Category Archives: የአርብ ጫወታ
ሐዘን የሸሸገው ፈገግታ
ይህንን ያህል ከተጫወትን ይበቃናል:: ሐዘን ላይ ነሽና/ነህና ቀልደህ ሞተሃል ብንባል እንቀበላለን!
‘ተቃዋሚ’ ስንል
ባልቻን ፍለጋ
<<ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ፣መድፍ አገላባጭ፣ ብቻ ለብቻ፡፡>>
ደከመኝ ሰለቸኝ፣ እረፍት የማያውቀው፣አብዮታዊ መሪ፣ ጓድ መንግስቱ ነው፡፡
ከሌሎች ሀገሮች ህገ መንግስቶች በተለየ የኢፌድሪ ህገ-መንግስት ገበየሁ ቢሞት የባልቻ መገኛ የት እንደሆነ በግልፅ አይጠቁምም፡፡ ይልቅስ ህገ መንግስቱ ገበየሁ ‹በማይኖር ጊዜ› በሚል ጥቅል አጠራር ምክትሉ ‘የባልቻን’ ድርሻ ይወርሳል ይላል፡፡ ይህ ህገመንግስታዊ አንቀፅ ለትርጉም ክፍት ነው፡፡ ‘ገበየሁ’ ከስራ ለአጭር ጊዜ ሲርቅ ነው ብቻ ነው ተብሎ ሊተረጎምም ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አይ ‘ገበየሁ’ በሞተም ጊዜ ተክቶ ሊሰራ ይችላል ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ እንግዲህ ‘ባልቻን’ ከህጋዊ መስመር አገኘን የሚሉም ከሁለተኛው ትርጉም የተነሳ መሆን አለባቸው፡፡ አሁን ካለው ድባብ በመነሳት ይህ የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ይመስላል፡፡ ቢሆን እንኳን እንደ ‘ገበየሁ’ ህዝቡን ብቻውን ማገላበጡ ያጠራጥራል፡፡
እነሆ ‘ባልቻን’ ፍለጋ የጦር ካምፕ ውስጥ ነን ‘ባልቻን’ በግልፅ ለማየት ግን አልተቻለም፡፡ በርግጥም ‘ባልቻን’ ከጦር ካምፕ የምናገኝው ከሆነ ግን ጉዳዩ ያስፈራል፡፡ ቢያስፈራም ግን ‘ባልቻ’ በጦር ካምፕ ውስጥ መሽጎ ሊሆን ይችላል፡፡ የተገኝ እለት ‘ጀኔራል ባልቻ’ ሀገሪቱን በአንድ እግሯ አቆሟት መባሉ የማይቀር ነው፡፡
በርግጥም ‘ባልቻን’ ከምድረበዳ ያልነው ‘ከተቃዋሚው’ ጎራ ይመጣ ይሆን የሚለውን ግምታችን ነው፡፡ ዲያስፖራ ተቃዋሚው መግለጫ፣ ኮምኒኬ ወ.ዘ.ተ በማውጣት ዱብ ዱብ እያለ እራሱን እያሟሟቀ ይገኛል፡፡ መቸም ‘ባልቻ’ ‘አትላንቲክን’ ወይም ‘ሚድትራኒያንን’ አለዚያም ‘መረብ’ ወንዝን አቋርጦ ሊመጣ ይችላል ማለት ከባድ ነው! ኧረ በጣም ከባድ ነው፡፡ በሌላ ጎኑ ሀገር ውስጥ ያለውን ተቃዋሚ ስናይ አሁን ባለበት ሁኔታ ጀኔራሎቹ፣ ይሆኑ ወይስ ከቤተ መንግስት እያለ ከመገመት ውጭ ያው በምድረበዳ እየተንከራተተ ነው፡፡ እናም አንድ ነገር ላይ እርግጠኛ መሆን እንችላለን አዎ ‘ባልቻን’ በምድረ በዳ መፈለግ ከንቱ ልፋት ነው፡፡
ስለምንስ ከምሁራን መካከል ትፈልጉኛላችሁ? !
ገነትም ከነዚህ ሰልጣኞች መካከል አንዷ ስትሆን በ3 አመት የዩንቨርስቲ ቆይታዋ Applied Biology ያጠናች ስትሆን ከተቻለ አንድ ፋርማሲ ሰራተኛ ውስጥ አለዚም መምህር እሆናለው የሚል ህልም ነበራት፡፡ በስልጠናው የሰማችው የስራ መስክ ግን አልተዋጠላትም፡፡ ተደራጅቶ የባልትና ውጤቶችን መሸጥ፣ የከተማ ግብርና ላይ መሰማራት፣ የኮብል ስቶን ማንጠፍ ስራ፣ፓርኪንግ ወ.ዘ.ተ፡፡
ይህ በ2004 ዓ.ም ተማሪዎቻቸውን ያስመረቁ የሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች እና ተማሪዎች ሰሞነኛ ቆይታ ነው፡፡
ትምህርት
የሰው ልጅ ሁሉን ያውቅ ዘንድ አይቻለውም ስለዚህም ስለ ክዋክብቱ መረዳቱ የበዛለት ላላወቀው እሱም ስለ ስነ ተዋልዶ እውቀቱ ከሌለው ከአዋቂው የሚቀስምበት ስርዓት ነው ትምህርት፡፡ አንድ ሰው አቃቂ ምሁር ይባል ዘንድ በሁሉም የትምህርት ዘርፎች የዕውቀት ላቂያ ይኑረው ያኔም አዋቂ ይባላል ይለናል የRenaissance Man Theory፡፡ ለዛም ይመስላል በአብርሆት ዘመን (15-18 Century) የነበሩ ምሁራን ሁሉን አቀፍ እውቀት ነበራቸው ልንል የምንችለው፡፡ የፍልስፍና፣ የሂሳብ፣ የስነ-ክዋክብት፣ የስነ-ሰብ ወ.ዘ.ተ እውቀቶችን አንድ ምሁር አቅፎ ሊይዝ ይችል ነበር፡፡
ይሄ ትክክል አይደለም ይልቅስ በህብረተሰቡ ውስጥ እምርታ ይመጣ ዘንድ የስራ ክፍፍል (Division of Labor) ወሳኝ ነው ብሎ ስኮትላንዳዊው የስነ-ምጣኔ ምሁር አዳም ስሚዝ የሀሳብ ሽግግር ካደረገ ወዲህ፡፡ እያንዳንዱ ህብረተሰቡ አካል አንድ የስራ መስክ ላይ በተለየ(Specialize) አድርጎ ጥናት ካደረገ እና ከተማረ በዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያመጣል በሚል የትምህርት ስርዓቶቹም በዚህ ሀሳብ መቀረፅ ጀመሩ፡፡ ባጫ ምህንድስና ፣ አበበ ህግ ፣ አይዳ እርሻ ወ.ዘ.ተ እየተማሩ በያዙት ሙያ ላቂያን ማሳት ይችላሉ የሚለው የ Specialization Theory አሁን ድረስ በትምህርቱ ዘርፍ ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡
ሱፍ ለባሽ ምሁር
በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ታሪክ መቶ አመት እንኳን አልደፈነም ፡፡ የመጀመሪያው ዘመናዊ የመንግስት ትምህርት ቤት በ1908 ነው የተቋቋመው እስከ ጣልያን ወረራም ብዙ ተማሪዎችን ማስተማር አልተቻለም በአብዛኛውም ከውጭ ተምረው የመጡ ኢትዮጵያዊያን ነበሩ እንደ ምሁር የሚቆጠሩት፡፡ ከነዚህ በውጭ ተምረው የመጡ 120 ተማሪዎች ውስጥ ጣልያን በተለምዶ የሚያዚያ 28ቱ ጭፍጨፋ ተብሎ በሚጠራው ድርጊት 75 በመቶዎቹን እንደ ገደላቸው የመንግስትን ሪፖርት ጠቅሰው Mrgery Perham, The Government of Ethiopia ባሉት መፅ ሃፋቸው ያስረዳሉ፡፡
እንግዲህ በጣሊያን ወረራ 75 በመቶ የተማረ ሀይሏን (በነገራችን ላይ የተማረው ሀይል 75 በመቶ ማለት 90 ምሁራን ብቻ ማለት ነው) ካጣች በኋላ እስከ ንጉሱ የስልጣን ዘመን ማክተሚያ ድረስ የተማሪዎች ቁጥር (በውጭም በሀገር ውስጥም ተምረው የመጡት) በብዙ እጥፍ ጨምሯል፡፡
- አለ ከተባለ የፈረንሳይ ህግ ትምህርት ቤት ህግ ተምሮ የሀረርጌ አውራጃ አስተዳዳሪ የእልፍኝ አሽከር፣
- Literature 4 ዓመት ሙሉ እነ ሸክስፒርን፣ እነ ሞንታኝን፣ እነ ዳንቴን እንዲያም ሲል እነ ቶልስቶይን ሲያጠና ከርሞ በንግድ ሚኒስቴር የወርሃዊ የዋጋ ጥናት ባለሙያ መሆን፣
- የምጣኔ ሀብት ትምህርትን እንደ ውሃ ጨልጦ በበጌምድር አውራጃ የደምቢያ ወረዳ የመንግስት ሹም ወ.ዘ.ተ እየሆኑ ነበር እነዚህ እውቀትን እና አለባበስን ከአውሮፓ የቀዱ ምሁራን ወደ ስራ አለም የሚሰማሩት ፡፡
በርግጥ አቢዮተኛ ው ያ ትውልድም የዚህ ሱፍ ለባሽ ምሁር አካል ነበር፡፡
የተማረ ሁሉ ያስተምር
ደርጉ መጣ ሁሉንም ነገር ወደ ጦር ግንባር ከማለቱ በፊት የትምህርት ዘመቻ ጀመረ ‘ማሃይምነት አይነስውርነት‘ ነው በሚል የሚያሸማቅቅ መፈክር የገጠሩን ህዝብ ስሙን ይፅፍ ዘንድ ፊርማ በእርሳስ ይፈርም ዘንድ አስቻለው፡፡ ነገር ግን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚወጡ ተማሪወች የተማሩትን ትምህርት የት አደረሱት ከተባለ፡፡ ግማሾቹ አቢዮት ጠባቂ፣ ግማሾቹ የቀበሌ ሹም ፣ ወታደር ቤትም የገቡ አሉ፡፡
ይልቁንም ደርጉ ተማሪዎችን ከነ ኢህአፓ ጋር ‘ንክኪ’ አላቸው በሚል በጥርጣሬ ነበር የሚመለከታቸው፡፡ ይባስ ብሎም ከሀገር በፊት የምን ትምህርት ብሎ በተለምዶ ‘ምሁሩ ጦር’ የሚባለውን ወታደር ከዩንቨርስቲ አፍሶ ብላቴ ጦር ማሰልጠኛ ከተተ፡፡ የተማሩት ትምህርትም አላማው ጠፋባቸው ለነዚህ ምሁር ወታደሮች፡፡
ስለምንስ ከምሁራን መካከል ትፈልጉኛላችሁ? !
ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ከሰራቸው አመርቂ ስራዎች አንዱ ትምህርትን በነፃ ተደራሽ ለማድረግ ያደረገው ጥረት እና ያም ያመጣው ውጤት ነው፡፡ አጠቃለይ የትምህርት ፖሊሲ በ1986 ዓ. ም ከወጣ በኋላ ብዙ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተሰርተዋል፣ የትምህርት ቤቶች የቅበላ አቅም በብዙ እጥፍ ጨምሯል፣ ከ30 በላይ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ተገንብተዋል፡፡
ነገር ግን የትምህርት ፖሊሲውን ሁለት ዋነኛ ተግዳሮቶች አንቀው ይዘውታል፡፡
1. የትምህርት ጥራት ጉዳይ፡
መንግስትም እንደሚለው ዋነኛው የትምህርት ፖሊሲያችን ፈተና የጥራት መጓደል ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ:
- የዩንቨርስቲ የChemistry ምሩቅ ተማሪዎች Chemistryን Khemistry እያሉ እንደሚፅፉ ይነገራል፡፡
- አራቱን የሂሳብ ስሌቶች የመለየት ችግርም የምሩቃኑ ሌላው ጣጣ ነው፡፡
- በሶሲዎሎጅ ተመርቀው ካርል ማርክስ ሲባል እሱ ደግሞ ማነው? ማለትም ያስደነግጣል፡፡
- ህግ ተምረው የCivil Right እና የCivil Code ልዩነትን አለማወቅም ይወራል፡፡
አዎ ጥራቱ ችግር ውስጥ ነው፡፡
2. ሁለተኛው እና አዲሱ የትምህርት ፖሊሲው ችግር ሰዎች ተምረው በተማሩበት ትምህርት መስክ ሊሰሩ አለመቻላቸው ነው፡፡
የማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን የ2011 ዓ.ም የከተማ ስራ አጥነት 18 በመቶ እንደሆነ መረጃው ያስረዳል ፡፡ሌሎች አለማቀፍ ተቋማት ደግሞ መጠኑ ከዚህ እንደሚልቅ ይገልፃሉ፡፡
እንግዲህ ከዩንቨርስቲ የሚወጡት ምሩቃን ከነዚህ ስራ አጦች ቁጥር ላይ የሚደመሩ ናቸው፡፡ ይሄን ቁጥር ለመቀነስ ይመስላል መንግስት ሰሞኑን እንደምንሰማው ወጣቶችን በተለያዩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ተግባራት ላይ እንዲሰማሩ እያደረገ የሚገኝው፡፡
- ችግሩ ግን አንድ ሰው Computer Science ተምሮ የኮብል ስቶን ጠረባ ላይ የመሰማራቱን ጥቅም ስናሰላስለው ነው፡፡
- ችግሩ ግን አንድ ወጣት በPhysics ተመርቆ በከተማ ግብርና ተግባር ላይ ሲሰማራ የተማረውን ትምህርት ተግባር ላይ እንዴት ሊያውለው ይችላል? ያልን እንደሆነ ነው፡፡
- ችግር የሚሆነው Afan Oromo & Literature የተማረች ወጣት በባልትና ውጤት ስራ ላይ ተሰማርታ ስናይ ነው፡፡
ይሄ ስኬት ነው እንዴ ለመሆኑ?
Nelson Mandela በግለ-ታሪካቸው ላይ ስለ ትምህርት ሲናገሩ :
“Education is the great engine of personal development. It is through education that the daughter of a peasant can become a doctor, that a son of a mineworker can become the head of the mine, that a child of farm workers can become the president of a nation.”
አሁን ወዳለው ሀገራችን የትምህርት ውጤት ስንሄድ ማንዴላ እንደሚሉት ትምህርት የገበሬውን ልጅ ዶክተር ፣ የማዕድን ቆፋሪውን ልጅ የሀገር መሪ የሚያደርግ መሳሪያ ነው ያሉትን የትምህርት Upgrade የማድረግ ሚና Downgrade በማድረግ የተተካ ያስመስለዋል፡፡ አለዚያማ ስለ ፓለቲካል ህልዮት ሲማር የከረመ ወጣት እንዴት የብየዳ ስራ ላይ ይሰማራል?፡፡
ገነት ‹‹ስለ ስራ አስበሽ ታወቂያለሽ?›› ተብላ ስትጠየቅ ‹‹እኔ የምማረው እናቴ ተመርቄ ስታየኝ ደስ እንዲላት ነው እንጅ ስራ መስራት አልፈልግም›› ትላለች፡፡ እንግዲያውስ ገነቶችን ከምሁራን መካከል መፈለግ ምን ሊረባ?
የኪራይ ሰብሳቢ ማዕበል
“Rent-seeking may, indeed, impose costs to the economy as high, if not higher, than those arising from corruption.”
Anthony Ogus , Corruption and Regulatory Structures.
ገንዘብን መግዛት (Rent seeking)
በስነ ምጣኔ ሳይንስ ከእያንዳንዱ ኢኮኖሚ ጀርባ ብዙ ጋሬጣዎች(Economic Inefficiencies) ሊኖሩ ይችላሉ ለምሳሌ እንደ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲ ክፍተት፣ ሙስና ፣ ገንዘብን መግዛት (Rent seeking) ወ.ዘ.ተ ናቸው፡ ከነዚህ የኢኮኖሚ ማነቆዎች ውስጥ ገንዘብን መግዛት (Rent seeking) የተባለውን ስንመለከት፡፡በአጠቃለይ ኢኮኖሚስቶች ‹‹እሴት አልባ ትርፍ ወይም አሁን ያለው ገንዘብ በራሱ ያለምንም ዕሴት ማጎልበት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲገዛ ለዛ መበርታት›› ብለው ይተረጉሙታል፡፡
John Mbaku የተባሉ ኢኮኖሚስት ‘Corruption and Rent-seeking’ ባሉት ፅሁፋቸው ገንዘብን መግዛትን ‹‹የመንግስት ፖሊሲዎችን ውጤት ለማስቀየር የሚደረግ እንቅስቃሴ›› ብለው ይተረጉሙታል ፡፡ የገንዘብን መግዣ ድርጊቶች ስንመለከት የተያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
Anne Kruger የተባሉ የሚኒሶታ ዩንቨርስቲ ኢኮኖሚስትThe Political Economy of Rent-Seeking Economy’ ባሉት ፅሁፋቸው ‹‹ገንዘብን ለመግዛት የሚደረገው ውድድር አንዳንዴ ንፁህ እና ህጋዊ በሆነ መልኩ አንዳንዴ ደግሞ እንደ ሙስና፣ ጥቁር ገበያ እና ህገወጥ የዕቃ ማስተላለፍ ያሉትን ህገወጥ መንገዶች በመጠቀም ሊከናወን ይችላል›› ይላሉ፡፡ ይሄም ገንዘብን መግዛት ሁሌም ህገወጥ ተግባር ብቻ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ ያደርሰናል ማለት ነው፡፡
John Mbaku ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፋቸው በታዳጊ ሀገራት የገንዘብን መግዛት ተግባር በስፋት የሚታይ እንደሆነ ይሄም በከተሞች ጎላ ብሎ እንደሚታይ እና ከገንዘብን መግዥ ተግባራት ማነኞቹ ቢሮክራሲያዊ ሙስና እና የፖለቲካ አመፅ ማስነሳት መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ አያይዘውም ‹‹በመንግስት የተያዙ ሞኖፖሊዮች ለገንዘብን መግዣ ተግባራት ዋነኛዎቹ መፈልፈያዎች ናቸው›› ይላሉ፡፡ ‹‹ምክንያቱም እነዚህ ኖፖሊዩች ተወዳዳሪ ስለሌላቸው ገንዘብን እንደፈለጉ ያደኑታል ያለምንም ማህበራዊ አበርክቶ ደንበኞችም ያለምንም አማራጭ የቀረበላቸውን አገልግሎት ይጠቀማሉ፡፡››
ኪራይ ሰብሳቢነት ስንል
ኢትዩጵያ ውስጥ የገንዘብን መግዣ (Rent Seeking) ፅንሰ ሃሳብ ከሶሻሊዝም ጋር አብሮ እንደጎለበተ ለማየት ይቻላል እንደ ካፒታሊዝም ውድቀት ተደርጎ በመወሰድ፡፡ በዋነኛነት ግን የህብረተሰቡ ተወስኦ(Public Discourse) አካል እየሆነ የመጣው ከ1997 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ምርጫ በኋላ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ‘AFRICAN DEVELOPMENT: DEAD ENDS AND NEW BEGINNINGS’ ባሉት እና ከ600 ገፅ በላይ እንዳለው የተነገረውን የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያቸውን ከሆነው ፅሁፍ ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ (Preliminary Draft) ላይ በ50 ገፅ ቁራጭ ታሪኮች (Excerpts) ፅሁፍ እ.አ.አ በ2006 ዓ.ም አቅርበዋል፣ ለውይይት አላማ በሚል፡፡ የዚህ ፅሁፍ ዋነኛ ማጠንጠኛም ይሄው የገንዘብን መግዛት (Rent Seeking) ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ለዛም ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ 50 ገፅ አካባቢ ፅሁፍ ውስጥ ወደ መቶ ለሚጠጋ ጊዜ Rent Seeking የሚለውን ቃል ይደጋግሙታል፡፡ አንድ ምዕራፍም በአፍሪካ ያለውን የገንዘብን መግዛት (Rent Seeking) ፖለቲካል ኢኮኖሚን ለመተንተን አውለዋል፡፡
እንደ መደምደሚያም “Only when there is a state that has the characteristics of a developmental state can one meaningfully discuss the elimination of rent-seeking behavior. In its absence rent-seeking will be rampant no matter what the size of the state might be.” በማለት የገንዘብን መግዛት ክፉ ጠንቅን የሚዋጋው ልማታዊ መንግስት (Developmental State ) እንጅ ከዳር ቆሞ የሚመለከት መንግስት (Night watch man State) አይደለም በማለት ሀሳባቸውን ያሳርፋሉ፡፡
እንግዲህ በኢትዮጵያ የገንዘብን መግዛት ፅንሰ ሀሳብ ‘ኪራይ ሰብሳቢነት’ በሚል ስም ዋነኛ የውይይት አርዕስት የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከላይ የጠቀስነውን ፅሁፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ የኢህአዴግ ዋነኛ ልሳኖችም ጉዳዩን ለህብረተሰቡ በሰፊው ማቀበል የጀመሩት ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው በኋላ ላይ ከፓርቲው ልሳኖች በተጨማሪ የመንግስት የሚዲያ ተቋማትም ጉዳዩ የሀገሪቱ ታላቅ ስጋት እንደሆነ አድርገው እያቀረቡት ይገኛሉ፡፡
‹‹ደላሎችን በሙሉ ኪራይ ሰብሳቢ ናቸው ማለት ተገቢ አይደለም››
ይህ አንድ የደላላ ማህበር ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የፃፈው ደብዳቤ ርዕስ ነው፡፡ አሁን ባለው አካሄድ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በ2 ጎራ ከፍሏል ማለት ይቻላል፡፡ የልማታዊነት ጎራ እና የኪራይ ሰብሳቢነት ጎራ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢው ማነው? ካላችሁ እስከ አሁን ድረስ በፓርቲው ሰነዶች ውስጥ ግልፅ ትርጉም አልተሰጠውም ይልቅስ ድርጊቶችን ብቻ በመጥቀስ ይሄ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው ይሄ ልማታዊነት ነው በማለት እየተገለፀ ነው፡፡
ጨዋታ ነውና ጉዳዩን እንደሚከተለው እንየው እስኪ ፡
* ኪራይ ሰብሳቢነት ምንድን ነው?
– እስከ አሁን የተገለፀ ነገር የለም፡፡
* የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች ምንድን ናቸው?
– ‹‹ኪራይ ሰብሳቢው በዋነኛነት የመሸገባቸው፣ መሬት፣ ግብር፣ ንግድ፣ የመንግስት ግዥ አሰራሮች ናቸው›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 45-46
* ኪራይ ሰብሳቢነት በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ እንዴት ይገለፃል?
– ‹‹የመንግስት መዋቅሩ የኪራይ ሰብሳቢነት ፍርፋሪ በመለቃቀም የተጨማለቀ ወይም ከዛሬ ነገ ፍርፋሪ ይጣልልኝ ይሆናል ብሎ የሚጠብቅ ሰው ያልተለየው መዋቅር ነው፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት የውስጥ አርበኛ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 28-29 እያለ የመንግስት ሰራተኛውን ይከሳል እንዲያም ሲል ‘የመንግስት ሌቦች’ ይለዋል፡፡
* ኪራይ ሰብሳቢነት በጥቅሉ በሀገሪቱ እንዴት ይገለፃል?
– ‹‹ከአስር አመታት በፊት የሀገራችን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተመቸ እና ኪራይ ሰብሳቢው የሚቆጣጠረው ነበር፡፡ኪራይ ሰብሳቢነትን የመታገል እና የማዳከም ስራችን በመሰረቱ በትክክለኛ አቅጣጫ እየተጓዘ ነው ፡፡ አደጋውን ለይተናል ምንጩን እና የትግል አግባቡን አስቀምጠናል፡፡ ተግባራዊ ትንቅንቅ ጀምረናል፡፡›› እንዲሁም ‹‹ኪራይ ሰብሳቢው መግቢያ መውጫውን ከማወቁ እና የቁማርተኛ አይነት ድፍረት ተጠናወተው በመሆኑ ከእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኝት ከሚገባው በላይ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 45
* ኪራይ ሰብሳቢነትን በዋናነት መታገል ያለበት ማነው? ብላችሁ ስትጠይቁ ደግሞ፡
– ‹‹የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር በመታገል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የዜግነት ግዴታ ያለበት ቢሆንም መምህራን ካለባቸው ብቁ ዜጋ የመቅረፅ ኃላፊነት አኳያ ያለባቸው ኃላፊነት ድርብ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 54 ብሎ መምህሩን ሀላፊነት ይሰጠዋል፡፡
* የኪራይ ሰብሳቢነት እና የዕምነት ግንኙነት እንዴት ነው ካላችሁ?
– ‹‹አክራሪነትን ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር አስተሳስረን እንፋለመዋለን›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 38 እንዲሁም ‹‹አክራሪነትን ከኪራይ ሰብሳቢነት ነጥለን መታገል አንችልም›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 40 በማለት የኪራይ ሰብሳቢነትን አድማስ ከአክራረነት ጋር አያይዞ ያየዋል፡፡
* Where is the Rendezvous of this ‘ኪራይ ሰብሳቢነት’? ካላችሁ መልሱ :
– ‹‹የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከቶች በከተሞች ሰፋ ያለ አድማስ አላቸው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 31
* ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዴት ይታያሉ?
– ‹‹በሀገራችን የሚገኝው የተቃውሞ ቡድን ባነገበው አላማና በኪራይ ሰብሳቢነቱ አንድ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ጋቢት ሚያዚያ 2002 ገፅ 4
* ለመሆኑ ኪራይ ሰብሳቢነት በህግ ያስቀጣል?
– ‹‹ዋናዎቹን ኪራይ ሰብሳቢዎች ወደመቅጣት የምንገባው ከመጥፎ ተግባር አልላቀቅ ሲሉና ማረሚያ ሌላ አማራጭ ሲጠፋ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 33
* በአጠቃለይ ከኢትዮጵያዊያን ምን ይጠበቃል?
– ‹‹የልማት አብዮቱን ለማጎልበት ኪራይ ሰብሳቢነትን ለቀቅ ልማታዊነትን ጠበቅ›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 6 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 36 እያለ ፓርቲው ምላሽ ይሰጣል ጉዳዩንም ከመሬት ወራሪዎች እስከ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እንዲሁም መምህሩን እና የሀይማኖት መሪዎችን እየነካካ መጨረሻ የሌለው እስኪመስል ድረስ ይጓዛል፡፡ ይሄን ስንመለከትም ኪራይ ሰብሳቢነትን እንረዳው ዘንድ ይከብድብናል፡፡ ምን ማለት ይሆን? ያስብለናል::
ለማንኛውም፡
‹‹ጉልበተኛ ይሰይማል፡፡ መሰየም የጉልበተኛ አንዱ እና ትልቁ አቅም ነው፡፡ አንተ ሽብረተኛ ነህ ምክንያቱም ፂምህ ከደረትህ ደርሷልና፣ አንች ያለፈውን ስርዓት ናፋቂ ነሽ ምክንያቱም አባትሽ ለንጉሱ ስርዓት አፋሽ አገንባሽ ነበርና፣ አንተ መንግስትን በሀይል ለመገልበጥ ከሚሰሩ ህሎች አንዱ እና ዋነኛው ነህ ምክንያቱም ሀምሌ 27 የተባለ ፓርቲ ልሳን እቤትህ ተገኝቷልና ወ.ዘ.ተ እያለ ስያሜው ይቀጥላል፡፡ ምክንያቱም ጉልበተኛ ሲሰይም ማንም ተው አይለውምና፡፡››
ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ ?
ህዝብ አብሮ ሲኖር ግጭት ሊያስወግደው የማይችለው ነገር ነው፡፡ የሰዎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እስካለ ድረስ ግጭት አለ፡፡ በግጭቱ ጉልበተኛው አሸንፎ ተሸናፊውን እንደፈለገ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ እንግሊዛዊው የስነ መንግስት ሊቅ Thomas Hobbes ‘State of Nature’ የሚለው ወይም ጉልበተኛ የሚገዛበት ደካማ የሚጠቃበት እና Hobbes “ life is solitary, poor, nasty, brutish, and short” ብሎ የገለፀው ሀሳባዊ አለም ነው፡፡
ይህ እንዳይሆን ህዝብ ስምምነት ላይ ደረሰ ይሄንም ስምምነት በልቦናው ፈረመ ‘መንግስት’ የሚባልም አካል መሰረተ፡፡ ይህ አካልም ከህዝቡ ጉልበት ተቀንሶ ጉልበተኛን ይቀጣ ዘንድ ተሰጠው እንዲሁም ይህ መብት እንዳለው ሁሉ የህዝቡን ሰላም የማስጠበቅም ግዴታ ተሰጠው፡፡ ማን ? መንግስት የተባለው አካል፡፡
ታዲያ መንግስት በጦር በጎራዴ ብቻ ሰላምን አያሰጠብቅም ይልቅስ ሰላማዊ መሳሪያውን ይመዛል ይሄም መሳሪያ የመንግስት ህግ ነው፡፡ ህዝቡም ያከብረው ዘንድ ይወዳል ወይም ይገደዳል፡፡ ስለዚህ የመንግስት ህግ ማለት መንግስት ህዝብ ከራሱ የተፈጥሮ ስልጣን ቀንሶ መንግስት ለተሰኝው አካል ስለሰጠው መንግስቱ ይሄን የህዝብ አደራ ለመጠበቅ የሚቀርብ በትር ነው፡፡
በመሰረቱ የኢትዮጵያም ታሪክ በዚህ የመንግስት ህልዮት ይገዛል፡፡ ነገሩ የሚበላሸው መንግስት የተባለው አካል የህዝብን አደራ በልቶ ሌላ ዳቦ መጋገር ሲጀምር ነው፡፡ የህዝቡን ዳቦ በልቶ የራሱን ሽልጦ ሲያነጉት ነው መከራው፡፡
መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የህዝብን ሰላም እና ጥቅም ለመስጠበቅ ህግ ያወጣሉ፣ ይከለክላሉ፣ ያስጠብቃሉ፡፡ ይሄም እውነት በጠነከረ ሁኔታ አሁን ባለንባት ኢትዮጵያ ገዝፎ ይታያል፡፡
ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ ?
ህዝብ አብሮ ሲኖር ግጭት ሊያስወግደው የማይችለው ነገር ነው፡፡ የሰዎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እስካለ ድረስ ግጭት አለ፡፡ በግጭቱ ጉልበተኛው አሸንፎ ተሸናፊውን እንደፈለገ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ እንግሊዛዊው የስነ መንግስት ሊቅ Thomas Hobbes ‘State of Nature’ የሚለው ወይም ጉልበተኛ የሚገዛበት ደካማ የሚጠቃበት እና Hobbes “ life is solitary, poor, nasty, brutish, and short” ብሎ የገለፀው ሀሳባዊ አለም ነው፡፡
ይህ እንዳይሆን ህዝብ ስምምነት ላይ ደረሰ ይሄንም ስምምነት በልቦናው ፈረመ ‘መንግስት’ የሚባልም አካል መሰረተ፡፡ ይህ አካልም ከህዝቡ ጉልበት ተቀንሶ ጉልበተኛን ይቀጣ ዘንድ ተሰጠው እንዲሁም ይህ መብት እንዳለው ሁሉ የህዝቡን ሰላም የማስጠበቅም ግዴታ ተሰጠው፡፡ ማን ? መንግስት የተባለው አካል፡፡
ታዲያ መንግስት በጦር በጎራዴ ብቻ ሰላምን አያሰጠብቅም ይልቅስ ሰላማዊ መሳሪያውን ይመዛል ይሄም መሳሪያ የመንግስት ህግ ነው፡፡ ህዝቡም ያከብረው ዘንድ ይወዳል ወይም ይገደዳል፡፡ ስለዚህ የመንግስት ህግ ማለት መንግስት ህዝብ ከራሱ የተፈጥሮ ስልጣን ቀንሶ መንግስት ለተሰኝው አካል ስለሰጠው መንግስቱ ይሄን የህዝብ አደራ ለመጠበቅ የሚቀርብ በትር ነው፡፡
በመሰረቱ የኢትዮጵያም ታሪክ በዚህ የመንግስት ህልዮት ይገዛል፡፡ ነገሩ የሚበላሸው መንግስት የተባለው አካል የህዝብን አደራ በልቶ ሌላ ዳቦ መጋገር ሲጀምር ነው፡፡ የህዝቡን ዳቦ በልቶ የራሱን ሽልጦ ሲያነጉት ነው መከራው፡፡
መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የህዝብን ሰላም እና ጥቅም ለመስጠበቅ ህግ ያወጣሉ፣ ይከለክላሉ፣ ያስጠብቃሉ፡፡ ይሄም እውነት በጠነከረ ሁኔታ አሁን ባለንባት ኢትዮጵያ ገዝፎ ይታያል፡፡
ለምሳሌ ኢህአዴግ ስልጣን ይዞ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ከፀደቀበት ህዳር 1987 ዓ.ም ወዲህ፡
– ወደ 750 የሚደርሱ አዋጆች፣
– ከ200 በላይ ደንቦች፣
– በሽዎች የሚቆጠሩ መመሪያዎች ወጥተዋል፡፡
እነዚህ ህጎች በአጠቃላይ መብትን ማስጠበቂያና ግዴታን መስጫ ናቸው፡፡ እንደ ሁሉም የህግ ባህሪያት፡፡ አስገራሚ የሚሆነው ጉዳይ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ የሚወጡ ህጎች ብርታት እና ሀይል ነው፡፡
የፕረስ ህጉ አዋጅ ቁጥር 590/2000 ፣ የሙያ ማህበራት ህግ አዋጅ ቁጥር 620/2000፣ የፀረ-ሽብር ህግ አዋጅ ቁጥር 652/2001፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ቁጥር 662/2001፣ የሊዝ ህግ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ብለን የዋነኛዎቹን ብርቱ ህጎች መዘርዘር ይቻላል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪ ደግሞ በረቂቅ ደረጃ ያለ የሁሉንም ሰው በር ሊያንኳኳ የሚችል አዲስ የህግ ረቂቅ የቴሌኮም ህግ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
እንግዲህ ለጨዋታችን ይሄን ረቂቅ ህግ ከፀረ-ሽብር ህጉ ጋር አብረን እንመልከተው፡
– ማሞ እና ብሪቱ አዲስ ሙሽራዎች ሲሆኑ የፍቅራቸው ሙቀት አልበርድላቸው ብሎ የሚያደርጉትን አሳጥቷቸዋል:: ለዚህም ይመስላል ማሞ ህዝብ ይወቀው፣ ይመልከተው ብሎ ከብሪቱ ጋር ሲቃበጡ እና የጭናቸው ፍም በጋለበት ወቅት እያደረጉት ያሉትን ድርጊት ምስል የፌስቡክ ገፁ ላይ የለጠፈው፡፡ ግማሾቹ ጓደኞቹ ምነው ማ ሞ ! ሲሉት ግማሾቹ ደግሞ ኧረ ማሚሻ ቀወጥሽው ሎል ምናምን ብውለታል፡፡
በአዲሱ ረቂቅ የቴሌኮም አዋጅ አንቀፅ 6 መሰረት ማንኛውም ሰው ፀያፍ የሆነ ነገርን ማንኛውንም የቴሌኮም መሳሪያ ተጠቅሞ ለህዝብ ያሳወቀ ከሆነ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 640 የተደነገገው ቅጣት እንዳለ ሁኖ ከ 3 – 8 ዓመት ያስቀጣል፡፡ እንግዲህ ህጉ ከፀደቀ አቶ ማሞንም መልካም የእስር ወቅት ለማለት እንገደዳለን እንዲሁም ሞቶ በክር መታሰር ነው ክፉ ስምንት ዓመት እማ ስምንት ቀን ናት ብለን ለማፅናናት እንወዳለን፡፡
– አያንቱ የዩንቨርስቲ ትምህርቷን ጨርሳ በአንድ የመንግስት ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ ለሁለት ዓመታት ካገለገለች በኋላ በአንድ የምስራቅ አውሮፓ ሀገር ነጻ የትምህርት ዕድል ታገኛለች፡፡ ማንንቷን እና የቋንቋ ችሎታዎን ለማረጋገጥ በሚል ዩንቨርስቲው አያንቱን በ Skype ለሚደረግ የ30 ደቂቃ ቃለ መጠይቅ ይጋብዛታል፡፡ አያንቱም በተቀጠረችበት ሰዓት ሰፈር ውስጥ የሚገኝ አንድ ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ተገኝታ ቃለ ምልልሱንም በድል ትወጣለች፡፡ የማረጋጋጫ ደብዳቤም ይደርሳታል፡፡
በአዲሱ የቴሌኮም አዋጅ አንቀፅ 10 ንኡስ ቁጥር 4 መሰረት ማንም ሰው እያወቀም ሆነ በቸልተኝነት በኢንተርኔት የሚደረግን የስልክ ወይም የፋክስ ጥሪ ያደረገ ከሆነ ከ3 ወራት እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ቅጣት ይቀጣል፡፡
እንግዲህ ይህ ረቂቅ አዋጅ ከወጣ እህት አያንቱ ወደ ትምህርት ከመሄድ ይልቅ ወደ እስር ቤት መሄዷ እውን ይሆናል፡፡
እሱ እንዳለው ያ ሎሬቱ <>
– ዳርጌ ፌስቡክ ላይ ነው ውሎ አዳሩ፡፡ የሆነ ቀን ነሸጥ ሲያደርገው “አልሻባብ ድሬዳዋን ተቆጣጠረ ይሄም የጫትን ዋጋ ሊያንረው ይችላል” ብሎ ይለጥፋል:: በጉዳዩ የተደናገጡት ፌስቡካዊያን ጨኸታቸውን ያሰማሉ፡፡
በፀረ ሽብር ህጉ ማኝኛውንም የሽብር ድርጅት መደገፍ እንዲሁም ህዝብን ሊያሸብሩ የሚችሉ መረጃዎችን የለቀቀ አሁን ደግሞ በረቂቁ የቴሌኮም አዋጅ ማንኛውንም የቴሌኮሚኒኬሽን መሳሪያ ተጠቅሞ አሸባሪ መልዕክት ያስተላለፈ ሰው እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡
እንግዲህ ዳርጌም የዚሁ አንቀፅ ተሸላሚ ነው ማለት ነው፡፡ በርግጥ ዳርጌ “ፅሁፉን የፃፍኩት ጓደኞቼን አሰደንግጨ April the Fool ለማለት ነው” እንደሚል አይጠረጠርም፡፡
Thomas Hobbes ከመቃብር ቀና ብሎ ይሄን ቢመለከት የስነ መንግስት ትንታኔውን ያሻሽለው ይሆን ወይስ Sometimes, the state of nature can be the case even if there is a Law, since an unjust law is not a law at all” ይላል? እኛም መንግስት ከሕዝብ ኃይል ተቀናንሶ የተሰጠውን በትር አደራውን ሳይሆን ሌላ ነገር ሲጠብቅበት ባየን ጊዜ Is Rule by law a Rule of Law? ብለን እንጠይቃለን::
Generation “?”
ትውልድ ይሄዳል የሄደውን ለመተካት ደግሞ ሌላ ትውልድ የመጣል፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ማህተም አስቀምጦ በሌላ ይተካል፡፡ በምዕራቡ አለም በተለያየ ጊዜ የሚመጡ ትውልዶች የትወልዱን ባህርያት መሰረት በማድረግ የተለያየ የጊዜ ክፍፍል እና የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ፡
The Lost Generation ፡ ይሄ ትውልድ ከ19 ክፍለ ዘመን መጨረሻ እስከ አንደኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ የነበረው ሲሆን በጦርነቱ ማብቂያ ህልውናው ያከተመ ነው፡፡
The Silent Generation፡ ይህ ዝምተኛ ትውልድ ደግሞ የአንደኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀበት እስከ ታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት (The Great Depression) ድረስ የነበረው ሲሆን በአመዛኙ ድብታ የዋጠው ነበር፡፡
The Greatest Generation: ታላቁ ትውልድ የተሰኝው ደግሞ ታላቁን የኢኮኖሚ ድቀት ተቋቁሞ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተፈትኖ ያለፈው እና እንደ ብረት የጠነከረ የተባለው ነው፡፡
Generation X፡ ይህ ትውልድ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ የ1960ዋቹን አለማቀፍ የነፃነት፣ የአንድነት እንዲሁም የፀረ-ጦርነት ሰልፎች ሲያካሂድ የነበረ እና በባህል ለውጥ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው ትውልድ ነው፡
Generation Y or The Millennial Generation: የ Generation X ተከታይ ትውልድ ሲሆን በቴሌቪዥን እና በዲጅታል ሚዲያዎች ፍቅር የወደቀ እንዲሁም በሁሉም ነገር ለዘብተኛ ሊባል የሚችለው ትውልደ ነው፡፡
Generation Z፡ የDotcom Bubble ውጤት የWorld Wide Web ፍሬ እና ቀሰስተኛው ትውልድ ሲሆን ዘመኑም አሁን ነው ይላሉ፡፡
እነዚህን እና የመሳሰሉትን የትውልድ ተረኮች አሉ፡፡
ወደ ሀገር እኛ ሁኔታ ስንመጣ መሰረታዊ የሆነ የትውልድ ልዩነት፣ ጊዜ እንዲሁም ስያሜ አለ ማለት ባይቻልም በተለምዶ ‘ያ ትውልድ’ እየተባለ የሚጠራው እና የኢትየጵያን አብዮት የመራው እንዲሁም ከ ሶሻሊዝም ጋር በፍቅር ያበደው ትውልድ እንደ አንድ ትውልድ ይዘን ወደፊት እና ወደኋላ መሄድ እንችላለን፡፡ Read the rest of this entry
Generation “?”
ትውልድ ይሄዳል የሄደውን ለመተካት ደግሞ ሌላ ትውልድ የመጣል፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ማህተም አስቀምጦ በሌላ ይተካል፡፡ በምዕራቡ አለም በተለያየ ጊዜ የሚመጡ ትውልዶች የትወልዱን ባህርያት መሰረት በማድረግ የተለያየ የጊዜ ክፍፍል እና የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ፡
The Lost Generation ፡ ይሄ ትውልድ ከ19 ክፍለ ዘመን መጨረሻ እስከ አንደኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ የነበረው ሲሆን በጦርነቱ ማብቂያ ህልውናው ያከተመ ነው፡፡
The Silent Generation፡ ይህ ዝምተኛ ትውልድ ደግሞ የአንደኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀበት እስከ ታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት (The Great Depression) ድረስ የነበረው ሲሆን በአመዛኙ ድብታ የዋጠው ነበር፡፡
The Greatest Generation: ታላቁ ትውልድ የተሰኝው ደግሞ ታላቁን የኢኮኖሚ ድቀት ተቋቁሞ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተፈትኖ ያለፈው እና እንደ ብረት የጠነከረ የተባለው ነው፡፡
Generation X፡ ይህ ትውልድ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ የ1960ዋቹን አለማቀፍ የነፃነት፣ የአንድነት እንዲሁም የፀረ-ጦርነት ሰልፎች ሲያካሂድ የነበረ እና በባህል ለውጥ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው ትውልድ ነው፡
Generation Y or The Millennial Generation: የ Generation X ተከታይ ትውልድ ሲሆን በቴሌቪዥን እና በዲጅታል ሚዲያዎች ፍቅር የወደቀ እንዲሁም በሁሉም ነገር ለዘብተኛ ሊባል የሚችለው ትውልደ ነው፡፡
Generation Z፡ የDotcom Bubble ውጤት የWorld Wide Web ፍሬ እና ቀሰስተኛው ትውልድ ሲሆን ዘመኑም አሁን ነው ይላሉ፡፡
እነዚህን እና የመሳሰሉትን የትውልድ ተረኮች አሉ፡፡
ወደ ሀገር እኛ ሁኔታ ስንመጣ መሰረታዊ የሆነ የትውልድ ልዩነት፣ ጊዜ እንዲሁም ስያሜ አለ ማለት ባይቻልም በተለምዶ ‘ያ ትውልድ’ እየተባለ የሚጠራው እና የኢትየጵያን አብዮት የመራው እንዲሁም ከ ሶሻሊዝም ጋር በፍቅር ያበደው ትውልድ እንደ አንድ ትውልድ ይዘን ወደፊት እና ወደኋላ መሄድ እንችላለን፡፡
ከ ጣሊያን ወረራ እስከ ያትውልድን ድረስ ያለውን ዘመን ‘የነፃነት ትውልድ’ ልንለው እንችላለን ህይወቱ ሁሉ በወረራው ዘመን የተቃኝ በመሆኑ፡፡ ኑሮው ሁሉ የአርበኛ እና ባንዳ ፉክክርን ያስተናገደ እንደመሆኑ፡፡ እንግዲህ በምዕራቡ አለም Generation Yዎች የ Generation X ልጆች ናቸው ካልን በኛ ሁኔታ ደግሞ ያ ትውልድ የነፃነት ትውልድ ልጆች ናቸው ማለት እንችላለን፡፡
ችግር የሚሆነው የያ ትውልድን ጊዜ ማስቀመጥ አሁን ያለውንም ትውልድ ልዩነት ማወቁ ላይ ነው፡፡ ፖለቲካል ኢኮሚውን የያ ትውልድ አባላት እስከ አሁን እንደሚያሽከረክሩት መናገሩ የተራራ ላይ ሚስጥር ነው፡፡ እና የአሁኑ ዘመን ትውልድ መለያዎችስ ምን ይሆኑ? ነገሩ ጨዋታ እንደመሆኑ ቀጣዮቹ ምልልሶች እመልከት እስኪ፡
ሊሊ እና ጄሪ
ሊሊ፡ እኔ እምልሽ Justin ፀጉሩን ተቆረጠ የሚባለው እውነት ነው?
ጄሪ፡ No way, አያደርገውም ! ይሄ ለኛ ለአድናቂዎቸ ክብር አለመስጠት ነው፡፡ ከSelinaጋር ያለውን ግንኙነት ግልፅ አለመሆን ሲገርመኝ ብሎ ብሎ ደግሞ በምንወድለት ፀጉሩ መጣ? I swear, Online petition ካለ I will do that !
ሊሊ፡ Donation ነው አሉ የሰጠው፡፡
ጄሪ፡ ኡፍፍ የዚህን ሁሉ ድሃ ሆድ የሱ ፀጉር ይሞላ ይመስል፡፡ በእውነት Lil Wayneን የምወደው ለአድናቂዎቹ ባለው ክብር ነው! Never, Babyማ ይሄን አያደርግም፡፡
ዳኒ እና ጆኒ
ዳኒ፡ የ Balotelli አይነት የፀጉር ቁርጥ ፈልጌ እዛ እነ ሚኪ ፀጉር ቤትብሄድ ገገማ ብቻ ነው የሞላበት፡፡ አንዱም እንኳን አይችሉም፡፡
ጆኒ፡ እኔ እምለው Balotelli መልበሻ ክፍል ውስጥ የሆነ ነገር ሳያደርግ አልቀረም ስልጠና ላይ ብቻውን ነበር፡፡
ፊፊ እና ቲቲ
ፊፊ፡ የKaty Perry ፀጉር Human Hair መሆኑን ትናንት ሊዮና ነግራኝ ከምር Katyን ታዘብኳት፡፡
ቲቲ፡ እንጅ እኔም ግንባሯን Botox ተሰርታለች የመል ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ Otherwise, how on earth, her skin slimmed as lip?
ባቢ እና ጃክ
ባቢ፡ Rooney ባለፈው Surgery ካደረገ በኋላ አውሮፓ ዋንጫ ላይ ከBeckham ጋር ተቀራራቢ የፀጉር ቁርጥ መቆረጡን አየህ?
ጃክ፡ አዎ ቅድም Sky Sport ላይ አይቸዋለሁ፡፡ መጀመሪውኑ በድብቅ ሰርጀሪ የተሰራ ጊዜ ነውእሱን የታዘብኩት፡፡ እሽ ለማንም ሳይናገር አንደ ነገር ቢሆን የምንጎዳው እኛ አይደለንም?
ባቢ፡ እውነትሽን እኮ ነው ጃኮ፤ ግን ፈርጊ ያስተካክለዋል ብየ አስባለሁ፡፡ ሁልጊዜም በፈርጊ እምነት አለኝ፡፡
The Lost Generation or The EPRDF Generation?
የሁለት ‘ሚኒስትሮች’ ወግ
ወግን ‹‹ሥርዐት ደንብ ወይም የተደረገውን ታሪክ ማውጋት መተረክ ፣ ለሹሞች ለአለቃ ለቄስ ገበዝ የሚሰጥ ወይም የነፍስ አባት የሙት ልብስን አልጋን ዋንጫን መግፈፍ።›› ብሎ ከሳቴ ብረሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ይፈታዋል፡፡
እኛም ከዚህ ትርጉም ውስጥ ‹‹የተደረገውን ታሪክ ማውጋት መተረክ›› የሚለውን ተከትለን የሁለት መሪዎችን/ጠቅላዮችን ጨዋታ እንጨዋወታለን፡፡
Twitter በተባለው የማህበራዊ ድረ ገፅ አስከ ፈረንጆቹ 2012 ድረስ ከ 140 ሚሊየን በላይ ግለሰቦች ተመዝግበው ስለተለያዩ ጉዳዮች ሃሳባቸውን ያካፍላሉ በተከታዮቻቸውም (Followers) ምላሽ እና አስተያየት ያገኛሉ እነርሱም የፈለጉትን ሰው መከተል (Follow) ይችላሉ፡፡
ከነዚህ መራጆቸ (Twitterati) መካከልም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ @MelesZenawi እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ @HailemariamD እንደሚገኙበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰምተናል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ Twitterን የተቀላቀሉት ከ3 ዓመት በፊት ማለትም April 9/2009 እንደሆነ የTwitter ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በመጀመሪያ ያደረጉት Tweetም “Just had some of my favorite Shiro. Thank You Chef” የሚል ሲሆን፡፡ ይህችም Tweet በተለያዩ ግለሰቦችም ዘንድ የተለያየ አንድምታ የምትፈጥር ሆናለች፡፡ Read the rest of this entry