይ ንግግር ያደረጉት የደራሲያን ማህበሩ ሊቀመንበር አቶጌታቸው እንዲህ ብለዋል “ለበእውቀቱ የለንደን ጉዞ መሳካት የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን እና መንግስትን ማመስገን እወዳለሁ…! በእውቀቱ በጉዞህ የሀገሪቱን መልካም ገፅታ እንድታስተዋውቅም አደራ እልሃለሁ!” ብለዋል፡፡ ይህ ንግግራቸው ነው አቤ  ሰውዬውን ‹‹ካድሬ መሳይ›› ያላቸው፡፡

ለአቶ ጌታቸው መልስም በእውቀቱ ሰጥቷል “በመጀመሪያ አቶ ጌታቸው ባሉት አልስማማም። መንግስትም ሆነ የመንግስት መስሪያቤቶችን ምንም አላደረጉልኝምና አላመሰግናቸውም። ትብብር ያደረገለኝ የደራሲያን ማህበር መመስገን ካለበት እርሱን አመሰግናለሁ።›› አቤ ለበእውቀቱ መልካም ጉዞም ተመኝቶለታል፡፡ ሙሉ ሽሙጡን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

‹‹ግርምት፣ትዝብት፣ፍርሃትእና ፀሎት!››

*ሽሙጥም መሰረት መብራቴ በተባበሩት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቋ

*ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካልሻባብ ደብዳቤ እንደደረሰው ….እና ሌሎችም ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

***

ኢትዮ ቼንጅ የተባለው ብሎግ ደግሞ አቶ በረከት ስካይፒን መከልከላቸውን ኢሳትን ጠቅሶ ይህን ጽሁፍ አስነብቧል፡፡ እዚህ ይጫኑ፡፡

***

ዳንኤል ክብረት በጦማሩ ‹‹የመጀመርያዋን ኢትዮጵያዊት ሴት ደራሲ›› ተዋወቋት ይለናል፡፡ በዚህ ጽሁፉ እሌኒ መሃመድ ስለምትባል ሴትና በአስተዳደር፣ በእምነትና በፖለቲካ ያደረገችውን አስተዋጽኦ የተለያዩ መፅሀፍቶችን ጠቅሶ እንዲህ ያትታል፡፡

‹‹…..እሌኒ በኢትዮጵያ ታሪክ በአስተዳደር፣ በእምነትና በፖለቲካ ኃያላን ከሆኑ ጥቂት መሪዎች የምትመደብ ናት፡፡ ምናልባትም ከንግሥተ ሳባና ከሕንደኬ ቀጥላ ልትጠቀስ የምትችል ኃያል ሴት ትመስለኛለች፡፡ ማዕከላዊው መንግሥት እንዲጠናከር፣ በሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል የነበረው ግንኙነትም የተሻለ እንዲሆን ጥረት አድረጋለች፡፡ ምንም እንኳን የአብራኳ ክፋይ ልጅ ባይኖራት በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድ እንደእናት ትታይ ነበር፡፡ …..››

       ‹‹…..ንግሥት እሌኒ ከፖለቲካውና አስተዳደሩ በተጨማሪ በሃይማኖት በኩል ብርቱ ምእመን ነበረች፡፡ አልቫሬዝ እንደሚለው እሌኒ ዓመቱን ሙሉ የምትጾም ሰው ነበረች፡፡ ምግብ የምትመገበውም በሳምንት ሦስት ቀን ማክሰኞ፣ ሐሙስና ቅዳሜ ብቻ ነበር፡፡…..››

ሙሉ ፅሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ጋዜጣ እና መጽሄቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – ሦስት

(ከሰኔ 11 እስከ ሰኔ 17፤ 2004)

የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት በልዩ ዝግጅት ለማክበር ደፋ ቀና እያለ ያለው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ በዓይነቱ የተለየ ‹‹የንድፈ ሐሳብና የፖሊሲ ትንተና መጽሄት›› ሊያሳትም እንደሆነ የሚነግር ዜና ይዞ ወጥቷል፡፡ ‹‹.. በዓይነቱ የተለየ የንድፈ ሐሳብና የአማራጭ ትንተና የሚቀርብበት መጽሄት ለማሳተም ዝግጅት መጨረሱን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቀ፡፡ ‹ዳንዲ› የሚል ስያሜ የተሰጣት መጽሄቷ ሙሉ ለሙሉ የንድፈ ሐሳቦችና አማራጭ የፖሊሲ መነሻ የሚሆኑ ሐሳቦች የሚተነተኑባት መሆኗ ተነግሯል፡፡

* * *

‹‹የመንግስት ገንዘብ ለሚያባክኑ መ/ቤቶች ከፍተኛ በጀት ተመደበ›› ያለው ደግሞ የኛ ፕሬስ ጋዜጣ ነው፡፡ ‹‹ከፍተኛ የመንግስት ገንዘብ ባለማወራረድ ዋና ኦዲተር ለመሰከረባቸው መስሪያ ቤቶች ከበፊቱ የበለጠ ከፍተኛ በጀት እንደተመደበላቸው ተጠቆመ፡፡›› ካለ በኋላ ባለፈው ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር ያባከኑትን መ/ቤቶች ሲዘረዝር ‹‹… መከላከያ ሚኒስቴር፣ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የመቀሌ ዩንቨርሲቲ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የመቀሌ ጤና ሳይንስ፣ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመንግስትን ገንዘብ ያለበቂ ማስረጃ ወጪ በማድረግና ሳያወራርዱ በመቅረት በዋና ኦዲተር ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንደገቡ አረጋግጧል፡፡›› በተመሳሳይ ዜና ፍኖተ ነፃነትም የመጪው ዓመትን በጀት ‹‹ለአፈና የሚውል በጀት›› ሲል ወርፎታል፡፡

* * *

‹‹የየመኑ ፕሬዘዳንት ሳላህ አዲስ አበባ መሽገዋል?›› የሚል መካከለኛ ሐተታ ይዞ የወጣው መሰናዘሪያ ‹‹…የብዙዎች ግምት ሳላህ ከእይታ የተሰወሩት ለደህንነታቸው በተፈጠረው ስጋት ሳይሆን ቀደም ሲል ስልጣን ላይ እያሉ ለሕዝባቸው እኔ በፊት በየቀኑ ጫት እቅም ነበር፡፡ አሁን የምቅመው በሳምንት አንድ ጊዜ ነው ስለዚህ እናንተም የእኔን አርአያ ተከተሉ በማለት ያስተላለፉትን መልዕክት መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ መሽገው ሱሳቸውን እያወራረዱ ነው ወይም ከሕዝብ በዘረፉት ገንዘብ አዲስ አበባ እየተመላለሱ ሱሳቸውና ፍላጎታቸውን እያጣጠሙ እንደሆነ የሚገልፅ ነው፡፡…››

* * *

ሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹ዳኞች የፍርድ ቤት ተገልጋዮን በቁጣ ማሸማቀቃቸው ጥያቄ አስነሳ›› የሚል ዜና በረቡዕ ዕትሙ የፊት ገጽ ላይ ይዞ ወጥቷል፡፡ በዝርዝሩም ‹‹…በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተለያዩ የክስ ሒደቶችን የሚያስችሉ ዳኞች በተገልጋዮ ላይ በሚያደርሱት ቁጣ፣ ተገልጋዮቹ በችሎቱ የተገኙበትን ጉዳይ ሳያስረዱ ተሸማቅቀው እንደሚመለሱ ተገለጸ፡፡..›› እያለ ይቀጥላል፡፡ ይህ የተገለጸው ከሕዝብ በቀረቡ ጥያቄዎች እንደሆነ በዜናው ላይ ተገልጧል፡፡

* * *

ሰንደቅ ጋዜጣ ‹‹ተማሪዎችን በውጤት ያንበሸበሸው የአ.አ.ዩ. ባልደረባ ቅጣቱን እየጠበቀ ነው›› ሲል ዘግቧል፡፡ ‹‹በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና የስነ-ትምህርት ፋኩሊቲዎች ውስጥ የተማሪዎች ሪከርድና ማኅደር ክፍል ሰራተኛ ሆኖ የ18 ተማሪዎችን ውጤት ከዲፓርትመንቱ መምህራኖች በመቀበል አሻሽሎ ወደሬጅስትራር አስተላልፏል ሲል የፌዴራሉ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚስን ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተበት አቶ ሰለሞን ኩምሳ….. የሰውም ሆነ የሠነድ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት.. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡››

* * *

ተመስገን ደሳለኝ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹ፍትህን እና አልሻባብን ምን አገናኛቸው?›› ባለው መጣጥፉ ላይ ካልታወቀ እራሱን የአልሻባብ ወኪል ብሎ ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ውል እንደነበረው ለማስመሰል በፍትህ ኢሜይል መልዕክት ስለላከ ሰው ጽፏል፡፡ ‹‹… እንደምታውቀው ለ30 ተከታታይ እትሞች 24,000 የአሜሪካን ዶላር ከፍለንሃል፡፡ አሁን ግን አልሻባብ ዕቅዶቹን ለመፈፀም የስልት ለውጥ አድርጓል፡፡ ስለዚህም 11,200 የአሜሪካን ዶላር የሚሆነውን የ14 እትሞች ክፍያ ለአልሻባብ እንዲመለስ እንፈልጋለን፡፡…›› የሚል እና ሌላም፣ ሌላም ይዘት ያለውን ደብዳቤ ተመስገን የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ማረጋገጫ ያላቸውን ነገሮች ከዘረዘረ በኋላ ‹‹… ስርዓቱ እዚህ ድረስ ወርዶ ለመወንጀል እየሞከረ ያለው ሀገራችንን ጥለን እንድንሄድ አልያም ራሳችንን በዝምታ እንድንሸብብ ከሆነ፤ የሚሰማ ካለ አቋማችንን በተደጋጋመ ማሳወቃችንን ብቻ አስታውሶ ከማለፍ ውጪ አማራጭ የለውም፡፡..›› ብሏል፡፡

* * *

‹‹ዶ/ር እሌኒ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ›› የሚል ዜና በፊት ገጹ ያስነበበው አዲስ አድማስ ‹‹… የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን፣ የሥራ ማስፋፊያ ዕቅዳቸው ተቀባይነት ማጣቱን ሮይተርስ የዘገበ ሲሆን ሥራ አስፈፃሚዋ ከነበራቸው ኃላፊነት ለቀዋል፡፡ ዶ/ር እሌኒ በምርት ገበያ መስራችነታቸው ዓለምአቀፍ እውቅናና ሽልማቶች እንዳገኙ የሚታወቅ ሲሆን ድርጅቱን ለመመስረትና ለመምራት አብረዋቸው እንዲሠሩ በዓለምአቀፍ መመዘኛ ቀጥረዋቸው የነበሩ ዘጠኝ ባለሙያዎችም ከሳቸው ጋር ለቀዋል፡፡ የደርጅቱን ሥራ ለማስፋፋት ከመንግስት ጋር ውይይት ሲያካሂዱ መቆየታቸውን የተናገሩት ዶ/ር እሌኒ፣ አንዳንድ ዋና ዋና እቅዶች እንደከሸፉ ለሮይተርስ ገልፀዋል፡፡…. በዶ/ር እሌኒ ምትክ የአቢሲኒያ ም/ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ አንተነህ አሰፋ የተሾሙ ሲሆን፣ ኩባንያው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ሲሰሩና ልምድ ሲቀስሙ የነበሩ የአገር ውስጥ ተቀጣሪ የማኔጅመንት ባለሙያዎች፣ አመራሩን ተክተው ይሰራሉ ተብሏል፡፡…››

* * *

ላይፍ መጽሄት ‹‹‹ጥቁር ሰው› ለሚኒልክ፣ ‹ስቴድ›ስ ለማን ተዘፈነ?›› በሚል ርዕስ በጻፈው ጽሁፍ ላይ የብርቱኳን ሚዼቅሳን ምስል አስቀምጦ ለርሷ እንደተዘፈነ ተከራክሯል፡፡ እንደማስረጃ ያስቀመጠው ‹‹…ቃል እንዲህ ሆነ እንዴ…›› የሚለውን ሐረግ ሲሆን ይህንንም ያለው ብርቱኳን ለሁለተኛ ጊዜ ከመታሰሯ በፊት ‹‹ቃሌ›› ብላ የጻፈችውን ደብዳቤ በማጣቀስ ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹…ቃል እንዲ ሆነ እንዴ…›› ካለ በኋላ በደበሰባሳው ‹‹…በሃገሬ…›› የሚል ዜማ ያሰማል በማለት ክርክሩን አጠናክሯል፡፡

* * *

የቴዎድሮስ ተ/አረጋይን ቃለ ምልልስ በአዲስጉዳይ የሚያነቡ ከBBC – Hardtalk ጋር ያመሳስሉታል፡፡ በዚህ ሳምንት አቦይ ስብሃትን አነጋግሯቸዋል፡፡ ‹‹አቦይ ስብሃት ከኢሕአዴግ ፊትና ኋላ›› የሚል ርዕስ ከተሰጠው ምልልሳቸው ውስጥ እየቀነጫጨብን እንመለከታለን፡-

‹‹… በ60ዎቹ አጋማሽ ላይ እዚህም እዚያም ትግል ነው፡… የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በተሻለ ብቃት ተንትኖ የተነሳ ኅወሓት ብቻ ነበር ብል ትክክል ነኝ፡፡››

‹‹… [ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ስለመልቀቃቸው] በሁሉም ሐሳቦች እንግባባለን ማለት አይደለም፡፡ ሆኖም አለመግባባቱ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንድለቅ የሚያደርገኝ አይደለም፡፡…››

‹‹… [የግል ፕሬስ ላይ ስለመጻፋቸውና ለቃለምልልስ ስለመገኘታቸው] ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስለ ሀገሩ የመናገር፣ ሐሳብ መስጠትና ለውጥ የማምጣት ዕድል እንደተሰጠው እኔም እሱን እያደረግሁ ነው፡፡ ሐሳቤን መግለጽ ደግሞ መብቴም ግዴታዬም ነው፡፡…››

‹‹…[ሐሳባቸውን መግለጽ ስለሚፈሩ ምሁራን] ሐሳብ የሌላቸው ወይም እልም ያሉ አድርባዮች ይሆናሉ – እነዚህ ምሁራን፡፡ በተረፈ ግን ስህተትም ቢሆን ዝም ከማለት ተናግሮ ሐሳብን ማስተካከል ይሻላል፡፡…››

‹‹…[ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ቃለ ምልልስ ስለአለመስጠታቸው] ይሄን ጥያቄ ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢመልሱት ይሻላል፡፡…››

‹‹… ኢህአፓዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው እንጂ ኢትዮጵያዊ ፕሮግራም አልነበራቸውም፡፡…››

‹‹…የሽግግር ዘመን መንግስት ሊመሰረት በነበረ ጊዜ ቀንና ሌሊቱ [መገንጠል እንፈልጋለን የሚሉትን] በልመና ነበር ያሳለፍነው፡፡…››

‹‹…ባለፉት መንግስታት በተሰራበት ግፍ አሁንም ሕዝቡ ያለው ምሬት ቀላል አይደለም፡፡ አሁንም ቢሆን በዴሞክራሲያዊ ስርዓቱና ልማቱ ካልተፋጠነ ችግር ውስጥ መግባታችን አይቀርም፡፡…››

‹‹…የአማራም ሕዝብ ቢሆን በስሙ ተነገደ እንጂ አልተጠቀመም፡፡…››

‹‹…[‹እስከ መገንጠል› ከሚለው አንቀጽ ሌላ ስለማስገባት] አንተስ ሌላ አማራጭ የነበረ ይመስልሃል? በርካታ ድርጅቶች ወዲያው ለመገንጠል ነበር የፈለጉት፡፡… ይህም ሁሉ ሆኖ እኮ ነው እነኦነግ ጥለው የወጡት፡፡››

‹‹…[በግንቦት 20 ወንድም ወንድሙን እንዴት እንደገደለው ስለማውራት] ብሔራዊ አንድነታችንን ስለሚያጠናክር በደንብ መነገር አለበት…››

‹‹…[ስላለፈው በደልና እልቂት ማውራት ስለማቆም] ገና መቀጠል አለበት፡፡ መቼም ማብቃት የለበትም፡፡…ግንቦት 20 ሲደርስ እንደነገሩ ይወራል እንጂ ገና በብቃት አልተነገረም፡፡››

‹‹…ልጆች ከህፃንነታቸው ጀምሮ የነበረው ግፍ መረዳት አለባቸው…››

‹‹…ሲስተሙ መስተካከል አለበት እንጂ ዛሬም ነገም ከመቶ ዓመት በኋላም መነገር አለበት ነው የምለው፡፡…››

‹‹…‹ጠላት› የሚለው ቃል፣ ‹የውጭ ጠላት›፣ ‹የሃገር ጠላት› ተብሎ መለየት አለበት የለበትም የሚለው አንፃራዊ ነው፡፡ ይህን የስነልሳን ሰዎች ሊያጠኑት ይችላሉ፡፡… ለሌላውም ሰው ቢሆን የነበረውን ስርዓት ማየትና የመጣውን ለውጥ ማሰብ እንጂ ቃል ላይ አተኩሮ መንገፍገፍ የለበትም ብዬ አምናለሁ፡፡…››

‹‹… [የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም አደጋ ላይ ስለመሆን አለመሆኑ] ነፍጠኛ ሳይሆን ሰራተኛ ትግሬ ወደሌላ ብሔር እየሄደ ነው፣ አማራም ነፍጠኛ ሳይሆን ሰራተኛ ሁኖ ወደሌላ እየሄደ ነው፡፡… አጀማመሩ አበረታች ነው፡፡… ችግሮች የሉም ማለት አይደለም፡፡ በአስተዳደር፣ በአመለካከት የአያያዝ ችግሮች አሉ፡፡…››

‹‹ሙስና አለ፡፡››

‹‹…ከቁጥጥር ውጭ የወጣ ሙስና የለም፡፡…››

‹‹የሀገሪቱ እድገት መኖሩ ጥያቄ ውስጥ አይገባም፡፡…››

‹‹…የከተማው ሕዝብ ኑሮው እየከበደው ሄዷል፡፡… ይህ ግንዘቤ ተወስዶበት፣ ምክንያቱ  ታውቆ የማስተካከል እርምጃ እየተደረገ ነው፡፡…››

‹‹…የዋጋ ግሽበቱ ደመወዝተኛውን ወደማይጎዳበት ሁኔታ እንደሚደርስ እርግጠኛ ነኝ፡፡››

‹‹…[በኢሕአዴግ ውስጥ ስለግለሰቦች መጉላት] የበላይነቱን ለማረጋገጥ ብሎም ከሥርዓቱ በላይ ለመሆን ያሰበም እንቅስቃሴ የጀመረም የለም፡፡… አንዳንዶቻችን ተገደን ከወረስነው የሰው አምልኮ አመለካከት በህሊናችን የማሰብ የበላይነት ጎልቶ ታይቶን ሊሆን ይችላል፡፡…››

‹‹…በእኔ አመለካከት አባይን የደፈረው መለስ ይቅርና ኢሕአዴግም አይደለም፡፡››

‹‹…ኢሕአዴግ በፈጠረው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም… የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው ደፈሩት የምለው፡፡››

ሌላም፣ ሌላም

 • በኢትዮጵያ የግብረ-ሰዶማውያን ቁጠር 16ሺ ደረሰ፤ አንድ ግብረሰዶማዊ 75 የወንድ (የወሲብ) ጓደኛ አለው፡፡ – የኛ ፕሬስ
 • 1.5 ሚሊዮን ካሬ መሬት ተዘረፈ – መሰናዘሪያ
 • ኢትዮጵያ ከወርቅ ሽያጭ ሪከርድ የሰበረ ትርፍ አገኘች – መሰናዘሪያ
 • ከስድስት ጊዜ በላይ የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች መንጃ ፍቃዳቸውን ሊነጠቁ ነው – ሪፖርተር (ረቡዕ)
 • ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጨምሮ የቀድሞ የኅወሓት ባለስልጣናትን ለምስክርነት ለማጓጓዝ 20,000 ብር ተዋጣ – ሰንደቅ
 • አንድነት የረሃብ አድማ ያደረጉ ታሳሪዎች ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠየቀ – ሰንደቅ
 • በቴዲ አፍሮ በከፈትኩት የፌስቡክ አካውንት የአበሻ ሴቶችን ታዘብኳቸው – ቃልኪዳን
 • እነ እስክንድር ነጋ ለውሳኔ በድጋሚ ተቀጠሩ – ፍትህ

‹‹…. የዕለቱ የቀኝ ዳኛ ሁሴን ይመር፣ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን መርምሮ አለማጠናቀቁን ገልፀው ለውሳኔ ለሰኔ 20 ቀን 2004 ተለዋጭ ጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡…››

 • የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እግር ሊቆረጥ ይችላል ተባለ – ፍትህ
 • ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምስክርነት አይቀርቡም – ፍትህ

‹‹…አቃቤ ሕግ… የተከሳሽን መከላከያ ምስክሮች ማድመጥ እንደማያስፈልግ ከገለፁ በኋላ በአቶ አስገደ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለሐምሌ 26 ቀን 2004 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡…››

ስፖርት

‹‹ሉሲዎቹ›› የአትሌቶቻችንን ገድል ለመድገም የቻሉ ጀግኖች ሆነዋል፤ ቀዳማይት እመቤት አዜብ መስፍን የበላይ ጠባቂ ሆነዋል – የኛ ፕሬስ

የመጽሄትና ጋዜጦቹ ርዕሰ አንቀጾች

 • የ2005 ረቂቅ በጀትና የኢሕአዴግ የብልጭልጭ ኢኮኖሚ – ፍኖተ ነፃነት
 • አዲስ አበባን የወጠረ የመንግስት ዝምታ – የኛ ፕሬስ
 • ለምግብ ዋስትና በጀት አለመያዙ ለዋጋ ንረቱ አለመታሰቡን አጉልቶ ያሳያል (ዜጋ ሁሉ የበይ ተመልካች እየሆነ መቀጠሉ አሳሳቢና አደናጋሪነቱ መቋረጥ ይገባዋል) – መሰናዘሪያ
 • መንግስት የግል ዘርፉን ይደግፍ! ያበረታታ! – ሪፖርተር (ረቡዕ)
 • የአዲስ አበባ 125ኛ በዓል ከማክበር ባሻገር – ሰንደቅ
 • ፍትህ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም የህዝብ ድምፅ ነችፍትህ
 • በሰንዓ የኢትዮጵያን መከራ – ላይፍ
 • በስብሰባ ብዛት የበለፀገች ሀገር – ቆንጆ
 • ‹‹ልማት እንደምስማር ከላይ ወደታች የሚመታ ሳይሆን እንደ እንጉዳይ ከመሬት የሚፈላ ነው›› – የድሬደዋ ገበሬ – አዲስ አድማስ
 • ኢሕአዴግ ራሱንም አገርንም ከማፈሪያነት ይጠብቅ! – ነጋድራስ
 • ነፃው ፕሬስ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው – ኢትዮ ቻናል
 • ዓሣውን ለማግኘት ወንዙን ማድረቅ!? – አዲስጉዳይ
 • ኢትዮጵያ በአይምሬው የሙስና ቫይረስ ተጠቅታለችሪፖርተር (እሁድ)

ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ ?

ዘላለም ክብረት

ህዝብ አብሮ ሲኖር ግጭት ሊያስወግደው የማይችለው ነገር ነው፡፡ የሰዎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እስካለ ድረስ ግጭት አለ፡፡ በግጭቱ ጉልበተኛው አሸንፎ ተሸናፊውን እንደፈለገ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ እንግሊዛዊው የስነ መንግስት ሊቅ Thomas Hobbes ‘State of Nature’ የሚለው ወይም ጉልበተኛ የሚገዛበት ደካማ የሚጠቃበት እና Hobbes “ life is solitary, poor, nasty, brutish, and short” ብሎ የገለፀው ሀሳባዊ አለም ነው፡፡

ይህ እንዳይሆን ህዝብ ስምምነት ላይ ደረሰ ይሄንም ስምምነት በልቦናው ፈረመ ‘መንግስት’ የሚባልም አካል መሰረተ፡፡ ይህ አካልም ከህዝቡ ጉልበት ተቀንሶ ጉልበተኛን ይቀጣ ዘንድ ተሰጠው እንዲሁም ይህ መብት እንዳለው ሁሉ የህዝቡን ሰላም የማስጠበቅም ግዴታ ተሰጠው፡፡ ማን ? መንግስት የተባለው አካል፡፡

ታዲያ መንግስት በጦር በጎራዴ ብቻ ሰላምን አያሰጠብቅም ይልቅስ ሰላማዊ መሳሪያውን ይመዛል ይሄም መሳሪያ የመንግስት ህግ ነው፡፡ ህዝቡም ያከብረው ዘንድ ይወዳል ወይም ይገደዳል፡፡ ስለዚህ የመንግስት ህግ ማለት መንግስት ህዝብ ከራሱ የተፈጥሮ ስልጣን ቀንሶ መንግስት ለተሰኝው አካል ስለሰጠው መንግስቱ ይሄን የህዝብ አደራ ለመጠበቅ የሚቀርብ በትር ነው፡፡

በመሰረቱ የኢትዮጵያም ታሪክ በዚህ የመንግስት ህልዮት ይገዛል፡፡ ነገሩ የሚበላሸው መንግስት የተባለው አካል የህዝብን አደራ በልቶ ሌላ ዳቦ መጋገር ሲጀምር ነው፡፡ የህዝቡን ዳቦ በልቶ የራሱን ሽልጦ ሲያነጉት ነው መከራው፡፡

መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የህዝብን ሰላም እና ጥቅም ለመስጠበቅ ህግ ያወጣሉ፣ ይከለክላሉ፣ ያስጠብቃሉ፡፡ ይሄም እውነት በጠነከረ ሁኔታ አሁን ባለንባት ኢትዮጵያ ገዝፎ ይታያል፡፡

ለምሳሌ Read the rest of this entry

ለምሳሌ ኢህአዴግ ስልጣን ይዞ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ከፀደቀበት ህዳር 1987 ዓ.ም ወዲህ፡

– ወደ 750 የሚደርሱ አዋጆች፣
– ከ200 በላይ ደንቦች፣
– በሽዎች የሚቆጠሩ መመሪያዎች ወጥተዋል፡፡

እነዚህ ህጎች በአጠቃላይ መብትን ማስጠበቂያና ግዴታን መስጫ ናቸው፡፡ እንደ ሁሉም የህግ ባህሪያት፡፡ አስገራሚ የሚሆነው ጉዳይ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ የሚወጡ ህጎች ብርታት እና ሀይል ነው፡፡

የፕረስ ህጉ አዋጅ ቁጥር 590/2000 ፣ የሙያ ማህበራት ህግ አዋጅ ቁጥር 620/2000፣ የፀረ-ሽብር ህግ አዋጅ ቁጥር 652/2001፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ቁጥር 662/2001፣ የሊዝ ህግ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ብለን የዋነኛዎቹን ብርቱ ህጎች መዘርዘር ይቻላል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪ ደግሞ በረቂቅ ደረጃ ያለ የሁሉንም ሰው በር ሊያንኳኳ የሚችል አዲስ የህግ ረቂቅ የቴሌኮም ህግ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

እንግዲህ ለጨዋታችን ይሄን ረቂቅ ህግ ከፀረ-ሽብር ህጉ ጋር አብረን እንመልከተው፡

– ማሞ እና ብሪቱ አዲስ ሙሽራዎች ሲሆኑ የፍቅራቸው ሙቀት አልበርድላቸው ብሎ የሚያደርጉትን አሳጥቷቸዋል:: ለዚህም ይመስላል ማሞ ህዝብ ይወቀው፣ ይመልከተው ብሎ ከብሪቱ ጋር ሲቃበጡ እና የጭናቸው ፍም በጋለበት ወቅት እያደረጉት ያሉትን ድርጊት ምስል የፌስቡክ ገፁ ላይ የለጠፈው፡፡ ግማሾቹ ጓደኞቹ ምነው ማ ሞ ! ሲሉት ግማሾቹ ደግሞ ኧረ ማሚሻ ቀወጥሽው ሎል ምናምን ብውለታል፡፡

በአዲሱ ረቂቅ የቴሌኮም አዋጅ አንቀፅ 6 መሰረት ማንኛውም ሰው ፀያፍ የሆነ ነገርን ማንኛውንም የቴሌኮም መሳሪያ ተጠቅሞ ለህዝብ ያሳወቀ ከሆነ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 640 የተደነገገው ቅጣት እንዳለ ሁኖ ከ 3 – 8 ዓመት ያስቀጣል፡፡ እንግዲህ ህጉ ከፀደቀ አቶ ማሞንም መልካም የእስር ወቅት ለማለት እንገደዳለን እንዲሁም ሞቶ በክር መታሰር ነው ክፉ ስምንት ዓመት እማ ስምንት ቀን ናት ብለን ለማፅናናት እንወዳለን፡፡

– አያንቱ የዩንቨርስቲ ትምህርቷን ጨርሳ በአንድ የመንግስት ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ ለሁለት ዓመታት ካገለገለች በኋላ በአንድ የምስራቅ አውሮፓ ሀገር ነጻ የትምህርት ዕድል ታገኛለች፡፡ ማንንቷን እና የቋንቋ ችሎታዎን ለማረጋገጥ በሚል ዩንቨርስቲው አያንቱን በ Skype ለሚደረግ የ30 ደቂቃ ቃለ መጠይቅ ይጋብዛታል፡፡ አያንቱም በተቀጠረችበት ሰዓት ሰፈር ውስጥ የሚገኝ አንድ ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ተገኝታ ቃለ ምልልሱንም በድል ትወጣለች፡፡ የማረጋጋጫ ደብዳቤም ይደርሳታል፡፡

በአዲሱ የቴሌኮም አዋጅ አንቀፅ 10 ንኡስ ቁጥር 4 መሰረት ማንም ሰው እያወቀም ሆነ በቸልተኝነት በኢንተርኔት የሚደረግን የስልክ ወይም የፋክስ ጥሪ ያደረገ ከሆነ ከ3 ወራት እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ቅጣት ይቀጣል፡፡

እንግዲህ ይህ ረቂቅ አዋጅ ከወጣ እህት አያንቱ ወደ ትምህርት ከመሄድ ይልቅ ወደ እስር ቤት መሄዷ እውን ይሆናል፡፡

እሱ እንዳለው ያ ሎሬቱ <>

– ዳርጌ ፌስቡክ ላይ ነው ውሎ አዳሩ፡፡ የሆነ ቀን ነሸጥ ሲያደርገው “አልሻባብ ድሬዳዋን ተቆጣጠረ ይሄም የጫትን ዋጋ ሊያንረው ይችላል” ብሎ ይለጥፋል:: በጉዳዩ የተደናገጡት ፌስቡካዊያን ጨኸታቸውን ያሰማሉ፡፡

በፀረ ሽብር ህጉ ማኝኛውንም የሽብር ድርጅት መደገፍ እንዲሁም ህዝብን ሊያሸብሩ የሚችሉ መረጃዎችን የለቀቀ አሁን ደግሞ በረቂቁ የቴሌኮም አዋጅ ማንኛውንም የቴሌኮሚኒኬሽን መሳሪያ ተጠቅሞ አሸባሪ መልዕክት ያስተላለፈ ሰው እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡

እንግዲህ ዳርጌም የዚሁ አንቀፅ ተሸላሚ ነው ማለት ነው፡፡ በርግጥ ዳርጌ “ፅሁፉን የፃፍኩት ጓደኞቼን አሰደንግጨ April the Fool ለማለት ነው” እንደሚል አይጠረጠርም፡፡

Thomas Hobbes ከመቃብር ቀና ብሎ ይሄን ቢመለከት የስነ መንግስት ትንታኔውን ያሻሽለው ይሆን ወይስ  Sometimes, the state of nature can be the case even if there is a Law, since an unjust law is not a law at all” ይላል? እኛም  መንግስት ከሕዝብ ኃይል ተቀናንሶ የተሰጠውን በትር አደራውን ሳይሆን ሌላ ነገር ሲጠብቅበት ባየን ጊዜ Is Rule by law a Rule of Law? ብለን እንጠይቃለን::

የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት

የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት የሚጀምረው ‹‹አዋጁ ፀድቋል፣ አልፀደቀም?›› የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ስንጀምር ነው፡፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ በግንቦት 18፤ 2004 እትሙ ‹‹አዋጁ ፀድቋል›› ብሎ ቢዘግብም ለገዢው ፓርቲ በሚወግኑ ጽሁፎቹ የሚታወቀው ጦማሪ ዳንኤል ብርሃነ ደግሞ ገና ‹‹የመጀመሪያውን የንባብ ደረጃ ማለፉ ነው›› ይላል፡፡ ፍኖተ ነፃነትም በበኩሉ በሰኔ 12፤ 2004 እትሙ ‹‹ፍርሀት የወለደው የቴሌ አፋኝ ረቂቅ ሕግ›› ባሰኘው ጽሁፉ ገና ረቂቁ በፓርላማ እንደቀረበ ነገር ግን ከፓርላማችን ያለፈ ልምድ መረዳት እንደሚቻለው ‹‹የቀናት ጉዳይ ነው እንጂ መጽደቁ እንደማይቀር›› ያትታል፡፡

በአገራችን ረቂቅ ሕጎች የሚመለከተው ሕዝብ’ጋ በግልፅ ሳይደርሱ በጭምጭምታ ይቆዩና ድንገት በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ሕግ የመሆናቸው የተለመደ ድራማ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ይለወጣል ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ይሄም ጽሁፍ በጭምጭምታው እውነታነት እና በረቂቅ ሕጉ ዙሪያ መጠነኛ ትንታኔ ይሰጣል፡፡

በቃሉ ኃይሉ (ስሙ ለዚህ ጽሁፍ ሲባል የተቀየረ) በስካይፕ የሚያወራው ከሚናፍቃቸውና ባሕር ማዶ ከሚኖሩ፣ እሱን ለማግኘት ኮምፒዩተር ላይ ቁጭ ብለው ከሚጠብቁት ጓደኞቹ’ጋ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ›› አለ ለዞን ዘጠኝ አስተያየቱን ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ፤ ምንም ዓይነት ሕግ ሲወጣ ብወደውም ብጠላውም እታዘዝለት ነበር፡፡ አሁን ግን በስካይፕ ማውራት ሕገ-ወጥ ከሆነ ከጓደኞቼ እና ከሕጉ መምረጥ ሊኖርብኝ ነው፡፡ ጓደኞቼን ከሕጉ የማስበልጥበት ምክንያት እስካሁን አይታየኝም፡፡›› በቃሉ ይህንን የተናገረው አዋጁ ስካይፕ መጠቀምን በወንጀልነት ፈርጆታል የሚለውን ወሬ ከሰማ በኋላ ነው፡፡

‹‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጁ›› ከስያሜውና ከትርጉም ክፍሉ ውጪ 18 አንቀጾች ብቻ አሉት፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ስልክ ማስደወልም ሆነ ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ያለ ኢትዮ ቴሌኮም እውቅና መስጠት የማይቻል መሆኑ ድሮም በሕግ የተደነገገ ቢሆንም አሁን የዚህ አዋጅ መውጣት አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማሕበራዊ ደረገጾች ላይ እያደገ የመጣውን ፀረ-አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊነት ለመገደብ እንደሆነ ብዙዎች መጠራጠር ጀምረዋል፡፡ የአዋጁ መግቢያ ላይም እንዲህ የሚል ይነበባል፡፡ ‹‹…የቴሌኮም ማጭበርበር ከኤኮኖሚ ኪሳራውም ባሻገር ዋና የደህንነት ስጋት በመሆኑ…›› ህግ አውጪው በረቂቅ አዋጂ ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ባለፈ ለሃገር ደህንነት ማሰቡን በግልጽ ይናገራል፡፤(በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አዋጁ የተጣቀሰው ከእንግሊዝኛው ቅጂ ሲሆን ትርጉሙ የዞን ዘጠኝ ነው፡፡)

ኢሕአዴግ ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚያደርገው ቅጥ ያጣ ጥበቃ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ትችቶቹን በሐሳብ ማሸነፍ እንዳቃተው ያሳብቃል፡፡ በጥቅሉ የመረጃ መረብን እና በዋናነት ማሕበራዊ ድረገጾችን ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱት የመረጃ ምንጮች እንደ ዶ/ር ዳኛቸው አባባል ‹‹የመረጃ ኦና.›› (Information Vacuum) ለመፍጠርና አውራ ፓርቲው ‹የሕዝብ› መገናኛ ብዙሐንን በመጠቀም የሚያጮኻቸው ወደአንድ አስተሳሰብ ያዘነበሉ መረጃዎች ለሚፈጥሯቸው የገደል ማሚቱ ድምጾች እንቅፋት ሆነዋል፡፡ Read the rest of this entry

የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት

የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት የሚጀምረው ‹‹አዋጁ ፀድቋል፣ አልፀደቀም?›› የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ስንጀምር ነው፡፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ በግንቦት 18፤ 2004 እትሙ ‹‹አዋጁ ፀድቋል›› ብሎ ቢዘግብም ለገዢው ፓርቲ በሚወግኑ ጽሁፎቹ የሚታወቀው ጦማሪ ዳንኤል ብርሃነ ደግሞ ገና ‹‹የመጀመሪያውን የንባብ ደረጃ ማለፉ ነው›› ይላል፡፡ ፍኖተ ነፃነትም በበኩሉ በሰኔ 12፤ 2004 እትሙ ‹‹ፍርሀት የወለደው የቴሌ አፋኝ ረቂቅ ሕግ›› ባሰኘው ጽሁፉ ገና ረቂቁ በፓርላማ እንደቀረበ ነገር ግን ከፓርላማችን ያለፈ ልምድ መረዳት እንደሚቻለው ‹‹የቀናት ጉዳይ ነው እንጂ መጽደቁ እንደማይቀር›› ያትታል፡፡

በአገራችን ረቂቅ ሕጎች የሚመለከተው ሕዝብ’ጋ በግልፅ ሳይደርሱ በጭምጭምታ ይቆዩና ድንገት በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ሕግ የመሆናቸው የተለመደ ድራማ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ይለወጣል ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ይሄም ጽሁፍ በጭምጭምታው እውነታነት እና በረቂቅ ሕጉ ዙሪያ መጠነኛ ትንታኔ ይሰጣል፡፡

በቃሉ ኃይሉ (ስሙ ለዚህ ጽሁፍ ሲባል የተቀየረ) በስካይፕ የሚያወራው ከሚናፍቃቸውና ባሕር ማዶ ከሚኖሩ፣ እሱን ለማግኘት ኮምፒዩተር ላይ ቁጭ ብለው ከሚጠብቁት ጓደኞቹ’ጋ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ›› አለ ለዞን ዘጠኝ አስተያየቱን ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ፤ ምንም ዓይነት ሕግ ሲወጣ ብወደውም ብጠላውም እታዘዝለት ነበር፡፡ አሁን ግን በስካይፕ ማውራት ሕገ-ወጥ ከሆነ ከጓደኞቼ እና ከሕጉ መምረጥ ሊኖርብኝ ነው፡፡ ጓደኞቼን ከሕጉ የማስበልጥበት ምክንያት እስካሁን አይታየኝም፡፡›› በቃሉ ይህንን የተናገረው አዋጁ ስካይፕ መጠቀምን በወንጀልነት ፈርጆታል የሚለውን ወሬ ከሰማ በኋላ ነው፡፡

‹‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጁ›› ከስያሜውና ከትርጉም ክፍሉ ውጪ 18 አንቀጾች ብቻ አሉት፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ስልክ ማስደወልም ሆነ ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ያለ ኢትዮ ቴሌኮም እውቅና መስጠት የማይቻል መሆኑ ድሮም በሕግ የተደነገገ ቢሆንም አሁን የዚህ አዋጅ መውጣት አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማሕበራዊ ደረገጾች ላይ እያደገ የመጣውን ፀረ-አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊነት ለመገደብ እንደሆነ ብዙዎች መጠራጠር ጀምረዋል፡፡ የአዋጁ መግቢያ ላይም እንዲህ የሚል ይነበባል፡፡ ‹‹…የቴሌኮም ማጭበርበር ከኤኮኖሚ ኪሳራውም ባሻገር ዋና የደህንነት ስጋት በመሆኑ…›› ህግ አውጪው በረቂቅ አዋጂ ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ባለፈ ለሃገር ደህንነት ማሰቡን በግልጽ ይናገራል፡፤(በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አዋጁ የተጣቀሰው ከእንግሊዝኛው ቅጂ ሲሆን ትርጉሙ የዞን ዘጠኝ ነው፡፡)

ኢሕአዴግ ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚያደርገው ቅጥ ያጣ ጥበቃ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ትችቶቹን በሐሳብ ማሸነፍ እንዳቃተው ያሳብቃል፡፡ በጥቅሉ የመረጃ መረብን እና በዋናነት ማሕበራዊ ድረገጾችን ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱት የመረጃ ምንጮች እንደ ዶ/ር ዳኛቸው አባባል ‹‹የመረጃ ኦና.›› (Information Vacuum) ለመፍጠርና አውራ ፓርቲው ‹የሕዝብ› መገናኛ ብዙሐንን በመጠቀም የሚያጮኻቸው ወደአንድ አስተሳሰብ ያዘነበሉ መረጃዎች ለሚፈጥሯቸው የገደል ማሚቱ ድምጾች እንቅፋት ሆነዋል፡፡

ከቻይና ምን መማር?
‘ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ’ የተባለ የጋዜጠኞች ድንበር የለሽ ቡድን ቻይናን ‹ከኢንተርኔት ጠላቶች› አንዷ እንደሆነች ያስቀምጣታል፡፡ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ልኡካን ቡድን ደግሞ በአዲስ አበባ ለሚገኘው አቻው – ኢሕአዴግ በብዙሐን መገናኛ እና ኢንተርኔት አስተዳደር  ዙሪያ ያካበተውን ልምድ አካፍሎ ተመለሰው በቅርብ ጊዜ እንደሆነ በገዢው ፓርቲ ድረገጽ ላይ የሰፈረው ዜና ያስረዳል፡፡

ቻይና ‹‹የምዕራቡ ዓለም የመረጃ ነፃነት ባሕል የአገሬን ባሕል ያጠፋል›› በሚል ስም ለበርካታ ብዙሐን መገናኛ በሯን ዘግታለች፡፡ ለቻይና ብቻ ተብሎ የተዘጋጀው ጉግል አንዳንድ የኮሙኒስት ፓርቲን የሚያስቀይሙ ቃላቶችን እንዳይፈልግ ተደርጎ በልኳ ተሰፍቶላታል፡፡ ፌስቡክና ትዊተርም ታግደዋል፡፡

የቻይና የፍቅር ልጅ የሆነችው ሃገራችን ከቻይና በቀሰመችው ልምድና ቴክኖሎጂ የቪኦኤና የዶቼቬሌን ሬዲዮ ጣቢያ ማፈኗን መንግስቷ አምኗል፡፡ በርካታ ድረገጾችም ታግደዋል፡፡ አንድ የዞን ዘጠኝ አባል በግሉ ባደረገው ቅኝት 65 ነፃ ድረአምባዎች፣ 14 የፓርቲ እና ለፓርቲ የሚወግኑ ድረአምባዎች፣ 37 ጦማሮች፣ 7 የበይነመረብ ሬዲዮና ቴሌቪዥኖች እና 37 የፌስቡክ ቡድን ገጾች በኢትዮጵያ እንዳይነበቡ መደረጋቸውን አረጋግጧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው አዲሱ አዋጅ በመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አርቃቂነት ለፓርላማ የቀረበው፡፡ ‹አዲሱ አዋጅ ምን ዓይነት በቀላሉ ትርጉማቸው ሊጠመዘዝ የሚችሉ አንቀጾች አሉት? የማሕበራዊ ድረገጽ እንቅስቃሴዎችን እንዴት ያውካቸዋል? ሐሳብን በነፃ ከመግለጽ መብት አንጻርስ አዋጁ እንዴት ይታያል? ስካይፕና ጉግል ቶክን የመሳሰሉት በVoice over Internet Protocol (VoIP) የሚጠቀሙ አገልግሎቶችን ሕገወጥ ያደርጋቸው ይሆን?› የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ እና ለማብራሪያ ክፍት የሆኑ አንቀጾችን ከዚህ በታች እንጠቃቅሳለን፡፡

አወዛጋቢዎቹ አንቀጾች
በአዋጁ ክፍል አንድ በተለዩ ቃላት ትርጉሞች ላይ የሚከተሉትን ያስቀምጣል፡፡ አንቀጽ 2 ላይ ‹‹የቴሌኮሙኒኬሽን ቁሳቁስ ማለት ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የዋለ ወይም ሊውል የታቀደ ዕቃ፤ መገጣጠሚያ (accessories) እና ሶፍትዌሮችን ጨምሮ ማለት ነው፡፡›› ይላል፡፡ አንቀጽ 1 ላይ ‹የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት› የሚለውን ሲተረጉም በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚቀርቡ ጽሁፎች እና ምስሎች ከአገልግሎቱ እንደሚካተቱ ጠቁሟል፡፡ ሶፍትዌሮችን በዚህ ትርጉም ውስጥ በማካተት የተከታይ አንቀጾችን ትርጉም በዚያ መልክ እንድናይ ያስገድደናል፡፡

ክፍል ሁለት፣ አንቀጽ 3 ‹‹ሚኒስትሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር የትኞቹ የቴሌኮሙኒኬሽን ቁሳቁሶች፣ አምራቾች፣ ገጣጣሚዎች፣ አስመጪዎች ፈቃድ እንደማይሹ ይገልጻል፤ ደንብ ያበጃል›› ይላል፡፡ ይህም በሚኒስትሩ (ሚኒስትሩ የሚባለው የኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡) ያልተዘረዘሩ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ ተጠቃሚውን በወንጀልነት እስከ 4 ዓመት ፅኑ እስራት እና እስከ 40,000 ብር በሚደርስ ቅጣት፣ አስመጪ እና አከፋፋይ ድርጅቶችን ደግሞ ‹‹..ከ10 እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ100,000ብር እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት..›› ሊያስከትልበት እንደሚችል ረቂቁ ይደነግጋል፡፡

የዚህ አንቀጽ ለትርጉም ክፍት መሆን የምንጠቀምባቸው የበይነመረብ ማሰሻዎች (Internet browsers)፣ ሶፍትዌሮች (skype, google talk…)፣ የስልክ ቀፎዎች (blackberry, iPhone, Android ስልኮች፣ ወዘተ…)፣ እና ሌሎችም ዓይነት በሚኒስትሩ ይወሰናሉ፣ ካልተወሰኑ ደግሞ ለመጠቀም ፈቃድ ያስፈልጋል የሚል አንድምታ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡(የጆሮ ማዳመጫ /head set/ የተጠቀመ ሰው ያልተፈቀደ መሳሪያ ገጣጥሞ ተጠቀመ ቢባል ሊስቀጣው ነው ማለት ነው እስከሚል የተለጠጠ ትርጉም ድረስ ሊወስደን ሁሉ ይችላል::)

አንቀጽ 6(1) ደግሞ ‹‹ማንም የቴሌኮም መረብን ወይም መሳሪያን በመጠቀም በፀረሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 መሰረት የሽብር መልዕክት ቢያሰራጭ ወይም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት የሚያስጠይቅ አጸያፊ መልዕክት ቢያሰራጭ… ከ3 እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከ30,000 እስከ 80,000 ብር ድረስ ይቀጣል›› ይላል፡፡በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰውን ወንጀል መፈጸም በዚህ ህግ ቢካታትም ባይካተትም ማስጠየቁ የማይቀር ሆኖ ሳለ በድጋሚ የተለየ ሽፋን መስጠቱ የህጉን አስፈላጊነት እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡

አንቀጽ 13 ‹‹የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመከላከል፣ ለመመርመርና ለመቆጣጠር ብሔራዊ የቴክኒክ ሥራ ቡድን ከሚመለከታቸው አካላት ተውጣጥቶ ይቋቋማል፡፡››

አንቀጽ 14 ‹‹ፖሊስ የቴሌኮም ማጭበርበር ተከስቷል ወይም ሊከሰት ይችላል ብሎ ባመነ ጊዜ ከፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል፡፡›› ይህም የአንድ ሰው የስልክ ንግግር፣ አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች፣ የኢሜይል መልዕክት ልውውጦች እንደአስፈላጊነታቸው የሚበረበሩበትን የሕግ አግባብ ይሰጣል ማለት ነው፡፡ መንግስት የኢንተርኔት አጠቃቀምን በተመለከተ ለአገሪቱ ደህንነት የሚያሰጉ ነገሮች ካሉ መቆጣጠር አለበት የሚለው ነጥብ ላይ መስማማት ቢቻልም የግለሰቦችን ነፃነት በተራ ፍራቻ ማሳጣት ግን ከሰብአዊ መብት ጥሰት ውስጥ ሊመደብ ይችላል፡፡

ህጉ በአጠቃላይ ካሉበት መሰረታዊ ገደቦች (limitations) መካከል ዋና ዋናዎቹ የግለሰቦችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሃገር ደህንነት ስም መንጠቁ፣ ለትርጉም ክፍት የሆኑ ሰፋፊ ሃሳቦችን ማጠቃለሉ እንዲሁም የህጉን አስፈላጊነት በሚገባ ሊያሳምን አለመቻሉ ናቸው፡፡

ከሌሎች የተለመዱ ሕጎች በተለየ የማስረጃ ሁኔታን የዳሰሰው ይህ አዋጅ ለወትሮ ከምንጠቀምባቸው የማስረጃ አይነቶች በተጨማሪ ተቀባይነት ያላቸውን ተጨማሪ የማስረጃ አይነቶች ይጨምራል፡፡ይህ ከመሰረታዊ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ጋር እና ከመሰረታዊ የወንጀል ህግ ጋር መታረቁ ያልተገጋገጠ የማስረጃ ስርአት በህጉ ትግበራ ወቅት ታርሞ ይተገበራል ማለት ዘበት ነው፡፡

ከኢንተርኔት ወደ ስልክ መደወልን፣ ያልተፈቀዱ ሶፍትዌሮችን መጠቀምን፣  እንዲሁም የጽሁፎችን ይዘትን በብዙ ከሚወቀሰው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ጋር ማቀላቀሉ ህጉን ከተጸፈበት በላይ አላማ  እንዳለው ሌላ ምስክር ነው፡፡ ወደ ስልክ መደወል እና ማስደወልን የሚከለክለው የህጉ አንቀፅ አስር  ከተከለከሉ ሶፍት ዌሮች ጋር ተደምሮ የኢንተርኔት የድምጽ ንግግርን ወደ ወንጀልነት ይቀይረዋል፡፡

VoIP (Skype, Google Talk…) በሚኒስትሩ ይፈቀዱ ይሆን?

የቀድሞዋ አዲስ ነገር መራኄ ኤዲተር መስፍን ነጋሽ በፌስቡክ ገጹ ላይ ‹Promote then criminalize!› በሚል ርዕስ ባሰፈረው አጭር የስዕል ማብራሪያ ላይ (ምስሉ እዚህ ጦማር መግቢያ ላይ ይታያል) ከሁለት ቀን በፊት በሚኒስትሩ ድረገጽ ላይ VoIPን (Voice over Internet Protocolን) የሚያስተዋውቅ ይዘት ያለው መልዕክት ተለጥፎ እንዳገኘ (ያ ገጽ አሁን በሌላ ይዘት ተተክቷል) በምስል አዘጋጅቶ እና የመጀመሪያው መስመር ላይ “ስለ VoIP ሰምታችሁ የማታውቁ ከሆነ የረዥም ርቀት የስልክ ጥሪዎችን የምታደርጉበትን መንገድ ለመቀየር ተዘጋጁ” የሚል ነገር እንዳነበበ ጠቅሶ ጽፎ ነበር፡፡ መስፍን ነጋሽ ይህንን ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ አንፃር በመታዘብ አገልግሎቱን እያስተዋወቁ፣ ተጠቃሚዎቹን ወንጀለኛ ከማድረግ የተቀነባበረ ሴራ ለይቶ እንደማያየው ተናግሯል፡፡

የሚኒስተሩ ድረገጽ በፍጥነት በሌላ ጽሁፍ መተካቱ አዋጁ እውነትም VoIP ኢላማ አድርጎ ተነስቷል ብሎ ለመጠርጠር እንደ አንድ ግብአት ሊቆጠር ይችላል፡፡ በሌላ በኩል እ.ኤ.አ. በ2002 የቴሌሴንተር አገልግሎት ፈቃድን በተመለከተ በወጣው መመሪያ አንቀጽ 13(2) ላይ VoIP (ከኮምፒዩተር ወደ ኮምፒዩተር የሚደረግ የድምጽ ግንኙነት ጨምሮ /ስካይፕን ያካትታል/) የተከለከለ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተለያዩ ኢንተርኔት ካፌዎች ስካይፕን በይፋ ሲጠቀሙ እንጂ በወንጀል ሲከሰሱ የታየበት አንድም መረጃ የለም፡፡ ሌላው ቀርቶ ኢቴቪ የሕዳሴው ግድብን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ በስካይፕ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል እያለ ሲያስተዋውቅ መክረሙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

በመሆኑም መመሪያው እያለ፣ የፀረ-ሽብርተኝነቱም ሆነ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እያሉ አዲሱ ‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ› እዚያ የተካተቱትን ሕግጋት ደግሞ መውጣቱ ያስፈለገበት ምክንያት ግልጽ አለመሆን የእነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች መስፋፋት ተከትሎ እያደገ የመጣውን ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ለማፈን የተወሰደ እርምጃ ነው የሚለውን መላምት ያጠናክረዋል፡፡ ለዚህም እንደዋቢ መጥቀስ የሚቻለው በረቂቁ ላይ ‹‹መንግስት በሕዝቡ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ…››፣ ‹‹… አፀያፊ ጽሁፎች›› የሚሉ አሻሚ እና ሰፊ ትርጉም የሚኖራቸውን ሐረጎች መጠቀሙ የአዋጁ ኢላማ በተለይ ማሕበራዊ ድረገጾች ላይ በሚደረጉ የግል ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ላይ ያነጣጠረ ነው በሚል ለስጋት የሚጥሉ ሆነዋል፡፡

ሚኒስትሩ VoIPን ከሚከለከሉ አገልግሎቶች መካከል እንደሚያስቀምጣቸው ለመጠርጠር የሚያበቃ ሌላም ምክንያት አለ – የገዢው ፓርቲ የቅርብ ሚዲያ እና “ህግ አውጪው”  በመባል የሚታማው ሬድዮ ፋና፡፡ የዜና መጽሄት በተሰኘው ፕሮግራሙ ሬዲዮ ፋና የረቂቅ አዋጁ መንፈስ ሁሉንም ዓይነት VoIPን የሚጠቀሙ አገልግሎቶችን ለማገድ የወጣ እንደሆነ ፍንጭ ይሰጣል:: በተለይ (በፕሮግራሙ ላይ) አንድ የምክር ቤት አባል የአዋጁን አስፈላጊነት ለማስረዳት ሲናገሩ ኢትዮ ቴሌኮም እንደስካይፕ ያሉ በኢንተርኔት ስልክ የማስደወያ ሶፍትዌሮችን በሕግም ሆነ በቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስር ማድረግ እንዳለበት አስረድተዋል:: አዲሱ የቴሌኮም አዋጅ ረቂቅ ደግሞ ለቴሌ ይህን ሕጋዊ ዳራ ይፈጥርለታል::

አዋጁ ከኢትዮ ቴሌኮምም በላይ በድብቅ የኢንተርኔት ማጥለል (Internet filtration) ሥራ በመስራት የሚታማውን የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (INSAን) ነፃ ያወጣዋል – የረቂቁ አንቀጽ 13 ‹የቴክኒክ የሥራ ቡድን›መቋቋም የሚለው ከለላ በማስቀመጥ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት እየተዘዋወርን ያነጋገርናቸው ጥቂት የኢንተርኔት ካፌ አገልግሎት ሰጪዎች ከወዲሁ (አዋጁ ከመጽደቁ እና በነጋሪት ጋዜጣ ከመውጣቱ በፊት) የስካይፕ እና ማንኛውንም የድምጽ (Voice over IP) አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

ዳንኤል ብርሃነ ከላይ ባጣቀስነው ጦማሩ ላይ ‹‹ስካይፕ በሕግ እንደማይታገድ የጥብቅና ባርኔጣዬን አስይዤ እወራረዳለሁ›› ሲል ከተከራከረው በተቃራኒ መደምደም እንደሚቻለው፣ አዋጁ አሁን አሁን እያቆጠቆጠ የመጣው በበይነመረብ ላይ ሐሳብን በነፃ የመግጽ ፍላጎት ላይ ክፉ ጥላ መጣሉ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች የአዋጁ ብቸኛ ዓላማም ይኸው ነው ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ከወዲሁ እየገለፁ ነው፡፡ ውጤቱን ለማየት ግን አዋጁ (በፓርላማ ክርክር እና የጋለ ውይይት?) ፀድቆ  የተግባር እርምጃው እስኪጀመር ጥቂት ወራት ብቻ መታገስ በቂ ይሆናል፡፡

የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት

የቴሌኮም ማጭበርበር ሕጉ አወዛጋቢነት የሚጀምረው ‹‹አዋጁ ፀድቋል፣ አልፀደቀም?›› የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ስንጀምር ነው፡፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ በግንቦት 18፤ 2004 እትሙ ‹‹አዋጁ ፀድቋል›› ብሎ ቢዘግብም ለገዢው ፓርቲ በሚወግኑ ጽሁፎቹ የሚታወቀው ጦማሪ ዳንኤል ብርሃነ ደግሞ ገና ‹‹የመጀመሪያውን የንባብ ደረጃ ማለፉ ነው›› ይላል፡፡ ፍኖተ ነፃነትም በበኩሉ በሰኔ 12፤ 2004 እትሙ ‹‹ፍርሀት የወለደው የቴሌ አፋኝ ረቂቅ ሕግ›› ባሰኘው ጽሁፉ ገና ረቂቁ በፓርላማ እንደቀረበ ነገር ግን ከፓርላማችን ያለፈ ልምድ መረዳት እንደሚቻለው ‹‹የቀናት ጉዳይ ነው እንጂ መጽደቁ እንደማይቀር›› ያትታል፡፡

በአገራችን ረቂቅ ሕጎች የሚመለከተው ሕዝብ’ጋ በግልፅ ሳይደርሱ በጭምጭምታ ይቆዩና ድንገት በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ሕግ የመሆናቸው ነገር የተለመደ ድራማ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ይለወጣል ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ይሄም ጽሁፍ በጭምጭምታው እውነታነት እና በረቂቅ ሕጉ ዙሪያ መጠነኛ ትንታኔ ይሰጣል፡፡

በቃሉ ኃይሉ (ስሙ ለዚህ ጽሁፍ ሲባል የተቀየረ) በስካይፕ የሚያወራው ከሚናፍቃቸውና ባሕር ማዶ ከሚኖሩ፣ እሱን ለማግኘት ኮምፒዩተር ላይ ቁጭ ብለው ከሚጠብቁት ጓደኞቹ’ጋ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ›› አለ ለዞን ዘጠኝ አስተያየቱን ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ፤ ምንም ዓይነት ሕግ ሲወጣ ብወደውም ብጠላውም እታዘዝለት ነበር፡፡ አሁን ግን በስካይፕ ማውራት ሕገ-ወጥ ከሆነ ከጓደኞቼ እና ከሕጉ መምረጥ ሊኖርብኝ ነው፡፡ ጓደኞቼን ከሕጉ የማስበልጥበት ምክንያት እስካሁን አይታየኝም፡፡›› በቃሉ ይህንን የተናገረው አዋጁ ስካይፕ መጠቀምን በወንጀልነት ፈርጆታል የሚለውን ወሬ ከሰማ በኋላ ነው፡፡

‹‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጁ›› ከስያሜውና ከትርጉም ክፍሉ ውጪ 18 አንቀጾች ብቻ አሉት፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ስልክ ማስደወልም ሆነ ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ያለ ኢትዮ ቴሌኮም እውቅና መስጠት የማይቻል መሆኑ ድሮም በሕግ የተደነገገ ቢሆንም አሁን የዚህ አዋጅ መውጣት አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማሕበራዊ ደረገጾች ላይ እያደገ የመጣውን ፀረ-አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊነት ለመገደብ እንደሆነ ብዙዎች መጠራጠር ጀምረዋል፡፡ የአዋጁ መግቢያ ላይም እንዲህ የሚል ይነበባል፡፡ ‹‹…የቴሌኮም ማጭበርበር ከኤኮኖሚ ኪሳራውም ባሻገር ዋና የደህንነት ስጋት በመሆኑ…›› ህግ አውጪው በረቂቅ አዋጂ ከኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ባለፈ ለሃገር ደህንነት ማሰቡን በግልጽ ይናገራል፡፤(በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አዋጁ የተጣቀሰው ከእንግሊዝኛው ቅጂ ሲሆን ትርጉሙ የዞን ዘጠኝ ነው፡፡

ኢሕአዴግ ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚያደርገው ቅጥ ያጣ ጥበቃ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ትችቶቹን በሐሳብ ማሸነፍ እንዳቃተው ያሳብቃል፡፡ በጥቅሉ የመረጃ መረብን እና በዋናነት ማሕበራዊ ድረገጾችን ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱት የመረጃ ምንጮች እንደ ዶ/ር ዳኛቸው አባባል ‹‹የመረጃ ኦና.›› (Information Vacuum) ለመፍጠርና አውራ ፓርቲው ‹የሕዝብ› መገናኛ ብዙሐንን በመጠቀም የሚያጮኻቸው ወደአንድ አስተሳሰብ ያዘነበሉ መረጃዎች ለሚፈጥሯቸው የገደል ማሚቱ ድምጾች እንቅፋት ሆነዋል፡፡

ከቻይና ምን መማር?
‘ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ’ የተባለ የጋዜጠኞች ድንበር የለሽ ቡድን ቻይናን ‹ከኢንተርኔት ጠላቶች› አንዷ እንደሆነች ያስቀምጣታል፡፡ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ልኡካን ቡድን ደግሞ በአዲስ አበባ ለሚገኘው አቻው – ኢሕአዴግ በብዙሐን መገናኛ እና ኢንተርኔት አስተዳደር ዙሪያ ያካበተውን ልምድ አካፍሎ ተመለሰው በቅርብ ጊዜ እንደሆነ በገዢው ፓርቲ ድረገጽ ላይ የሰፈረው ዜና ያስረዳል፡፡

ቻይና ‹‹የምዕራቡ ዓለም የመረጃ ነፃነት ባሕል የአገሬን ባሕል ያጠፋል›› በሚል ስም ለበርካታ ብዙሐን መገናኛ በሯን ዘግታለች፡፡ ለቻይና ብቻ ተብሎ የተዘጋጀው ጉግል አንዳንድ የኮሙኒስት ፓርቲን የሚያስቀይሙ ቃላቶችን እንዳይፈልግ ተደርጎ በልኳ ተሰፍቶላታል፡፡ ፌስቡክና ትዊተርም ታግደዋል፡፡

የቻይና የፍቅር ልጅ የሆነችው ሃገራችን ከቻይና በቀሰመችው ልምድና ቴክኖሎጂ የቪኦኤና የዶቼቬሌን ሬዲዮ ጣቢያ ማፈኗን መንግስቷ አምኗል፡፡ በርካታ ድረገጾችም ታግደዋል፡፡ አንድ የዞን ዘጠኝ አባል በግሉ ባደረገው ቅኝት 65 ነፃ ድረአምባዎች፣ 14 የፓርቲ እና ለፓርቲ የሚወግኑ ድረአምባዎች፣ 37 ጦማሮች፣ 7 የበይነመረብ ሬዲዮና ቴሌቪዥኖች እና 37 የፌስቡክ ቡድን ገጾች በኢትዮጵያ እንዳይነበቡ መደረጋቸውን አረጋግጧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው አዲሱ አዋጅ በመረጃ ደህንነት መረብ አርቃቂነት ለፓርላማ የቀረበው፡፡ ‹አዲሱ አዋጅ ምን ዓይነት በቀላሉ ትርጉማቸውን ሊጠመዘዝ የሚችሉ አንቀጾች አሉት? የማሕበራዊ ድረገጽ እንቅስቃሴዎችን እንዴት ያውካቸዋል? ሐሳብን በነፃ ከመግለጽ መብት አንጻርስ አዋጁ እንዴት ይታያል? ስካይፕና ጉግል ቶክን የመሳሰሉት በVoice over Internet Protocol የሚጠቀሙ አገልግሎቶችን ሕገወጥ ያደርጋቸው ይሆን?› የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ እና ለማብራሪያ ክፍት የሆኑ አንቀጾችን ከዚህ በታች እንጠቃቅሳለን፡፡

አወዛጋቢዎቹ አንቀጾች
በአዋጁ ክፍል አንድ በተለዩ ቃላት ትርጉሞች ላይ የሚከተሉትን ያስቀምጣል፡፡ አንቀጽ 2 ላይ ‹‹የቴሌኮሙኒኬሽን ቁሳቁስ ማለት ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የዋለ ወይም ሊውል የታቀደ ዕቃ፤ መገጣጠሚያ (accessories) እና ሶፍትዌሮችን ጨምሮ ማለት ነው፡፡›› ይላል፡፡ አንቀጽ 1 ላይ ‹የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት› የሚለውን ሲተረጉም በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚቀርቡ ጽሁፎች እና ምስሎች ከአገልግሎቱ እንደሚካተቱ ጠቁሟል፡፡ ሶፍትዌሮችን በዚህ ትርጉም ውስጥ በማካተት የተከታይ አንቀጾችን ትርጉም በዚያ መልኪ እንድናይ ያስገድደናል፡፡

ክፍል ሁለት፣ አንቀጽ 3 ‹‹ሚኒስትሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር የትኞቹ የቴሌኮሙኒኬሽን ቁሳቁሶች፣ አምራቾች፣ ገጣጣሚዎች፣ አስመጪዎች ፈቃድ እንደማይሹ ይገልጻል፤ ደንብ ያበጃል›› ይላል፡፡ ይህም በሚኒስትሩ (ሚኒስትሩ የሚባለው የኢንፎርሜሽን እና ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡) ያልተዘረዘሩ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ ተጠቃሚውን በወንጀልነት እስከ 4 ዓመት ፅኑ እስራት እና እስከ 40,000 ብር በሚደርስ ቅጣት፣ አስመጪ እና አከፋፋይ ድርጅቶችን ደግሞ ‹‹..ከ10 እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ100,000ብር እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት..›› ሊያስከትልበት እንደሚችል ረቂቁ ይደነግጋል፡፡

የዚህ አንቀጽ ለትርጉም ክፍት መሆን የምንጠቀምባቸው የበይነመረብ ማሰሻዎች (Internet browsers)፣ ሶፍትዌሮች (skype, google talk…)፣ የስልክ ቀፎዎች (blackberry, iPhone, Android ስልኮች፣ ወዘተ…)፣ እና ሌሎችም ዓይነት በሚኒስትሩ ይወሰናሉ፣ ካልተወሰኑ ደግሞ ለመጠቀም ፈቃድ ያስፈልጋል የሚል አንድምታ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡(የጆሮ ማዳመጫ የተጠቀመ ሰው ያልተፈቀደ መሳሪያ ገጣጥሞ ተጠቀመ ቢባል ሊስቀጣው ነው ማለት ነው እስከሚል የተለጠጠ ትርጉም ድረስ ሊወስደን ሁሉ ይችላል)

አንቀጽ 6(1) ደግሞ ‹‹ማንም የቴሌኮም መረብን ወይም መሳሪያን በመጠቀም በፀረሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 መሰረት የሽብር መልዕክት ቢያሰራጭ ወይም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት የሚያስጠይቅ አጸያፊ መልዕክት ቢያሰራጭ… ከ3 እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከ30,000 እስከ 80,000 ብር ድረስ ይቀጣል›› ይላል፡፡በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰውን ወንጀል መፈጸም በዚህ ህግ ቢካታትም ባይካተትም ማስጠየቁ የማይቀር ሆኖ ሳለ በድጋሚ የተለየ ሽፋን መስጠቱ የህጉን አስፈላጊነት እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡

አንቀጽ 13 ‹‹የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመከላከል፣ ለመመርመርና ለመቆጣጠር ብሔራዊ የቴክኒክ ሥራ ቡድን ከሚመለከታቸው አካላት ተውጣጥቶ ይቋቋማል፡፡››

አንቀጽ 14 ‹‹ፖሊስ የቴሌኮም ማጭበርበር ተከስቷል ወይም ሊከሰት ይችላል ብሎ ባመነ ጊዜ ከፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል፡፡›› ይህም የአንድ ሰው የስልክ ንግግር፣ አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች፣ የኢሜይል መልዕክት ልውውጦች እንደአስፈላጊነታቸው የሚበረበሩበትን የሕግ አግባብ ይሰጣል ማለት ነው፡፡ መንግስት የኢንተርኔት አጠቃቀምን በተመለከተ ለአገሪቱ ደህንነት የሚያሰጉ ነገሮች ካሉ መቆጣጠር አለበት የሚለው ነጥብ ላይ መስማማት ቢቻልም የግለሰቦችን ነፃነት በተራ ፍራቻ ማሳጣት ግን ከሰብአዊ መብት ጥሰት ውስጥ ሊመደብ ይችላል፡፡

ህጉ በአጠቃላይ ካሉበት መሰረታዊ ገደቦች(limitations) መካከል ዋና ዋናዎቹ የግለሰቦችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሃገር ደህንነት ስም መንጠቁ፣ለትርጉም ክፍት የሆኑ ሰፋፊ ሃሳቦችን ማጠቃለሉ እንዲሁም የህጉን አስፈላጊነት በሚገባ ሊያሳምን አለመቻሉ ናቸው፡፡

ከሌሎች የተለመዱ ሕጎች በተለየ የማስረጃ ሁኔታን የዳሰሰው ይህ አዋጅ ለወትሮ ከምንጠቀምባቸው የማስረጃ አይነቶች በተጨማሪ ተቀባይነት ያላቸው ያላቸውን ተጨማሪ የማስረጃ አይነቶች ይጨምራል፡፡ይህ ከመሰረታዊ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ጋር እና ከመሰረታዊ የወንጀል ህግ ጋር መታረቁ ያልተገጋገጠ የማስረጃ ስርአት በህጉ ትግበራ ወቅት ታርሞ ይተገበራል ማለት ዘበት ነው፡፡

ወደ ኢንተርኔት ወደ ስልክ መደወልን፣ያልተፈቀዱ ሶፍትዌሮችን መጠቀምን፣ እንዲሁም የጽሁፎችን ይዘትን በብዙ ከሚወቀሰው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ጋር ማቀላቀሉ ህጉን ከተጸፈበት በላይ አላም እንዳለው ሌላ ምስክር ነው፡፡
ወደ ስልክ መደወል እና ማስደወልን የሚከለክለው የህጉ አንቀፅ አስር ከተከለከሉ ሶፍት ዌሮች ጋር ተደምሮ የኢንተርኔት የድምጽ ንግግርን ወደ ወንጀልነት ይቀይረዋል፡፡

VoIP (Skype, Google Talk…) በሚኒስትሩ ይፈቀዱ ይሆን?

የቀድሞዋ አዲስ ነገር መራኄ ኤዲተር መስፍን ነጋሽ በፌስቡክ ገጹ ላይ ‹Promote then criminalize!› በሚል ርዕስ ባሰፈረው አጭር የስዕል ማብራሪያ ላይ (ምስሉን እዚህ ጦማር ላይ መመልከት ይቻላል) ከሁለት ቀን በፊት በሚኒስትሩ ድረገጽ ላይ VoIPን (Voice over Internet Protocolን) የሚያስተዋውቅ ይዘት ያለው መልዕክት ተለጥፎ እንዳገኘ (ያ ገጽ አሁን በሌላ ይዘት ተተክቷል) በምስል አዘጋጅቶ እና የመጀመሪያው መስመር ላይ “ስለ VoIP ሰምታችሁ የማታውቁ ከሆነ የረዥም ርቀት የስልክ ጥሪዎችን የምታደርጉበትን መንገድ ለመቀየር ተዘጋጁ” የሚል ነገር እንዳነበበ ጠቅሶ ጽፎ ነበር፡፡ መስፍን ነጋሽ ይህንን ሁኔታ ከረቂቅ አዋጁ አንፃር በመታዘብ አገልግሎቱን እያስተዋወቁ፣ ተጠቃሚዎቹን ወንጀለኛ ከማድረግ የተቀነባበረ ሴራ ለይቶ እንደማያየው ተናግሯል፡፡

የሚኒስተሩ ድረገጽ በፍጥነት በሌላ ጽሁፍ መተካቱ አዋጁ እውነትም VoIP ኢላማ አድርጎ ተነስቷል ብሎ ለመጠርጠር እንደ አንድ ግብአት ሊቆጠር ይችላል፡፡ በሌላ በኩል እ.ኤ.አ. በ2002 የቴሌሴንተር አገልግሎት ፈቃድን በተመለከተ በወጣው መመሪያ አንቀጽ 13(2) ላይ VoIP (ከኮምፒዩተር ወደ ኮምፒዩተር የሚደረግ የድምጽ ግንኙነት ጨምሮ /ስካይፕን ያካትታል/) የተከለከለ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተለያዩ ኢንተርኔት ካፌዎች ስካይፕን በይፋ ሲጠቀሙ እንጂ በወንጀል ሲከሰሱ የታየበት አንድም መረጃ የለም፡፡ ሌላው ቀርቶ ኢቴቪ የሕዳሴው ግድብን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ በስካይፕ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል እያለ ሲያስተዋውቅ መክረሙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

በመሆኑም መመሪያው እያለ፣ የፀረ-ሽብርተኝነቱም ሆነ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ እያሉ አዲሱ ‹የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ› እዚያ የተካተቱትን ሕግጋት ደግሞ መውጣቱ ያስፈለገበት ምክንያት ግልጽ አለመሆን የእነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች መስፋፋት ተከትሎ እያደገ የመጣውን ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ለማፈን የተወሰደ እርምጃ ነው የሚለውን መላምት ያጠናክረዋል፡፡ ለዚህም እንደዋቢ መጥቀስ የሚቻለው በረቂቁ ላይ ‹‹መንግስት በሕዝቡ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርግ…››፣ ‹‹… አፀያፊ ጽሁፎች›› የሚሉ አሻሚ እና ሰፊ ትርጉም የሚኖራቸውን ሐረጎች መጠቀሙ የአዋጁ ኢላማ በተለይ ማሕበራዊ ድረገጾች ላይ በሚደረጉ የግል ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ላይ ስጋት የሚጥሉ ሆነዋል፡፡

ሚኒስትሩ VoIPን ከሚከለከሉ አገልግሎቶች መካከል እንደሚያስቀምጣቸው ለመጠርጠር የሚያበቃ ሌላም ምክንያት አለ – የገዢው ፓርቲ የቅርብ ሚዲያ እና ህግ አውጪው ሬድዮ ፋና፡፡ የዜና መጽሄት በተሰኘው ፕሮግራሙ ሬዲዮ ፋና የረቂቅ አዋጁ መንፈስ ሁሉንም ዓይነት VoIPን የሚጠቀሙ አገልግሎቶችን ለማገድ የወጣ እንደሆነ ፍንጭ ይሰጣል:: በተለይ (በፕሮግራሙ ላይ) አንድ የምክር ቤት አባል የአዋጁን አስፈላጊነት ለማስረዳት ሲናገሩ ኢትዮ ቴሌኮም እንደስካይፕ ያሉ በኢንተርኔት ስልክ የማስደወያ ሶፍትዌሮችን በሕግም ሆነ በቴክኖሎጂ ቁጥጥር ስር ማድረግ እንዳለበት አስረድተዋል:: አዲሱ የቴሌኮም አዋጅ ረቂቅ ደግሞ ለቴሌ ይህን ሕጋዊ ዳራ ይፈጥርለታል::

አዋጁ ከኢትዮ ቴሌኮምም በላይ በድብቅ የኢንተርኔት ማጥለል (Internet filtration) ሥራ በመስራት የሚታማውን የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (INSAን) ነፃ ያወጣዋል – የረቂቁ አንቀጽ 13 ‹የቴክኒክ የሥራ ቡድን›መቋቋም የሚለው ከለላ በማስቀመጥ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት እየተዘዋወርን ያነጋገርናቸው ጥቂት የኢንተርኔት ካፌ አገልግሎት ሰጪዎች ከወዲሁ (አዋጁ ከመጽደቁ እና በነጋሪት ጋዜጣ ከመውጣቱ በፊት) የስካይፕ እና ማንኛውንም የድምጽ (Voice over IP) አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

ዳንኤል ብርሃነ ከላይ ባጣቀስነው ጦማሩ ላይ ‹‹ስካይፕ በሕግ እንደማይታገድ የጥብቅና ባርኔጣዬን አስይዤ እወራረዳለሁ›› ሲል ከተከራከረው በተቃራኒ መደምደም እንደሚቻለው፣ አዋጁ አሁን አሁን እያቆጠቆጠ የመጣው በበይነመረብ ላይ ሐሳብን በነፃ የመግጽ ፍላጎት ላይ ክፉ ጥላ መጣሉ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች የአዋጁ ብቸኛ ዓላማም ይኸው ነው ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ከወዲሁ እየገለፁ ነው፡፡ ውጤቱን ለማየት ግን አዋጁ ፀድቆ(በፓርላማ ክርክር እና የጋለ ውይይት ጋር) የተግባር እርምጃው እስኪጀመር ጥቂት ወራት ብቻ መታገስ በቂ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ጦማሮች ምን ፃፉ?

(ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 13)

‹‹እነአልበርት አንስታይን ስለዘንድሮው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ይላሉ?››በማለት በ‹የበፍቄ ዓለም› ላይ ይህን ፅሁፍ ጀባ ያለን በፍቃዱ ዘሀይሉ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፉ ላይ የዓለም ሶስት ታላላቅ ሰዎችን እይታ ከአገራችን ነባራዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር አነጻጽሮልናል፡፡

በአልበርት አንስታይን ታዋቂ አባባል “The world will not be destroyed by those who do evil, but by those who watch them without doing anything.” (ዓለማችን የምትጠፋው ክፉ በሚያደርጉ ሰዎች ሳይሆን ክፉ ሲያደርጉ እያዩ ዝም በሚሏቸው ሰዎች ነው፡፡) የጀመረው ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር አይተው እነዳላዮ አላፊዎችን እነዲህ ሸንቆጥ አድርጓቸዋል፡፡ Read the rest of this entry

የኢትዮጵያ ጦማሮች ምን ፃፉ?

(ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 13)

‹‹እነአልበርት አንስታይን ስለዘንድሮው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ይላሉ?››በማለት በ‹የበፍቄ ዓለም› ላይ ይህን ፅሁፍ ጀባ ያለን በፍቃዱ ዘሀይሉ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፉ ላይ የዓለም ሶስት ታላላቅ ሰዎችን እይታ ከአገራችን ነባራዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር አነጻጽሮልናል፡፡

በአልበርት አንስታይን ታዋቂ አባባል “The world will not be destroyed by those who do evil, but by those who watch them without doing anything.” (ዓለማችን የምትጠፋው ክፉ በሚያደርጉ ሰዎች ሳይሆን ክፉ ሲያደርጉ እያዩ ዝም በሚሏቸው ሰዎች ነው፡፡) የጀመረው ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር አይተው እነዳላዮ አላፊዎችን እነዲህ ሸንቆጥ አድርጓቸዋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ በየጓዳው ከመንሾካሾክ እና ከመብሸቅ ባሻገር ይሄ መንግስት (ይሄ ገዢ) ያለ እኛ ተገዢነት እና ፈቃደኝነት ሊጨቁነን እንደማይችል ገብቶን የተነጠቅነውን ነፃነት ለማስመለስ የምንሞክር እጅግ ጥቂቶች ነን፡፡ በተለይም ‹‹ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ ብዙሐኑን ስላላማከለ አንድ ቀን አገሪቱ ወደማትወጣው ችግር ውስጥ ትገባለች፣ ወዘተ. ወዘተ…›› እያሉ የጋን ውስጥ ትንታኔያቸውን የሚሰጡት ነገር ግን ለጋዜጣ እንኳን ማብራሪያ ለመስጠት ‹‹ስሜ ከተጠቀሰ አይሆንም›› የሚሉ ምሁራን ከአጥፊው ገዢው ፓርቲ ይልቅ – ለጥፋቱ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡››ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ተስፋዬ ገ/አብ የቅዳሜ ማስታወሻ በሚለው ጦማር በዕለተ ሰኞ ባኖረው ፅሁፍ አነጋጋሪው ‹ሰውለሰው› ድራማ መጠናቀቅን ተከትሎ የተዋናዮቹን ገጸባህሪ ወደ ነባራዊው አለም ቀይሮታል፡፡

አስናቀ አሸብርን እንደ‹ህወሃት ወኪል›

ማህሌትን እንደ ‹ኢትዮጵያ›

መስፍንን እንደ ‹ፕሮፌሰርመስፍን›

የመስፍንና የማህሌት ሁለት ልጆች እንደ ‹የኢትዮጵያ ህዝብ ወኪሎች›

ልኡል (የአስናቀን ወንድ ልጅ) እንደ ‹ከህወሃት የታወገዱት የህወሃት አመራር አባላት ወኪል›

ተስፋዬ በድራማው ከፍተኛ ትኩረት ያገኘውን አስናቀ የተባለው ገጸባህሪ ከህወሃት አሰራር ጋር እንዲህ አነጻጽሮታል፡፡

      ‹‹የወያኔ ድርጅታዊ አሰራሮች በድራማው በብዙ ቦታ ተጋልጠዋል። ለአብነት ማህሌት ህገወጥ ተግባር እንድትፈፅም ያደረጋት ራሱ አስናቀ ነበር። መልሶ ግን ማስረጃውን ለግል ጥቅሙ በማዋል ማህሌት እንድትንበረከክለት ለማድረግ ሲሞክር ይታያል። ወያኔ እነአባዱላን ወንጀል እንዲሰሩ ካደረገ በሁዋላ መልሶ እንደፈለገ የሚጠቀምባቸው በዚሁ መንገድ ነበር። እንደ ማህሌት በየዋህነት የፈፀሙት ወንጀል እንዳይጋለጥባቸው ሲሉ፣ ለህወሃት እየሰገዱ ለመኖር የተገደዱ በርካታ ባለስልጣናትን አውቃለሁ። ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

በየጊዜው ሽሙጦችን ጀባ የሚለን አቤቶክቻው) በስማቸው መጨረሻ ‹‹ዬ››ን እየጨመረ እያቆላመጠ የሚጠራራቸው አቶ መለስ ለቡድን ሀያ አገራት ስብሰባ ወደ ሜክሲኮ በሄዱ ጊዜ ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዳያቸውና እንደናፈቃቸው እንደ ድሮ ጎረቤት ቢሆኑ ኖሮ በቴሌቪዥን መስኮት ሲጠፉበት በሳሎናቸው መስኮት ለማየት ሙከራ እንደሚያደርግና ዛሬ ግን ተራርቀው ናፍቆታቸው ሲያስጨንቀው እንደሰነበተ ባያቸው ጊዜም መክሳታቸው እንዳሳሰበው ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትርዬ ከሱብኝ!››ባለው ጽሁፍ ምክር ቢጤም ጣል አርጎላቸዋል፡፡

‹‹ምን ሆኑ!? እንዴ ጠንከር ይበሉ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ! ቀጣዩ ጩኸት እኮ እየባሰነው የሚመጣው! ታድያ ጠንከር ጠንከር ማለት አይሻልም ይላሉ? ቁጣ እና ጩኸት ይህንን ያህል የሚረብሽዎት ከሆነ ግን ዘዴውን ልንገርዎት…!? እሺ አይሉኝም እንጂ ዛሬውኑ ስልጣንዎን ልቅቅ አድርገው አዲስ አገራዊ መግባባት፣ አዲስ አገራዊ ምርጫ ማከናወን! አቤት ያኔ ጤናዎ ላይ ራሱ ምን አይነት መሻሻል አንደሚመጣ ያዩት ነበር››በማለት ተቆርቋሪነቱን አሳይቷል፡፡

በመቀጠልም ከዚህ ቀደም በአዲስ አድማስ በወጣ ፅሁፍ አበበ ገላው ዋሽንግተን ዲሲያል ሄደው በርካታ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ስላሉ እነርሱን ፈርቶ ነው!” ብላችሁን ነበረ። ሰውየው እኮ አንገታቸውን የደፉት በዋሽንግተን ዲሲ ነው። በማለት ‹‹ምን አይነት አዲስ አድማሰ መጣ ደግሞ ባካችሁ!?›› ሲል ጥያቄ ጥሎ አልፋል፡፡ ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ከአቤ ወግ ሳንወጣ የኢሃዴግን ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ከአረብሳት ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት የኤርትራ ቴሌቪዥን ከፈለገ ይግባ በኢሳት ጉዳይ ግን አንደራደርም! ”ባሉት ንግግራቸው አቶ በረከትን ኢሳትን ትተው ለኤርትራ መፍቀዳቸው ወገንተኝነታቸውን እንዲሁም ‹‹ለአባይ መገደብያ ብለን በምናዋጣው ገንዘብ ራሳችንን እና እነኢሳትን መገደቡን ቀጥሎበታል።በዚህ አይነት ሁኔታ ነውለቀጣይ አርባ አመት ለመኖር ያቀድነው…? አረ ይደብራል!?………….

ተዉብሶቲቱ ዛሬም ታረግዛለች።

ተዉብሶቲቱ ዛሬም ትወልዳለች።

ተዉዛሬም ጀግና ይፈጠራል

ተዉዛሬም ንጉስ ይከሰሳል

ተዉኋላ ማጣፊያው ይቸግራል

ተዉምክር መስማት ይሻላል።

ተዉተዉተዉዉዉዉ…!

እያለ በዜማ አለቃቅሷል፡፡ ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡መልካም ሽሙጥ!

            ጉዳያችን የተኘው ጦማር ‹‹የአምባ ገነንነት ዲግሪው ስንት ነው?›› በተሰኘው ጽሁፍ ውስጥ ‹‹አንባገነንነት ምንድን ነው?›› ለሚለው ጥያቄ ዊኪፒድያን ጠቅሶ ይህን ፍቺ ይሰጣል፡፡ ‹‹ አንድ ሰው ወይንም የተወሰኑ ቡድሮች ፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር፤ በዘመናዊ ትርጉም ደግሞ ለህገመንግስት፣ለ ማህበረሰባዊ ህጎች ሁሉ የማይገዛ የመንግስት አስተዳደር›› ነው ይለዋል፡፡ በመቀጠልም የአምባገነኖችን አመራር ዘይቤ አንድ እርምጃ ወደፊት ሶስት እርሚጃ ወደኋላ ይለዋል፡፡ ‹‹ አምባገነን ስርዓት ስር የሚተዳደር ሃገር መንገድ ይሰራ ይሆናል ነገር ግን በመንገዱ ላይ የሚሔደው በፍርሃት የተሸበበ እና የተከዘ ህዝብ ነው፤

      በ አምባገነን ስርዓት ስር የሚተዳደር ሃገር ዩንቨርሲቲ ይከፍት ይሆናል:: ነገር ግን ስለምን መመራመር፤ ስለምን ማውራት፤ወዘተ እንዳለባቸው የሚነገራቸው ብቻ ሳይሆኑ የቱን ማንበብ ፤የቱን አለማንበብ፤ እንደሚገባቸው የተወሰነላቸው ምሁራን የሞሉበት ተቋም ይሆናል፤ ›› ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

ሰሞኑን የመነጋገሪያ ርዕስ ስለሆነው የቴልኮም አዋጅ እንዳልክ እነዲህ ጦምሯል፡፡ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

የዳንኤል ክብረት ጦማር <<…….ሰው ከእንስሳት ከሚለይበት ነገሮች አንዱ ይኼው ነው፡፡ ለምድራዊ ህልውናው ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ህልውናው ይጨነቃል፤ ያስባል፡፡ ሲኖርም ለእነዚያም ጭምር ይኖራል፡፡ እንስሳት በምድር ላይ ስላላቸው ኑሮ እንኳን አያስቡበትም፡፡ በደመ ነፍስ ይኖሩበታል እንጂ፡፡ ከዚያም አልፈው ሌላ ዓይነት አነዋወር የላቸውም፡፡ ትናንት የሚሉት ታሪክ፣ ነገ የሚሉት ተስፋ የላቸውም፡፡ ህልውናቸውን ሰው እንጂ ራሳቸው አይወስኑትም፡፡ ስለዚህም ብቻቸውን ሊመሰገኑም ሆነ ሊወቀሱ አይችሉም፡፡……>>ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡

Opportunism (ዝንደዳ?)

ጥንት

ከሰው ልጆች የስልጣኔ ታሪክ ጋር እኩል የሚጠቀስ ረጅም ታሪክ አለው፡፡ ከክርስቶስ ልደት አምስት መቶ አመታት በፊት አቴና የብዙ ሰዎች መመላለሻ በመሆኗ የከተማው ኑሮ የበረታ ወድድርን ፈጠረ፡፡ በዚህም ምክንያት ከተለመደው የተመጠነ ጤናማ አካልና መንፈስን የሚያጎለብት ትምህርት በላይ የሆነ ነገር ያስፈልግ ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩ (sophist)  ሶፊስት የተሰኙ ሊቃውንት  ሰባት የትምህርት ስልቶች (grammar, dialectics, Rhetoric, mathematics, geometry, astronomy and music) በደንብ አቀናብረው የከተማውን መላ ወጣቶች በተለይ የሀብታሞቹን ልጆች ደሞዝ እየተቀበሉ በመዘዋወር (አንድ ቦታ ሳይረጉ) ያሰተምሩ ነበር፡፡ ዋናው ዓላማቸውም እንዴት የወቅቱን ሁኔታ ተጠቅሞ መክበር እንደሚቻል ማሳየት ወይም አላግባብ ለመበልጸግ የሚረዳ ዕውቀት ማቀበል ነበር፡፡ ፖለቲከኛውን ለስልጣን፣ ነጋዴውን ወደሀብት በሌላም የኑሮ ዘርፍ ለተሰለፈው ለሥራው አስፈላጊውን ነገር ብቻ ይሰጡ ነበር፡፡

ይህ ነገርን ሁሉ ለግል ጥቀም ማበጃጀት ለዓለማችን ስልጣኔ እንደምሶሶ የሚቆጠሩት ቀደምት ፈላስፎች  (ሶቅራጠስ፣ ፕላቶና አሪስጣጣሊስ) በአጽንኦት የተቃወሙት ዐሳብ ነው፡፡ ትምህርት መታሰብ ያለበት ከጥቅም ባሻገር ነው፤ ከፍ ያሉ በሰውነት (ሰው በመሆን) በሚገኙ የስነምግባር ሕግጋትን በማስቀደም ነው፡፡ በተለይ ትልቁ የአውሮጳ መምህር ሶቅራጠስ ሰው እያንዳንዱን አጋጣሚ ለመመዝበር (to exploit) ወደወጭ ከማየቱ በፊት ‘ራስን ማወቅ’ን ፣ ወደውስጥ ማየትን ማስቀደም እንዳለበት አስተምሯል፡፡ ከእርሱ በወጉ የተማረው ፕላቶ ደግሞ ጉዳዩን አስፋፍቶ አስተምሯል፡፡ ይህ የትምህርት መሰረታዊ የአቅጣጫ ለውጥ በዘመናችን በምዕራባውያን መሪነት ዓለማችን ለደረሰችበት ቁሳዊም ሆነ ሌሎች ከፍታዎች እንደ መሰረትነት አገልግሏል፡፡የሶፊስቶችን ህጸጽ በቅጡ የተረዳው  ጀርመናዊ ባለቅኔ  “ዕውቀት ለአንዱ ለሁልጊዜ የሚያከብራት ወደላይ ወደአርያም የምትመራው ሰማያዊት ነብይት ናት፡፡ ለሌላው ግን በወተትና በቅቤ የምታገለግለው አንድ ወፍራም ላም ናት” ሲል የተናገረው ምነኛ! ድንቅ ነው፡፡ Read the rest of this entry