Author Archives: BefeQadu Z Hailu

ጋዜጣ እና መጽሄቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – ሁለት

(ከሰኔ 4 እስከ ሰኔ 10፤ 2004)

የኛ ፕሬስ ጋዜጣ ‹‹የኮንደምኒየም እጣ ውሃ በላው!››  የሚል ዜና ይዞ ወጥቷል፡፡ ‹‹… 128 ሰዎች ሁለትና ከሁለት በላይ የኮንደሚኒየም ቤቶችን ወስደዋል፣ ትክክለኛውን ተመዝጋቢ በመሰረዝና በሌላ በመተካት የሙስናና የዝምድና ሌብነት ተጧጡፏል፡፡…›› የሚሉ ችግሮችን የነቀሰው ዜና ምንጩ የመንግስት መስሪያ ቤት ነው፡፡ ‹‹… የፌዴራል የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ሂደት ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ያደረገ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ አደረኩት ካለው ጥናት መኖሪያ ቤቶቹን ለተጠቃሚዎች በማስተላለፍ ሂደት ላይ ለሙስና የተጋለጡ ስምንት የሚደርሱ አሰራሮችን አጋልጧል፡፡…››

‹‹ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጪ ያለው ሁሉ የጥፋት መንገድ ነው የሚል አመለካከት ነበረኝ›› ያሉት አቶ ገብሩ አስራት ለየኛ ፕሬስ ጋዜጣ ነው፡፡ አቶ ገብሩ ከጋዜጣው ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ቀነጫጭበን እንመለከታለን፡-

‹‹… እኛና ሌሎች ተቃዋሚዎች የምንሄድበት አቅጣጫ ይለያያል፡፡…››

‹‹… ከኢሕአዴግ ከወጣን በኋላ… ዴሞክራሲ ማለት ራሱ ምንድን ነው? ዴሞክራሲ ያለነፃ ጋዜጦች? ዴሞክራሲ ያለ ሲቪል ማሕበረሰብ? ያለነፃ የፍትሕ ስርዓት ሊኖር ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄዎችን አንስተናል፡፡ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሁሉም ተቋማት በአንድ ፓርቲ ስር መግባት አለባቸው የሚል አስተያየት አለ፡፡…››

‹‹…ልማትና ዕድገት ሁለት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ዕድገት ከየትም መጥቶ ጥቂት ሚሊየነሮችን ሊያስገኝ ይችላል፡፡ እነዚህ ሰዎች ገንዘብ ዘርፈው ካጠራቀሙም ዕድገት ነው፡፡…››

‹‹… እስቲ ቦሌ ሂዱና ተመልከቱ፡፡ ያ ሁሉ ሕንፃ የማነው? ምን ያህሉ እንዳሉ መቁጠር ትችላላችሁ፡፡ በመንግስት ስር የሚተዳደር ሰው ከ5 ሺህ እና 6 ሺህ በላይ አያገኝም፡፡ በዚህ ገንዘብ ልጆችን እንኳን ማስተማር አይቻልም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ልጆቻቸውን ውጭ አገር ልከው እያስተማሩ ነው፡፡ በመንግስት ሠራተኛ ደሞዝ ይሄ ሁሉ ሀብት ሊገኝ ይችላል ወይ? …››

‹‹… [የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር ሳሉ የግል ጋዜጦችን በተመለከተ ‹ትግራይ የማንም ቆሻሻ ማራገፊያ አትሆንም› ስለማለታቸው] ሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ የግል ጋዜጦች ፋይዳ የላቸውም የሚል አቋም በፓርቲ ደረጃ ይዘን ነበር፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ትክክለኛው አቅጣጫ ከዚያ ውጪ ግን የጥፋት መንገድ ነው የሚል እምነት ነበረን፡፡…››

የኛ ፕሬስ ቴዲ አፍሮ ሁለት ድግሶችን በአንድ ሳምንት መደገሱን ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ ላይ ‹‹… ባለፈው ቅዳሜ በጣይቱ ሆቴል በተከናወነው የምስጋና የምሳ ግብዣ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት የማስታወቂያ ባለሙያው አቶ ውብሸት ወርቅአለማሁ በወቅቱ አንድ ትልቅ ስብሰባ አቋርጠው ወደ ግብዣው እንደመጡ ከተናገሩ በኋላ ‹ይህንን ያደረግኩት ከእግዚአብሔር እና ከቴዲ አፍሮ ጥሪ ላይ መቅረት ያስቀስፋል› በሚል የተቀኘ የተጋነነ አድናቆታቸውን እንደሰነዘሩ ለመገንዘብ ተችሏል›› ብሏል፡፡

ምራቂ /ምርቃት/

የኛ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከኢትዮ ቻናል ተገንጥለው ነው የራሳቸውን ጋዜጣ የከፈቱት፡፡ ከኢትዮ ቻናል ሲወጡ ‹ሰዓት እላፊ› የተሰኘች ተነባቢ አምዳቸውን ከነካርቱነኛዋ ይዘዋት ወጥተዋል፡፡ ይቺ አምድ የ‹‹ሴተኛ አዳሪዎችን›› ቃለ ምልልስ ይዛ የምትወጣ ሲሆን ከግርጌዋ ‹‹ራስዎንና ቤተሰቦን ከኤችአይቪ ኤድስ ይጠብቁ፤ የዚህ ገፅ ስፖንሰር፡- ሰላም ባርና ሬስቶራንት (ሰበታ)›› የሚለውን ሲያነቡ ፈገግታ ታጭራለች፡፡

* *

‹‹ኢትዮ ቴሌኮም ዌብሳይቶችን የሚገድብ ኔትወርክ እየዘረጋ ነው›› ያለው ደግሞ መሰናዘሪያ ጋዜጣ ነው፡፡ በዝርዝሩም ‹‹በኢትዮጵያ በብቸኝነት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚሰጠውና በኢትዮጵያ መንግስት የሚተዳደረው ኢትዮ ቴሌኮም ግለሰቦችና ድርጅቶች በኢንተርኔት የሚለዋወጧቸውን መረጃዎች እየለጠፈ የሚመረምርና እንደአስፈላጊነቱ ዌብሳይቶችን የሚገድብ ቶር የተባለ ኔትወርክ እየዘረጋ መሆኑን ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደር የተባለ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን አስታወቀ፡፡…›› (በነገራችን ላይ መሰናዘሪያ ቶር በማለት የገለጸውን ዊኪፔድያ እንዲህ ሲል ይበይነዋል… Tor (short for The onion router) is a system intended to enable online anonymity. Tor client software routes Internet traffic through a worldwide volunteer network of servers to conceal a user’s location or usage from anyone conducting network surveillance or traffic analysis. በሌላ በኩል የቶር ፕሮጀክት ድረአምባ በኢትዮጵያ እንዳይነበብ ታግዷል፡፡)

መሰናዘሪያ በሌላ ዜና ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያ ድንበር ተሸጋሪ ጉዲፈቻ በስፋት ከሚካሄድባቸው አስር የአፍሪካ ሃግሮች በሁለተኛ ደረጃ መቀመጧን በመዲናችን በአዲስ አበባ በተካሄደው በአምስተኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ሕፃናት የፖሊሲ ኮንፈረንስ ላይ የቀረቡ መረጃዎች አመለከቱ፡፡…›› ብሎ ዘግቧል፡፡

* * *

ያለዕለቱ ዘግይቶ ረቡዕ የወጣው ፍኖተ ነፃነት  ‹‹በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተደረገው የማደራጀት ሙከራ እስረኞችን አስቆጣ›› የሚል ዜና በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል፡፡ ሲተነትነው ‹‹ቃሊቲ በሚገኘው ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች 1ለ25 እንዲደራጁ ታዘው አብዛኛዎቹ መደራጀት እንደማይፈልጉ አቋም በመያዛቸው አለመግባባት መፍጠሩን የዜና ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡… እስረኞቹ የእያንዳንዱን እስረኛ የ24 ሰዓት ውሎ የሚገመግም አደረጃጀት እንዲታቀፉ ቢጠየቁ እምቢተኛ ሆነዋል፡፡…›› Read the rest of this entry

ጋዜጦቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – አንድ

(የሳምንቱ ጋዜጦች ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3፤ 2004)

በአጭር ጊዜ ውስጥ ተነባቢነት ያተረፈውና በአንድነት ፓርቲ አሳታሚነት ማክሰኞ ገበያ ላይ የሚውለው ፍኖተ ነፃነት በመላው ሃገሪቱ ሰፊ የመረጃ መረብ ስላለው ሁሌም ዜናዎቹ ትኩስና ያልተሰሙ ናቸው፡፡ በዚህ ሳምንትም ከዜናዎቹ ውስጥ እነዚህ ነበሩበት፡-

‹‹…በጎንደር ፖሊስ የሟቾችን አስከሬን በመኪና መሬት ለመሬት አስጎተተ….

‹‹… የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ‹አቶ ሽንኩ ከፍያለውና አቶ ዳኛቸው የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው መሬት ለመሬት ሲጎተት ውሏል› ብለዋል፡፡….›› Read the rest of this entry