Category Archives: የአርብ ጫወታ

ሐዘን የሸሸገው ፈገግታ


ሐዘን አጥንት ሲደርስ ደግ አይደለም:: ሰውም እግዜሩም አይወዱትም:: ለአገርም አይጠቅምም ለጠላትም ደስ አይበለው:: እንዲህ አገር ነቅሎ ሙሾውን ሲያስነካው ተዉ እሚል ይጥፋ? ምስኪን ትዝ አለኝጃንሜዳ ጋር ሞቶ እሚቀብረው ሲያጣ አዝኖ ወደቤቱ የተመለሰው ሃሃሃሃ…:: ለማንኛውም ሕገ መንግስቱ እንደሚለው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲያርፍ ወይም በሞት ሲለይ አንድ ቀን ብሔራዊ ሃዘን ይታወጃል:: እንደ በረከት ስምኦን ቢሮ አሥራ አራት ቀን መሆኑ ነው:: [በየቀኑ የሚጣስን ሕገመንግስት አንስቶ መከራከሩ ፅንፈኛ ያስብለኛል ስለዚህ ይለፈኝ] በዛ ላይ ዋሽንት አለ [ለአንዳንዶች vuvusela ሆኖባቸዋል]:: ስለዚህም እንደ አንድ ሐዘናችንን ለማስረሳት እንደሚጥር ልማታዊ አፅናኝ በለቅሶው አካባቢ ከተሰሙት ንግግሮች ጀምሮ ወሬው እንዳመራን ውል አልባ ጨዋታ ብንጨዋወትስ
ሰሞኑን እንደ ጆሮ ስቃዩን ያየ (ሰደቃውን የበላ) የለምጆሮ ሆይ አድናቂህ ነኝ!
የልማታዊው በረንዳ አዳሪ አስተያየት፣አባታችንን ተማምነን ነው በረንዳ የምናድረውየሚለው አስገራሚ ለቅሶ የልማታዊውን እስረኛ ሰሜ ባላገሩን ቃለ ምልልስ ያስታውሰናል፤በመታሰሬ በጣም ደስተኛ ነኝ መንግስቴንም አመሰግነዋለውነበር ያለው ሰሜ ከእስር ቤት እንደወጣ [ሰሜ ሮሚዎን ሆኖ ትያትር እንደተጫወተ ላስታውስ]፡፡ ሰሜን ተንጠላጥለን ወደ ሁዋላ ስንሄድታንክ ተደግፎ መጽሐፍ ያነብ ነበርያለው የኢትዮፈርስት ዌብሳይት  አዘጋጅ ቤን፣ “HR 2003 ከማፅደቃቸው በፊት የአሜሪካን ሴናተሮች ጉዳዩን መላልሰው እንዲያዩት የመከሩት የብቸና ገበሬዎችየአሜሪካንን ኢምፔርያሊዝም ከተሳሳተ ርዕዮተዓለሙ እንዲታረም ያስጠነቀቁት የቦረና አርብቶ አደሮች” …

ለቅሶው የኪራይ ሰብሳቢዎች መጠቀሚያ እንዳይሆን የመከሩምትን ጨምሮእንግዲህ ዓለም ምን ይዋጣት!” ብለው ስለ አለማችን ያለቀሱም ነበሩ:: ዲሞክራሲውን በተደላደለ መሰረት ላይ ማስቀመጣቸውእንደ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች መሰዋታቸውንለዚህ ምስኪን ሕዝብ ሲሉ ፀጉራቸውን ተበጥረው፣ ቀበቶአቸውንም አስረው እንደማያውቁ ነግረው ክፉኛ አስደንግጠውናል:: ስለ ዴሞክራሲና ፍትህእኩልነት፣ምስክሮች ሰምተናል:: ነዋይምየሙሴን በትር የተቀበለሲል አቀነቀነ:: የዋልድባ ገዳም አባቶችምእናንተ ናችሁ መተተኞችተብለው መከራ አዩ ሲባልኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባትየሚልም መዝሙር ሰማንወይ ጆሮ:: ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያምም ከዋልድባአወልያና አበበ ገላው እንዲጠነቀቅ ምክር የለገሱ ብቅ አሉ:: የአባይ ግድብ በስማቸው እንዲሆን ወይንም አዲስ የብር ኖት በእርሳቸው ምስል እንዲታተም፣ ሐሳብ ያቀረቡና ጉዳዩን ሕዝባዊ ለማድረግ የሚሰሩም ታይተዋል:: የለቅሶ አይዶል ሊዘጋጅ እንደሚችልም ጭምጭምታ አለ::
አብዮታዊ ስያሜ ያላቸው ንግድ ቤቶችም ቁጥራቸው ጨምሯል፡፡
እነ “ጀግና አይሞትም ስጋ ቤት“፣ እነየስፎርሜሽን ዕቅዱ ይሳካል ሻይ ቤት“፣ እነ “ውሃ ማቆር ባርቤሪ“፣ እነ “አባይ ይገደባል ምግብ ቤት“፣ እነ “ቢፒ አር ልብስ ስፌት“፣ እነ “ባድሜ የኛ ናት የአልጀርሱ ስምምነት ውሳኔ ግን ተገቢ አይደለም ባልትና“፣ እነ “ሬነሳንስ ልማታዊ ቡና ቤት ለሐዘን ከሚሆን ጥሬና ጥብስ እና ከተከዘ አስተናጋጅ ጋር ተቀላቅሏል:: “ጣት እንቆርጣለንና በሊማሊሞ አቋርጡ ችርቻሮ መደብርሃሃሃሃ….
ስለ ደርግ ብዙ አላውቅም:: ትዝ እሚለኝሾላ እርግፍ እርግፍየሚባለው ጨዋታ ብቻ ነው:: እንግዲህ ዳርዳርታው ምነው አነሰ የሚል ክስ ከመጣ በሚል መሆኑ ነው:: ጎልማሶች እንደሚያወሩት ከሆነ ደርግን የሚስተካከል ያፈጠጡዉሃ የማያነሱና የጽሑፎቹ ቀለም ሳይደርቅ ዋጋ ቢስ የሚሆኑት መፈክሮችን ያህል ውሸት የባህሪው የሆነው ኢሕአዴግ እንኳን መፈብረክ አልቻለም::
ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደምተብሎ አብዮት ልጆችዋን በላችሲደመደምእንዲህም ተብሎ ሲገጠም
የሞተው ወንድምሽ
የገደለው ባልሽ
ሃዘንሽ ቅጥ አጣ
ከቤትሽም አልወጣ
ፖለቲካው ሴሰኛ ሲሆንባብዮት ግዜ የለም ትካዜእየተባለ ሲራገብበመጨረሻም በስሪያ ላይ ተጣበቀው ሰፈሩን የሚያሽኮረምሙትን ውሾች ቀጥቅጦ የሚያላቅ ወንድ ጠፍቶሁሉም ቤቱ መሽጎ!
በመሃልተፈጥሮን በቁጥጥር ስር እናውላለንየሚሉ መፈክሮች እስኪሰለቹ ሲለፈፉወይ ተፈጥሮ!!! ምን መስሎን ይሆን?!

ይህንን ያህል ከተጫወትን ይበቃናል:: ሐዘን ላይ ነሽና/ነህና ቀልደህ ሞተሃል ብንባል እንቀበላለን!

‘ተቃዋሚ’ ስንል

ሕይወት በአንድ ቦይ አትፈስም፡፡ ሕይወት ፍኖተ ብዙ ናት፡፡ አለምም በተቃርኖ የተሞላች ናት፡፡ ለእያንዳንዱ ጫላ ፣ ጫላቱ አለችው፤ ለእያንዳንዱ በለጠ ፣ በለጡ አለችው፡፡ ማህበራዊ ሕይወታችን፣ የፖለቲካው መንገድ፣ ኢኮኖሚያዊ ሀሳቡ ሁሉ በአማራጭ የተሞላ ነው፡፡ ስለ አይዲዎሎጂ ስታነሱ ካፒታሊዝም ወይስ ኮሚኒዝም ትባላላችው፣ ስለ ዕምነት ስታነሱ አንድ አምላክ ወይስ ብዙ ወይስ ምንም የሚል ሀሳብ ይነሳል፣ ስለ መብት ስታነሱ የግለሰብ መብት ወይስ የቡድን መብት ሲባል ትሰማላችሁ፡፡ ማለቂያ የለውም ተቃርኖው፡፡


ሕይወት ማለትም እነዚህን ተቃርኖዎች ስንመርጥ፣ ስንጥል፣ ስናሻሽል መኖር ነው፡፡

የፖለቲካ ተቃርኖ

ፖለቲካም ከዚህ የሕይወት ሕግ የተለየ መንገድ የለውም፡፡ ለምሳሌ አንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ፤  ሁለት ፖለቲከኞች አሉ እንበል ሁለቱም ሕዝቡ እንዲወዳቸው ጥረት ያደርጋሉ፡፡ አንዱ ለሕዝቡ ‹‹የህብረተሰቡ ዋነኛ ችግር የእንቅልፍ ማጣት ስለሆነ እኔን ከመረጣችሁ የምን መጨናነቅ ከውጭ ሀገር ለእያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ የስነ-ልቦና ባለሙያ  አስመጥቼ በመቅጠር የዕንቅልፍ ችግርን በ7 ቀናት ውስጥ አስወግዳለሁ›› እያለ ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ ሌላው በበኩሉ ‹‹የከተማዋ ህብረተሰብ እንቅልፍ አጥቶ መሰቃየቱ የኔ የእናንተ መልካም አገልጋይም ስቃይ ነው፡፡ እኔን የመረጣችሁ ጊዜ ግን መለኮታዊ ሀይል ከእንቅልፍ እጦት እንደሚገላግላችሁ አትጠራጠሩ›› እያለ ለምርጫው ሊተጋ ይችላል፡፡ ለእንቅልፍ እጦቱ የቀረቡት መፍትሄዎች የተለያዩ መሆናቸው ህዝቡ አማራጭ እንዲያገኝ እና ያመነበትን እንዲመርጥ ያስችሉታል፡፡ 

በነገራችን ላይ በከተማዋ ውስጥ ያለው የእንቅልፍ እጦት ችግር ዋነኛ መነሻ ከተማዋ ውስጥ የተተከለ ትልቅ የቆዳ ፋብሪካ የሚያወጣው ድምፅ ሊሆንም ይችላል፡፡ ፖለቲከኞቹም ይሄን ችግር ሊስቱት ይችላሉ፡፡ ዋነኛው የሕዝቡ ስቃይም ችግሩን የሚረዳለት ሰው ሲያጣ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ

ኢትዮጵያ  ውስጥ የፓርቲ ፖለቲካ ከተጀመረ ገና 50 ዓመት እንኳን አልሞላውም፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ምን አበርክተዋል የሚለው እጅግ ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ ነገር ነው፡፡

የንጉሳዊ ስርዓቱ በመውደቂያው ዋዜማ ብቅ፣ ብቅ ያሉት ፖለቲካ ፓርቲዎች ንጉሱ እንደ ወደቁ ወደ ስልጣን መንበሩ ቀረብ ቀረብ ማለት ጀመሩ፡፡ ያሳዝናል! በመጀመሪያ ሁሉም ግራ ዘመም ፓርቲዎች ብቻ ነበሩ፡፡ ሲከተልም ለህዝቡ ያቀረቡለት ሀሳብም ‹‹እኔ ከእርሱ የበለጠ ግራ ዘመም ነኝ›› እያሉ ለህዝቡ እንግዳ የሆኑትን እነ ማርክስን ካላመለክ፣ እነ ሌኒንን ካላወደስ አንተማ ኢምፔሪያሊስት ነህ እየተባባሉ አንድ ሁለት ያሉት ፓርቲዎች ፍፃሜያቸው አሳዛኝ ሆኖ አለፈ፡፡ አሸናፊው ቡድንም ሀገሪቱን በመሳሪያ አስተዳድራለሁ ብሎ ታገለ፡፡ ብሎ፣ ብሎ ግን እሱም  ወደቀ፡፡  

ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ ጋር ተያይዞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ መፍቀዱ ከስኬቶቹ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ነው፡፡ ይሄንም ተከትሎ በዛ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ መድረኩ ብቅ፣ ብቅ አሉ፡፡    
ተቃዋሚው ከየት ወደየት

ዲሞክራሲና ዲሞክራሲያዊነት በምስራቅ/ምእራብ ክፍፍል ማግስት ሶስተኛው ማዕበል (The Third Wave) ተብሎ ብቅ ካለ በኋላ የፓርቲ ፖለቲካ የዲሞክራሲው ማሳያ ተደርጎ ለህዝቡ እንዲቀርብ አስችሏል፡፡ ኢህአዴግም የዚህ የታሪክ አካል በመሆን የተቃውሞ ፖለቲካን የዲሞክራሲው መገለጫ እንዲሆን ከፈቀደ በኋላ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በየሰፈሩ ብቅ፣ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ገና ከመጀመሪያው ኢህአዴግን ሊቀናቀን ይችላል የተባለው ኦነግ አልቻልኩም ብሎ፡

‹‹እልም ያለው ጫካ፣ እልም ያለው ዱር፣
ሲነጋገር ያድራል ከመውዜሩ ጋር፡፡››

እያለ ጫካ ገባ፡፡

ከዛ በመቀጠል አንዳንድ በተለይም ዘውግ ተኮር ፓርቲዎች ብቅ፣ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ የዘውግ ተኮር ፓርቲዎች ወደ ፖለቲካው መምጣታቸው ያስደነገጣቸው ግለሰቦች ‹‹የቅይጥ ብሄር ብሄረሰቦች ፓርቲ›› ብለው ፓርቲ እስከ መመስረት ደርሰዋል፡፡ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የስልጣን ሽኩቻው አልለቃቸው ብሎ ግንባር ሲፈጥሩ እና በግንባራቸው ሲደፉ ሁለት ሀገር አቀፍ ምርጫዎች አለፉ፡፡

ሶስተኛው ሀገረ አቀፍ ምርጫ ግን የተቃማዊውን ጎራ በተለየ መሰረት ላይ አስቀመጠው፡፡ የህዝቡን አመኔታም አስገኙ በምርጫውም አስገራሚ ድል አገኙ፡፡ ምርጫውን እንዳሸነፍ ተናገሩ፣ ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ግን ‹‹ከበፊቱ የተሻለ ድል አምጥታችኋል፣ ነገር ግን ያሸነፍኩት እኔ ነኝ›› ብሎ ድል አወጀ አለማቀፍ ታዛቢዎችም ምርጫው አለምአቀፍ መለኪያዎችን ያላሟላ ነው አሉ፡፡

ከዛም ለትንሽ ጊዜ ብልጭ ያለው ጠንካራ የተቃውሞ ሀይል እያነሰ፣እያነሰ መጥቶ አሁን ሞተ ሊባል ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡
ለመሆኑ የተቃውሞ ሀይሉ አሁን ላይ ሆኖ ምን አላማ ይዟል?ቁርጠኝነቱስ? መጨረሻውስ ምን ይሆን? አንዳንድ አመላካቾችን አንመልከት እስኪ፡፡

የተቃውሞው አላማ

አንዳንዱ የተቃዋሚ ሀይል ተቃውሞውን የሚጀምረው ‘ተቃዋሚ’ ልንባል አይገባም በማለት ‘ተቀናቃኝ’ በሉን በሚል ጥያቄ ነው፡፡ ‹‹ተቃዋሚ ማለት ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲን ፖሊሲዎች በመቃወም ለመተካት እራሱን የሚያዘጋጅ ማለት ነው በሌላ ሀገርም በተመሳሳይ ነው Opposition Party ነው የሚባለው›› ሲባል የለም ስሜን ቀይሩ አጀንዳ አንድ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

ሲቀጥል አብዛኛው ፖለቲካ ፓርቲ አላማ አንድን የተወሰነ ሕዝብ ብቻ በመወከል መነሳቱ እይታውን ከመንደር ውስጥ የስልጣን ፍላጎት በላይ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ጥርሰ ፍንጭት* ሰዎች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢጥፍሰዲድ) ተቋቋመ እንበል፡፡ እንግዲህ ዋነኛ አላማው ጥርሰ ፍንጭት ሰዎችን በጥርሳቸው እንደ ፈለጉ እንዲስቁበት ለማድረግ ሊሆን ነው፡፡ እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ በመጀመሪያ ጥርሰ ፍጭት ሰዎች እንደፈለጉ እንዳይስቁ  የመብት ክልከላ አለ ወይ? የሚል ሲሆን በማስከተልም የመብት ጥሰቱስ ካለ የጥርሰ ፍንጭት ሰዎችን መብት ብቻ ለማስከበር መነሳት እና ተሳክቶለት በጥርሳቸው እንደ ፈለጉ እንዲሆኑ ቢያደርግ መብቸው ሙሉ ሊሆን ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄንም መመለስ የሚችል አይመስልም ይህ ‘የአንድ ወንዝ ፓርቲ’፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ በይፋ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱት ፓርቲዎች 76 እንደሆኑ የቦርዱ ዌብሳይት ያመለክታል ከነዚህ ውስጥ ከ53 የሚሆኑት ለአንድ ዘውግ (በተለምዶ ብሄር) መብት መከበር የሚታገሉ ሲሆኑ፤ ይሄም ከላይ ያነሳናቸው ጥያቄዎች በወሳኝነት መላሽ እንደሚስፈልጋቸው ያስገነዝበናል፡፡

ሌላው ከአላማቸው ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ግልፅ አላማ ያለው ፓርቲ ስንት ነው? ብለን ስንጠይቅ ነው፡፡ በምርጫ 2002 በአስገራሚ ሁኔታ  ‹‹ፖሊሲ የለንም፣ ፖሊሲ የምንቀርፀው የኢትዮጵያ ህዝብ ከመረጠን በኋላ ከህዝቡ ጋር አብረን መክረን ነው፡፡›› የሚል ‘ፓርቲ’ ህዝቡን ‘ነፃ’ ለማውጣት እንደተሰለፈ አይተናል፡፡ ለመሆኑ ስንቱ ፓርቲ ነው አላማ ቀርፆ ህዝቡን አላማየን አይታችሁ ምረጡኝ የሚለው? ቢሮውን መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አድርጎ አባላትን በዘመድ አዝማድ እየመለመለ ህዝብን እመራላው፣ እኔ ነኝ ትክክለኛ አማራጭ ቢል ህዝቡስ ምን አይቶ ይቅረበው? ለነገሩ ይሄስ ቢሆን የምርጫ ሰሞን ግርግር አይደል?
ለመሆኑ 31,869 ለሚሆነው የሀረሪ ሕዝብ 3 የተለያዩ ፓርቲዎች እኔ እሻልኻለው ብለው ሲቀርቡለት ምን አይነት የአላማ ልዩነት ይዘው ነው? ነው ዙፋን ጉዳዩ ነው ? እንድንል ያደርገናል፡፡

ቁርጠኝነት

ከላይ እንደ አየነው የአላማ አለመኖር፣ መደብዘዝ ወይም መጥበብ የተቃዋሚው ጎራ የመጀመሪያው ፈተና ነው፡፡ እሽ አላማው እንዳለ ሆኖ ፓርቲዎች ያስቀመጡትን አላማ ለማስፈፀም ምን ያክል መሰጠቱ (Submission) አላቸው? የሚለው ደግሞ ሌላው ጥያቄ ነው፡፡ ከላይ ያነሳነውን ምሳሌ እዚህም እናምጣው፡፡ የኢትዮጵያ ጥርሰ ፍንጭት ሰዎች  ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢጥፍሰዲድ) የተቋቋመለት አላማ ጥርሰ ፍንጭቱ ህዝብ በጥርሱ እንደፈለ እንዲሆን ማድረግ ነው እንበል፡፡ ፓርቲው ምን ያክል ከጥርሰ ፍንጭቱ የህብረተሰብ ክፍል ጋር አብሮ እየሰራ ነው? ለአላማውስ እስከ ምን ድረስ ነው የሚታገለው? ‹‹እኔ ድራፍት እየጠጣው ነው መታገል የምፈልገው›› እያለ ለሚታገልልት አላማ ሲል ከብርሌ አንገት እንኳን መራቅ የማይፈልግ ነው ወይስ እስከ ከርቸሌ ለመሄድ የወሰነ ነው?  በምንዳ ተታሎ የጥርሰ ፍጭቱን ሕዝብ መብት ይሸጣል ወይስ በአቋሙ ይፀናል? እነዚህ ጥያቄዎች ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ካሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በየጊዜው የምንሰማቸው ዋነኛ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ዲሞክራሲ ሲሉ

የኢትየጵያ ምርጫ ቦርድ በአሁኑ ወቅት በመዝገቡ ውስጥ ካካተታቸው 76 ፓርቲዎች ውስጥ 55ቱ ‘ዲሞክራሲያዊ’ ወይም ‘ዲሞክራቲክ’ የሚል ቅፅል በስያሜያቸው ውስጥ አካተዋል፡፡ ለምሳሌ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ፣ የጠምባሮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ  ሕብረት፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ፣ የደንጣ፣ ዱባሞ ክንችችላ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ  ድርጅት፣የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ  ንቅናቄ፣ የሲዳማ ሀዲቾ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ  ድርጅት እያለ ዝርዝሩ  ይቀጥላል፡፡ ለመሆኑ ስንቶቹ ፓርቲዎች ናቸው እንደ ስማቸው ዲሞክራሲያዊ የሆኑት? ውስጠ ዲሞክራሲ (Democratic Centralism) በስንቶቹ ፓርቲዎች ውስጥ አለ? ከተመሰረተ አስራ ምናምን አመት የሆነው ‘ዲሞክራሲያዊ’ ፓርቲ እንዴት አንዴ እንኳን የድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አይጠራም?
እንዴት አንድ የፓርቲ መሪ ራሱ ገንዘብ ሰብሳቢ፣ ራሱ ገንዘብ ያዥ፣ ራሱ ኦዲተር፣ ራሱ የፓርቲው አመታዊ ሪፖርት አዘጋጅ እና አፅዳቂ ይሆናል? ምን አይነትስ ‘ዲሞክራሲ’ ለማምጣት ነው የሚታገለው?

የፓርቲ አባላት ‹‹ይሄ ነገር መልካም አይደለም ስለዚህ እንዲህ ይደረግ ሲሉ›› ከመንግስት ጋር ወግናችኋል፣ የስልጣን ጥመኞች ናችሁ፣ አድማ በፓርተው ውስጥ ለመምታት አቅዳችኋል እያሉ ማውገዝ እና ከፓርቲው  ማባረር የተቃውሞው ጎራ ልማዳዊ ተግባር ሆኗል፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች ከነ መሪ ግለሰቦቻቸው ነገ ስልጣን ቢይዝ የሚያመጡት ዲሞክራሲያዊ ለውጥስ ምን አይነት ይሆን? አዎ፤ ፈተናው ብዙ ነው፡፡

ለመሆኑ የተቃውሞውን ሀይል እንዲህ በሞት አፋፍ ላይ ያስቀመጠው ማን ነው? ወደፊትስ ምንድን ነው መደረግ ያለበት? የሚለውን ለማየት በቀጣይ ፅሁፍ እንመለስበታለን፡፡

·       *  ፍንጭት ማለት የፊት ጥርሱ ክፍት  የኾነ ማለት ነው።

ባልቻን ፍለጋ

የመድፍ አረር አካባቢውን አጥኖታል፣ ጎራዴ ይብለጨለጫል፣ የደም ወንዝ ይጎርፋል፡፡ አዎ ይህ ጥቁር ጦር ቀላል  እንዳልሆነ እየታየ ነው፡፡ ያ የበጋ ሰማይ ደምን አየ መሰለኝ ክፉኛ ቀልቷል፡፡ በቀላ ሰማይ ስር ጦርን እንደ ብዕር ደምን እንደ ቀለም አድርገው ጀግኖች ታሪክ ይፅፋሉ፡፡ ታሪክን በመክተቡ መሀል ለጥቁሮቹ ጀግኖች አንድ አስደንጋጭ ነገር አጋጠማቸው፡፡ ከመሪዎቻቸው ንዱ የሆኑት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ  ፊትአውራሪ ገበየሁ ተሰው፡፡ ወላድ በድባብ ትሂድ ገበየሁን ያጣ ጦር አልተበተነም ባልቻን የሚያክል መሪ አግኝቷልና፡፡ ደጃዝማች ባልቻም መድፉን እንደ ቀላል ያገላብጠው ጀመር፡፡ ይሄን የታዘበ አዝማሪም፡

 <<ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ፣

መድፍ አገላባጭ፣ ብቻ ለብቻ፡፡>>

ብሎ ተቀ፡፡ ምስጋና ለባልቻ፣ ምስጋና ለገበየሁ ያ ጥቁር ጦር ጠላቱን ድል ነሳ፣ አዲስ ታሪክም ፃፈ፡፡ የካቲት 23/1888 ዓ.ም አድዋ ኢትዮጵያ፡፡
ዛሬ ገበየሁ
አዎ እነ ገበየሁ እነ ባልቻ ታሪክ ከጻፉ ድፍን አንድ ምእተ ዓመት ሊሞላቸው 5 ዓመታት ብቻ ነው የቀረው ወቅቱም 1983 ዓ.ም ውልደቱ በታሪካዊዋ አድዋ የሆነ፣ ራሰ በሀ፣ ቀጭን-አጭር መሪ ነገሰ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድር፡፡ የቀድሞው ፕሬዘደንት ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፡፡ መለስ እንደ ገበየሁ ከፊት ሆነው ህዝቡን ወደ ድል  ወይስ ወደ ገደል መሩት? ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ መልሶች ናቸው የሚሰጡት፡፡
ባንድ ወገን ‹‹ነፃነትን ያለገደብ ሰጠ፣  ድንቅ እና ውብ ህገ-መንግስት ለህዝቡ አስረከበ፣ ሀገሪቱን በልማት ጎዳና ትጓዝ ዘንድ አረር በማይሸትበት፣ጎራዴ በማይብለጨለችበት የልማት መንገድ መርተዋታል፣ ማን እንደ እርሳቸው? ማን እንደ መለስ?›› በማለት ‹‹ወዲ ወሊደሙ መለስ በልዩ›› (ልጅ ወልደሽ ስሙን መለስ በይው)  እያለ መለስ ለህዝቡ ከመሪም በላይ ናቸውን ሲሰበክ፣ ‹‹ይቀጥል ሊቁ ሰው ጥበብ የተካነው›› እያለ ንጉስ ሆይ ሽህ ዓመት ይንገሱ፣ ዙፋንዎት ይፅና፣ አመራርዎት ይቅና  ይዘምራል፡፡
በሌላ ወገን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በማይወዳት መሪ እየተመራች ነው፣ ‘ባንዲራን ጨርቅ’ ያለ የቅርስን ዋጋ ያሳነሰ፣ ‘ኮሮጆ የሚያስገለብጥ’፣ ህግ ደንታ የማይሰጠው ህግ ሰሪ ህግ አፈራሽ በአጠቃላይ ምሉዕ በኩሉሄ የሆነ መሪ ከቶ ለምኔ? እርሱ ወረደ እለት ስለቴን አስገባለሁ፣ እሱ የሞተ እለት ፈጣሪ የህዝቡን እንባ አይቷል ማለት ነው እያለ ይተቻል፡፡
አዎ ! ዛሬ ‘ገበየሁ’ ፈተናቸው ብዙ ነው፡፡ አዎ ! ዛሬ ‘ገበየሁ’ ‘ጠላትን’ ለመዋጋት ጦር ሜዳ መሄድ አላስፈለጋቸውም ያሉበት ቦታ ድረስ ይሰማቸዋል የመድፍ ጩኸት፣አይናቸው ላይ ያብረቀርቃል የጎራዴው ስለት፣ በዓይነ ህሊናቸው ይታያቸዋል ደም የቀደደው ቦይ ፡፡ በርግጥ ‘ገበየሁ’ ዛሬ ግለሰብ ብቻ ሳይሆኑ ስርዓትም ናቸው ቢባል አያሰገርምም፡፡ በርግጥም መድፉን ብቻቸውን አገላብጠውታል፡፡ 
የሆነ ሆኖ በአሁኑ ወቅትም ‘ገበየሁ’ የት እንዳሉ በትክክል ማወቅ አልተቻለም፡፡ ጓዶቻቸው ‹‹ሥራ ጫና ነበረባቸው አሁን እያረፉ ነው›› ሲሉ ህዝቡ ‹‹ድሮስ ብቻቸውን ህዝብን የሚያክል ነገር እያገላበጡ ምነው አይደክሙ?›› ይላል፡፡ እንዲሁም የ አለፉ ዘመናትን ሲያስታውስ፡
ደከመኝ ሰለቸኝ፣ እረፍት የማያውቀው፣

አብዮታዊ መሪ፣ ጓድ መንግስቱ ነው፡፡

ተብሎ  ለመንግስቱ-ኮመኒስቱ የተዘመረውን መዝሙር ይታወሰዋል፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ‹‹አይ ‘ገበየሁ’ ለዘላለሙ አሸልበዋል የስልጣን ሽኩቻውም በበታቾቻቸው መካከል ጡፏል›› የሚል መረጃ ይሰማል፡፡
የትኛው መረጃ እንደሚጨበት ማወቅ አልተቻለም፡፡ ለማንኛውም ጨዋታችን እንዲሞቅ እንዲህ እናስብ፡፡ ከእንግዲህ ‘ገበየሁ’ በህወይት ኖሩም አልኖሩም ወደስልጣን አይመለሱም ስለዚህም የገበየሁን ተኪ ‘ባልቻን’ እንፈልግ፡፡
‘ባልቻን’ ፍለጋ  
‘ገበየሁን’ ይተካ ዘንድ ‘ባልቻን’ እንፈልጋለን፡፡ መጀመሪያ ‘ባልቻ’ ሊኖርባቸው የሚችሉትን ቦታዎች እናስስ እስኪ፡፡
1.      – ‘በመስዋዕትነት ከተገኘው ህገ መንግስት’

ከሌሎች ሀገሮች ህገ መንግስቶች በተለየ የኢፌድሪ ህገ-መንግስት ገበየሁ ቢሞት የባልቻ መገኛ የት እንደሆነ በግልፅ አይጠቁምም፡፡ ይልቅስ ህገ መንግስቱ ገበየሁ ‹በማይኖር ጊዜ› በሚል ጥቅል አጠራር ምክትሉ ‘የባልቻን’ ድርሻ ይወርሳል ይላል፡፡ ይህ ህገመንግስታዊ አንቀፅ ለትርጉም ክፍት ነው፡፡ ‘ገበየሁ’ ከስራ ለአጭር ጊዜ ሲርቅ ነው ብቻ ነው ተብሎ ሊተረጎምም ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አይ ‘ገበየሁ’ በሞተም ጊዜ ተክቶ ሊሰራ ይችላል ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ እንግዲህ ‘ባልቻን’ ከህጋዊ መስመር አገኘን የሚሉም ከሁለተኛው ትርጉም የተነሳ መሆን አለባቸው፡፡ አሁን ካለው ድባብ በመነሳት ይህ  የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ይመስላል፡፡ ቢሆን እንኳን እንደ ‘ገበየሁ’ ህዝቡን ብቻውን ማገላበጡ ያጠራጥራል፡፡  

2.     – ‘ጀኔራል ባልቻ’

እነሆ ‘ባልቻን’ ፍለጋ የጦር ካምፕ ውስጥ ነን ‘ባልቻን’ በግልፅ ለማየት ግን አልተቻለም፡፡ በርግጥም ‘ባልቻን’ ከጦር ካምፕ የምናገኝው ከሆነ ግን ጉዳዩ ያስፈራል፡፡ ቢያስፈራም ግን ‘ባልቻ’ በጦር ካምፕ ውስጥ መሽጎ ሊሆን ይችላል፡፡ የተገኝ እለት ‘ጀኔራል ባልቻ’ ሀገሪቱን በአንድ እግሯ አቆሟት መባሉ የማይቀር ነው፡፡

3.     ‘ባልቻን’ ከቤተ መንግስት
 
ሌላው ጥርጣሬያችን ‘ባልቻን’ እዛው ‘የገበየሁ’ ቤተ-መንግስት ውስጥ ልናገኛቸው እንችላለን የሚለው ነው፡፡ አይሆንም አይባልም፡፡ ሴቱ-ወንዱ የቤተ መንግስት ባለሟል ድንገት ‹‹ባልቻ ነኝ እኮ ስለምን ርቃችሁ ትፈልጉኛላችሁ እዚሁ ቤተመንግስት ነበርኩ እኮ›› ሊል ይችላል፡፡ ‹‹ሹመት በተርታ፣ ስጋ በገበታ››ን እየተረተ ‹‹የሞትንም እኛ ያለንም እኛን›› እያለ ሊያሳውጅ ይችላል ‘ባልቻ’ ከቤተ መንግስት፡፡

4.     ባልቻን’ ከምድረበዳ

በርግጥም ‘ባልቻን’ ከምድረበዳ ያልነው ‘ከተቃዋሚው’ ጎራ ይመጣ ይሆን የሚለውን ግምታችን ነው፡፡ ዲያስፖራ ተቃዋሚው መግለጫ፣ ኮምኒኬ ወ.ዘ.ተ በማውጣት ዱብ ዱብ እያለ እራሱን እያሟሟቀ ይገኛል፡፡ መቸም ‘ባልቻ’ ‘አትላንቲክን’ ወይም ‘ሚድትራኒያንን’ አለዚያም ‘መረብ’ ወንዝን አቋርጦ ሊመጣ ይችላል ማለት ከባድ ነው! ኧረ በጣም ከባድ ነው፡፡ በሌላ ጎኑ ሀገር ውስጥ ያለውን ተቃዋሚ ስናይ አሁን ባለበት ሁኔታ ጀኔራሎቹ፣ ይሆኑ ወይስ ከቤተ መንግስት እያለ ከመገመት ውጭ ያው በምድረበዳ እየተንከራተተ ነው፡፡ እናም አንድ ነገር ላይ እርግጠኛ መሆን እንችላለን አዎ ‘ባልቻን’ በድረ በዳ መፈለግ ከንቱ ልፋት ነው፡፡

የሆነ ሆኖ ‘የገበየሁ’ ዘመን እያለቀ ይመስላል፡፡ ‘የባልቻን’ መምጫ ግን ማወቅ አልተቻለም፡፡ ቢመጣስ እንደ ‘ገበየሁ’ ብቻውን ህዝቡን ያገላብጠዋል የሚለውም ሌላ ጥያቄ ነው፡፡

ስለምንስ ከምሁራን መካከል ትፈልጉኛላችሁ? !

የትምህርት ጉዞው የተጠናቀቀ ይመስላል፡፡ ተማሪዎች በምረቃ ቀን የሚለብሱት ጋወን ፣ አስመራቂ ቤተሰቦቻቸው ወደ ምረቃው ቦታ የሚገቡበት የመግቢያ ትኬት ከየትምህርት ክፍላቸው እየወሰዱ ነው፡፡ አንድ ከዚህ በፊት ያልተለመደ ተግባር ግን ይቀራል፡፡ የአንድ ሙሉ ቀን ስልጠና፡፡ ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት በመጡ ባለሙያዎች ከምረቃ በኋላ ሊሰማሩባቸው ስለሚችሉባቸው የስራ አይነቶች፡፡

ገነትም ከነዚህ ሰልጣኞች መካከል አንዷ ስትሆን በ3 አመት የዩንቨርስቲ ቆይታዋ Applied Biology ያጠናች ስትሆን ከተቻለ አንድ ፋርማሲ ሰራተኛ ውስጥ አለዚም መምህር እሆናለው የሚል ህልም ነበራት፡፡ በስልጠናው የሰማችው የስራ መስክ ግን አልተዋጠላትም፡፡ ተደራጅቶ የባልትና ውጤቶችን መሸጥ፣ የከተማ ግብርና ላይ መሰማራት፣ የኮብል ስቶን ማንጠፍ ስራ፣ፓርኪንግ ወ.ዘ.ተ፡፡

ይህ በ2004 ዓ.ም ተማሪዎቻቸውን ያስመረቁ የሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች እና ተማሪዎች ሰሞነኛ ቆይታ ነው፡፡

ትምህርት

የሰው ልጅ ሁሉን ያውቅ ዘንድ አይቻለውም ስለዚህም ስለ ክዋክብቱ መረዳቱ የበዛለት ላላወቀው እሱም ስለ ስነ ተዋልዶ እውቀቱ ከሌለው ከአዋቂው የሚቀስምበት ስርዓት ነው ትምህርት፡፡ አንድ ሰው አቃቂ ምሁር ይባል ዘንድ በሁሉም የትምህርት ዘርፎች የዕውቀት ላቂያ ይኑረው ያኔም አዋቂ ይባላል ይለናል የRenaissance Man Theory፡፡ ለዛም ይመስላል በአብርሆት ዘመን (15-18 Century) የነበሩ ምሁራን ሁሉን አቀፍ እውቀት ነበራቸው ልንል የምንችለው፡፡ የፍልስፍና፣ የሂሳብ፣ የስነ-ክዋክብት፣ የስነ-ሰብ ወ.ዘ.ተ እውቀቶችን አንድ ምሁር አቅፎ ሊይዝ ይችል ነበር፡፡

ይሄ ትክክል አይደለም ይልቅስ በህብረተሰቡ ውስጥ እምርታ ይመጣ ዘንድ የስራ ክፍፍል (Division of Labor) ወሳኝ ነው ብሎ ስኮትላንዳዊው የስነ-ምጣኔ ምሁር አዳም ስሚዝ የሀሳብ ሽግግር ካደረገ ወዲህ፡፡ እያንዳንዱ ህብረተሰቡ አካል አንድ የስራ መስክ ላይ በተለየ(Specialize) አድርጎ ጥናት ካደረገ እና ከተማረ በዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያመጣል በሚል የትምህርት ስርዓቶቹም በዚህ ሀሳብ መቀረፅ ጀመሩ፡፡ ባጫ ምህንድስና ፣ አበበ ህግ ፣ አይዳ እርሻ ወ.ዘ.ተ እየተማሩ በያዙት ሙያ ላቂያን ማሳት ይችላሉ የሚለው የ Specialization Theory አሁን ድረስ በትምህርቱ ዘርፍ ተግባራዊ እየሆነ ነው፡፡

ሱፍ ለባሽ ምሁር

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ታሪክ መቶ አመት እንኳን አልደፈነም ፡፡ የመጀመሪያው ዘመናዊ የመንግስት ትምህርት ቤት በ1908 ነው የተቋቋመው እስከ ጣልያን ወረራም ብዙ ተማሪዎችን ማስተማር አልተቻለም በአብዛኛውም ከውጭ ተምረው የመጡ ኢትዮጵያዊያን ነበሩ እንደ ምሁር የሚቆጠሩት፡፡ ከነዚህ በውጭ ተምረው የመጡ 120 ተማሪዎች ውስጥ ጣልያን በተለምዶ የሚያዚያ 28ቱ ጭፍጨፋ ተብሎ በሚጠራው ድርጊት 75 በመቶዎቹን እንደ ገደላቸው የመንግስትን ሪፖርት ጠቅሰው Mrgery Perham, The Government of Ethiopia ባሉት መፅ ሃፋቸው ያስረዳሉ፡፡

እንግዲህ በጣሊያን ወረራ 75 በመቶ የተማረ ሀይሏን (በነገራችን ላይ የተማረው ሀይል 75 በመቶ ማለት 90 ምሁራን ብቻ ማለት ነው) ካጣች በኋላ እስከ ንጉሱ የስልጣን ዘመን ማክተሚያ ድረስ የተማሪዎች ቁጥር (በውጭም በሀገር ውስጥም ተምረው የመጡት) በብዙ እጥፍ ጨምሯል፡፡

  • አለ ከተባለ የፈረንሳይ ህግ ትምህርት ቤት ህግ ተምሮ የሀረርጌ አውራጃ አስተዳዳሪ የእልፍኝ አሽከር፣
  • Literature 4 ዓመት ሙሉ እነ ሸክስፒርን፣ እነ ሞንታኝን፣ እነ ዳንቴን እንዲያም ሲል እነ ቶልስቶይን ሲያጠና ከርሞ በንግድ ሚኒስቴር የወርሃዊ የዋጋ ጥናት ባለሙያ መሆን፣
  • የምጣኔ ሀብት ትምህርትን እንደ ውሃ ጨልጦ በበጌምድር አውራጃ የደምቢያ ወረዳ የመንግስት ሹም ወ.ዘ.ተ እየሆኑ ነበር እነዚህ እውቀትን እና አለባበስን ከአውሮፓ የቀዱ ምሁራን ወደ ስራ አለም የሚሰማሩት ፡፡

በርግጥ አቢዮተኛ ው ያ ትውልድም የዚህ ሱፍ ለባሽ ምሁር አካል ነበር፡፡

የተማረ ሁሉ ያስተምር

ደርጉ መጣ ሁሉንም ነገር ወደ ጦር ግንባር ከማለቱ በፊት የትምህርት ዘመቻ ጀመረ ‘ማሃይምነት አይነስውርነት‘ ነው በሚል የሚያሸማቅቅ መፈክር የገጠሩን ህዝብ ስሙን ይፅፍ ዘንድ ፊርማ በእርሳስ ይፈርም ዘንድ አስቻለው፡፡ ነገር ግን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚወጡ ተማሪወች የተማሩትን ትምህርት የት አደረሱት ከተባለ፡፡ ግማሾቹ አቢዮት ጠባቂ፣ ግማሾቹ የቀበሌ ሹም ፣ ወታደር ቤትም የገቡ አሉ፡፡

ይልቁንም ደርጉ ተማሪዎችን ከነ ኢህአፓ ጋር ‘ንክኪ’ አላቸው በሚል በጥርጣሬ ነበር የሚመለከታቸው፡፡ ይባስ ብሎም ከሀገር በፊት የምን ትምህርት ብሎ በተለምዶ ‘ምሁሩ ጦር’ የሚባለውን ወታደር ከዩንቨርስቲ አፍሶ ብላቴ ጦር ማሰልጠኛ ከተተ፡፡ የተማሩት ትምህርትም አላማው ጠፋባቸው ለነዚህ ምሁር ወታደሮች፡፡

ስለምንስ ከምሁራን መካከል ትፈልጉኛላችሁ? !

ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ከሰራቸው አመርቂ ስራዎች አንዱ ትምህርትን በነፃ ተደራሽ ለማድረግ ያደረገው ጥረት እና ያም ያመጣው ውጤት ነው፡፡ አጠቃለይ የትምህርት ፖሊሲ በ1986 ዓ. ም ከወጣ በኋላ ብዙ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተሰርተዋል፣ የትምህርት ቤቶች የቅበላ አቅም በብዙ እጥፍ ጨምሯል፣ ከ30 በላይ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ተገንብተዋል፡፡

ነገር ግን የትምህርት ፖሊሲውን ሁለት ዋነኛ ተግዳሮቶች አንቀው ይዘውታል፡፡

1. የትምህርት ጥራት ጉዳይ፡

መንግስትም እንደሚለው ዋነኛው የትምህርት ፖሊሲያችን ፈተና የጥራት መጓደል ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ:

  • ዩንቨርስቲ የChemistry ምሩቅ ተማሪዎች Chemistryን Khemistry እያሉ እንደሚፅፉ ይነገራል፡፡
  • አራቱን የሂሳብ ስሌቶች የመለየት ችግርም የምሩቃኑ ሌላው ጣጣ ነው፡፡
  • በሶሲዎሎጅ ተመርቀው ካርል ማርክስ ሲባል እሱ ደግሞ ማነው? ማለትም ያስደነግጣል፡፡
  • ህግ ተምረው የCivil Right እና የCivil Code ልነትን አለማወቅም ይወራል፡፡

አዎ ጥራቱ ችግር ውስጥ ነው፡፡

2. ሁለተኛው እና አዲሱ የትምህርት ፖሊሲው ችግር ሰዎች ተምረው በተማሩበት ትምህርት መስክ ሊሰሩ አለመቻላቸው ነው፡፡

የማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን የ2011 ዓ.ም የከተማ ስራ አጥነት 18 በመቶ እንደሆነ መረጃው ያስረዳል ፡፡ሌሎች አለማቀፍ ተቋማት ደግሞ መጠኑ ከዚህ እንደሚልቅ ይገልፃሉ፡፡

እንግዲህ ከዩንቨርስቲ የሚወጡት ምሩቃን ከነዚህ ስራ አጦች ቁጥር ላይ የሚደመሩ ናቸው፡፡ ይሄን ቁጥር ለመቀነስ ይመስላል መንግስት ሰሞኑን እንደምንሰማው ወጣቶችን በተለያዩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ተግባራት ላይ እንዲሰማሩ እያደረገ የሚገኝው፡፡

  • ችግሩ ግን አንድ ሰው Computer Science ተምሮ የኮብል ስቶን ጠረባ ላይ የመሰማራቱን ጥቅም ስናሰላስለው ነው፡፡
  • ችግሩ ግን አንድ ወጣት በPhysics ተመርቆ በከተማ ግብርና ተግባር ላይ ሲሰማራ የተማረውን ትምህርት ተግባር ላይ እንዴት ሊያውለው ይችላል? ያልን እንደሆነ ነው፡፡
  • ችግር የሚሆነው Afan Oromo & Literature የተማረች ወጣት በባልትና ውጤት ስራ ላይ ተሰማርታ ስናይ ነው፡፡

ይሄ ስኬት ነው እንዴ ለመሆኑ?

Nelson Mandela በግለ-ታሪካቸው ላይ ስለ ትምህርት ሲናገሩ :

“Education is the great engine of personal development. It is through education that the daughter of a peasant can become a doctor, that a son of a mineworker can become the head of the mine, that a child of farm workers can become the president of a nation.”

አሁን ወዳለው ሀገራችን የትምህርት ውጤት ስንሄድ ማንዴላ እንደሚሉት ትምህርት የገበሬውን ልጅ ዶክተር ፣ የማዕድን ቆፋሪውን ልጅ የሀገር መሪ የሚያደርግ መሳሪያ ነው ያሉትን የትምህርት Upgrade የማድረግ ሚና Downgrade በማድረግ የተተካ ያስመስለዋል፡፡ አለዚያማ ስለ ፓለቲካል ህልዮት ሲማር የከረመ ወጣት እንዴት የብየዳ ስራ ላይ ይሰማራል?፡፡

ገነት ‹‹ስለ ስራ አስበሽ ታወቂያለሽ?›› ተብላ ስትጠየቅ ‹‹እኔ የምማረው እናቴ ተመርቄ ስታየኝ ደስ እንዲላት ነው እንጅ ስራ መስራት አልፈልግም›› ትላለች፡፡ እንግዲያውስ ገነቶችን ከምሁራን መካከል መፈለግ ምን ሊረባ?

የኪራይ ሰብሳቢ ማዕበል

በዘላለም ክብረት
“Rent-seeking may, indeed, impose costs to the economy as high, if not higher, than those arising from corruption.”
  Anthony Ogus , Corruption and Regulatory Structures.

ገንዘብን መግዛት (Rent seeking)

በስነ ምጣኔ ሳይንስ ከእያንዳንዱ ኢኮኖሚ ጀርባ ብዙ ጋሬጣዎች(Economic Inefficiencies) ሊኖሩ ይችላሉ ለምሳሌ እንደ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲ ክፍተት፣ ሙስና ፣ ገንዘብን መግዛት (Rent seeking) ወ.ዘ.ተ ናቸው፡ ከነዚህ የኢኮኖሚ ማነቆዎች ውስጥ ገንዘብን መግዛት (Rent seeking) የተባለውን ስንመለከት፡፡በአጠቃለይ ኢኮኖሚስቶች ‹‹እሴት አልባ ትርፍ ወይም አሁን ያለው ገንዘብ በራሱ ያለምንም ዕሴት ማጎልበት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲገዛ ለዛ መበርታት›› ብለው ይተረጉሙታል፡፡

John Mbaku የተባሉ ኢኮኖሚስት ‘Corruption and Rent-seeking’ ባሉት ፅሁፋቸው ገንዘብን መግዛትን ‹‹የመንግስት ፖሊሲዎችን ውጤት ለማስቀየር የሚደረግ እንቅስቃሴ›› ብለው ይተረጉሙታል ፡፡ የገንዘብን መግዣ ድርጊቶች ስንመለከት የተያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

Anne Kruger የተባሉ የሚኒሶታ ዩንቨርስቲ ኢኮኖሚስትThe Political Economy of Rent-Seeking Economy’ ባሉት ፅሁፋቸው ‹‹ገንዘብን ለመግዛት የሚደረገው ውድድር አንዳንዴ ንፁህ እና ህጋዊ በሆነ መልኩ አንዳንዴ ደግሞ እንደ ሙስና፣ ጥቁር ገበያ እና ህገወጥ የዕቃ ማስተላለፍ ያሉትን ህገወጥ መንገዶች በመጠቀም ሊከናወን ይችላል›› ይላሉ፡፡ ይሄም ገንዘብን መግዛት ሁሌም ህገወጥ ተግባር ብቻ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ ያደርሰናል ማለት ነው፡፡

John Mbaku ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፋቸው በታዳጊ ሀገራት የገንዘብን መግዛት ተግባር በስፋት የሚታይ እንደሆነ ይሄም በከተሞች ጎላ ብሎ እንደሚታይ እና ከገንዘብን መግዥ ተግባራት ማነኞቹ ቢሮክራሲያዊ ሙስና እና የፖለቲካ አመፅ ማስነሳት መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ አያይዘውም ‹‹በመንግስት የተያዙ ሞኖፖሊዮች ለገንዘብን መግዣ ተግባራት ዋነኛዎቹ መፈልፈያዎች ናቸው›› ይላሉ፡፡ ‹‹ምክንያቱም እነዚህ ኖፖሊዩች ተወዳዳሪ ስለሌላቸው ገንዘብን እንደፈለጉ ያደኑታል ያለምንም ማህበራዊ አበርክቶ ደንበኞችም ያለምንም አማራጭ የቀረበላቸውን አገልግሎት ይጠቀማሉ፡፡››

ኪራይ ሰብሳቢነት ስንል

ኢትዩጵያ ውስጥ የገንዘብን መግዣ (Rent Seeking) ፅንሰ ሃሳብ ከሶሻሊዝም ጋር አብሮ እንደጎለበተ ለማየት ይቻላል እንደ ካፒታሊዝም ውድቀት ተደርጎ በመወሰድ፡፡ በዋነኛነት ግን የህብረተሰቡ ተወስኦ(Public Discourse) አካል እየሆነ የመጣው ከ1997 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ምርጫ በኋላ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ‘AFRICAN DEVELOPMENT: DEAD ENDS AND NEW BEGINNINGS’ ባሉት እና ከ600 ገፅ በላይ እንዳለው የተነገረውን የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያቸውን ከሆነው ፅሁፍ ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ (Preliminary Draft) ላይ በ50 ገፅ ቁራጭ ታሪኮች (Excerpts) ፅሁፍ እ.አ.አ በ2006 ዓ.ም አቅርበዋል፣ ለውይይት አላማ በሚል፡፡ የዚህ ፅሁፍ ዋነኛ ማጠንጠኛም ይሄው የገንዘብን መግዛት (Rent Seeking) ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ለዛም ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ 50 ገፅ አካባቢ ፅሁፍ ውስጥ ወደ መቶ ለሚጠጋ ጊዜ Rent Seeking የሚለውን ቃል ይደጋግሙታል፡፡ አንድ ምዕራፍም በአፍሪካ ያለውን የገንዘብን መግዛት (Rent Seeking) ፖለቲካል ኢኮኖሚን ለመተንተን አውለዋል፡፡

እንደ መደምደሚያም “Only when there is a state that has the characteristics of a developmental state can one meaningfully discuss the elimination of rent-seeking behavior. In its absence rent-seeking will be rampant no matter what the size of the state might be.” በማለት የገንዘብን መግዛት ክፉ ጠንቅን የሚዋጋው ልማታዊ መንግስት (Developmental State ) እንጅ ከዳር ቆሞ የሚመለከት መንግስት (Night watch man State) አይደለም በማለት ሀሳባቸውን ያሳርፋሉ፡፡

እንግዲህ በኢትዮጵያ የገንዘብን መግዛት ፅንሰ ሀሳብ ‘ኪራይ ሰብሳቢነት’ በሚል ስም ዋነኛ የውይይት አርዕስት የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከላይ የጠቀስነውን ፅሁፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ የኢህአዴግ ዋነኛ ልሳኖችም ጉዳዩን ለህብረተሰቡ በሰፊው ማቀበል የጀመሩት ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው በኋላ ላይ ከፓርቲው ልሳኖች በተጨማሪ የመንግስት የሚዲያ ተቋማትም ጉዳዩ የሀገሪቱ ታላቅ ስጋት እንደሆነ አድርገው እያቀረቡት ይገኛሉ፡፡

‹‹ደላሎችን በሙሉ ኪራይ ሰብሳቢ ናቸው ማለት ተገቢ አይደለም››

ይህ አንድ የደላላ ማህበር ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የፃፈው ደብዳቤ ርዕስ ነው፡፡ አሁን ባለው አካሄድ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በ2 ጎራ ከፍሏል ማለት ይቻላል፡፡ የልማታዊነት ጎራ እና የኪራይ ሰብሳቢነት ጎራ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢው ማነው? ካላችሁ እስከ አሁን ድረስ በፓርቲው ሰነዶች ውስጥ ግልፅ ትርጉም አልተሰጠውም ይልቅስ ድርጊቶችን ብቻ በመጥቀስ ይሄ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው ይሄ ልማታዊነት ነው በማለት እየተገለፀ ነው፡፡

ጨዋታ ነውና ጉዳዩን እንደሚከተለው እንየው እስኪ ፡

* ኪራይ ሰብሳቢነት ምንድን ነው?

እስከ አሁን የተገለፀ ነገር የለም፡፡

* የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች ምንድን ናቸው?

– ‹‹ኪራይ ሰብሳቢው በዋነኛነት የመሸገባቸው፣ መሬት፣ ግብር፣ ንግድ፣ የመንግስት ግዥ አሰራሮች ናቸው›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 45-46

* ኪራይ ሰብሳቢነት በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ እንዴት ይገለፃል?

‹‹የመንግስት መዋቅሩ የኪራይ ሰብሳቢነት ፍርፋሪ በመለቃቀም የተጨማለቀ ወይም ከዛሬ ነገ ፍርፋሪ ይጣልልኝ ይሆናል ብሎ የሚጠብቅ ሰው ያልተለየው መዋቅር ነው፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት የውስጥ አርበኛ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 28-29 እያለ የመንግስት ሰራተኛውን ይከሳል እንዲያም ሲል ‘የመንግስት ሌቦች’ ይለዋል፡፡

* ኪራይ ሰብሳቢነት በጥቅሉ በሀገሪቱ እንዴት ይገለፃል?

‹‹ከአስር አመታት በፊት የሀገራችን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተመቸ እና ኪራይ ሰብሳቢው የሚቆጣጠረው ነበር፡፡ኪራይ ሰብሳቢነትን የመታገል እና የማዳከም ስራችን በመሰረቱ በትክክለኛ አቅጣጫ እየተጓዘ ነው ፡፡ አደጋውን ለይተናል ምንጩን እና የትግል አግባቡን አስቀምጠናል፡፡ ተግባራዊ ትንቅንቅ ጀምረናል፡፡›› እንዲሁም ‹‹ኪራይ ሰብሳቢው መግቢያ መውጫውን ከማወቁ እና የቁማርተኛ አይነት ድፍረት ተጠናወተው በመሆኑ ከእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኝት ከሚገባው በላይ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 45

* ኪራይ ሰብሳቢነትን በዋናነት መታገል ያለበት ማነው? ብላችሁ ስትጠይቁ ደግሞ፡

– ‹‹የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር በመታገል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የዜግነት ግዴታ ያለበት ቢሆንም መምህራን ካለባቸው ብቁ ዜጋ የመቅረፅ ኃላፊነት አኳያ ያለባቸው ኃላፊነት ድርብ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 54 ብሎ መምህሩን ሀላፊነት ይሰጠዋል፡፡

* የኪራይ ሰብሳቢነት እና የዕምነት ግንኙነት እንዴት ነው ካላችሁ?

‹‹አክራሪነትን ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር አስተሳስረን እንፋለመዋለን›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 38 እንዲሁም ‹‹አክራሪነትን ከኪራይ ሰብሳቢነት ነጥለን መታገል አንችልም›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 40 በማለት የኪራይ ሰብሳቢነትን አድማስ ከአክራረነት ጋር አያይዞ ያየዋል፡፡

* Where is the Rendezvous of this ‘ኪራይ ሰብሳቢነት’? ካላችሁ መልሱ :

‹‹የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከቶች በከተሞች ሰፋ ያለ አድማስ አላቸው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 9 ገፅ 31

* ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዴት ይታያሉ?

‹‹በሀገራችን የሚገኝው የተቃውሞ ቡድን ባነገበው አላማና በኪራይ ሰብሳቢነቱ አንድ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ጋቢት ሚያዚያ 2002 ገፅ 4

* ለመሆኑ ኪራይ ሰብሳቢነት በህግ ያስቀጣል?

– ‹‹ዋናዎቹን ኪራይ ሰብሳቢዎች ወደመቅጣት የምንገባው ከመጥፎ ተግባር አልላቀቅ ሲሉና ማረሚያ ሌላ አማራጭ ሲጠፋ ነው፡፡›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 2 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 33

* በአጠቃለይ ከኢትዮጵያዊያን ምን ይጠበቃል?

– ‹‹የልማት አብዮቱን ለማጎልበት ኪራይ ሰብሳቢነትን ለቀቅ ልማታዊነትን ጠበቅ›› አዲስ ራዕይ ቁጥር 6 ቅፅ 3 ቁጥር 8 ገፅ 36 እያለ ፓርቲው ምላሽ ይሰጣል ጉዳዩንም ከመሬት ወራሪዎች እስከ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እንዲሁም መምህሩን እና የሀይማኖት መሪዎችን እየነካካ መጨረሻ የሌለው እስኪመስል ድረስ ይጓዛል፡፡ ይሄን ስንመለከትም ኪራይ ሰብሳቢነትን እንረዳው ዘንድ ይከብድብናል፡፡ ምን ማለት ይሆን? ያስብለናል::

ለማንኛውም፡

‹‹ጉልበተኛ ይሰይማል፡፡ መሰየም የጉልበተኛ አንዱ እና ትልቁ አቅም ነው፡፡ አንተ ሽብረተኛ ነህ ምክንያቱም ፂምህ ከደረትህ ደርሷልና፣ አንች ያለፈውን ስርዓት ናፋቂ ነሽ ምክንያቱም አባትሽ ለንጉሱ ስርዓት አፋሽ አገንባሽ ነበርና፣ አንተ መንግስትን በሀይል ለመገልበጥ ከሚሰሩ ህሎች አንዱ እና ዋነኛው ነህ ምክንያቱም ሀምሌ 27 የተባለ ፓርቲ ልሳን እቤትህ ተገኝቷልና ወ.ዘ.ተ እያለ ስያሜው ይቀጥላል፡፡ ምክንያቱም ጉልበተኛ ሲሰይም ማንም ተው አይለውምና፡፡››

ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ ?

ዘላለም ክብረት

ህዝብ አብሮ ሲኖር ግጭት ሊያስወግደው የማይችለው ነገር ነው፡፡ የሰዎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እስካለ ድረስ ግጭት አለ፡፡ በግጭቱ ጉልበተኛው አሸንፎ ተሸናፊውን እንደፈለገ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ እንግሊዛዊው የስነ መንግስት ሊቅ Thomas Hobbes ‘State of Nature’ የሚለው ወይም ጉልበተኛ የሚገዛበት ደካማ የሚጠቃበት እና Hobbes “ life is solitary, poor, nasty, brutish, and short” ብሎ የገለፀው ሀሳባዊ አለም ነው፡፡

ይህ እንዳይሆን ህዝብ ስምምነት ላይ ደረሰ ይሄንም ስምምነት በልቦናው ፈረመ ‘መንግስት’ የሚባልም አካል መሰረተ፡፡ ይህ አካልም ከህዝቡ ጉልበት ተቀንሶ ጉልበተኛን ይቀጣ ዘንድ ተሰጠው እንዲሁም ይህ መብት እንዳለው ሁሉ የህዝቡን ሰላም የማስጠበቅም ግዴታ ተሰጠው፡፡ ማን ? መንግስት የተባለው አካል፡፡

ታዲያ መንግስት በጦር በጎራዴ ብቻ ሰላምን አያሰጠብቅም ይልቅስ ሰላማዊ መሳሪያውን ይመዛል ይሄም መሳሪያ የመንግስት ህግ ነው፡፡ ህዝቡም ያከብረው ዘንድ ይወዳል ወይም ይገደዳል፡፡ ስለዚህ የመንግስት ህግ ማለት መንግስት ህዝብ ከራሱ የተፈጥሮ ስልጣን ቀንሶ መንግስት ለተሰኝው አካል ስለሰጠው መንግስቱ ይሄን የህዝብ አደራ ለመጠበቅ የሚቀርብ በትር ነው፡፡

በመሰረቱ የኢትዮጵያም ታሪክ በዚህ የመንግስት ህልዮት ይገዛል፡፡ ነገሩ የሚበላሸው መንግስት የተባለው አካል የህዝብን አደራ በልቶ ሌላ ዳቦ መጋገር ሲጀምር ነው፡፡ የህዝቡን ዳቦ በልቶ የራሱን ሽልጦ ሲያነጉት ነው መከራው፡፡

መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የህዝብን ሰላም እና ጥቅም ለመስጠበቅ ህግ ያወጣሉ፣ ይከለክላሉ፣ ያስጠብቃሉ፡፡ ይሄም እውነት በጠነከረ ሁኔታ አሁን ባለንባት ኢትዮጵያ ገዝፎ ይታያል፡፡

ለምሳሌ Read the rest of this entry

ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ ?

ዘላለም ክብረት

ህዝብ አብሮ ሲኖር ግጭት ሊያስወግደው የማይችለው ነገር ነው፡፡ የሰዎች የእርስ በእርስ ግንኙነት እስካለ ድረስ ግጭት አለ፡፡ በግጭቱ ጉልበተኛው አሸንፎ ተሸናፊውን እንደፈለገ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ እንግሊዛዊው የስነ መንግስት ሊቅ Thomas Hobbes ‘State of Nature’ የሚለው ወይም ጉልበተኛ የሚገዛበት ደካማ የሚጠቃበት እና Hobbes “ life is solitary, poor, nasty, brutish, and short” ብሎ የገለፀው ሀሳባዊ አለም ነው፡፡

ይህ እንዳይሆን ህዝብ ስምምነት ላይ ደረሰ ይሄንም ስምምነት በልቦናው ፈረመ ‘መንግስት’ የሚባልም አካል መሰረተ፡፡ ይህ አካልም ከህዝቡ ጉልበት ተቀንሶ ጉልበተኛን ይቀጣ ዘንድ ተሰጠው እንዲሁም ይህ መብት እንዳለው ሁሉ የህዝቡን ሰላም የማስጠበቅም ግዴታ ተሰጠው፡፡ ማን ? መንግስት የተባለው አካል፡፡

ታዲያ መንግስት በጦር በጎራዴ ብቻ ሰላምን አያሰጠብቅም ይልቅስ ሰላማዊ መሳሪያውን ይመዛል ይሄም መሳሪያ የመንግስት ህግ ነው፡፡ ህዝቡም ያከብረው ዘንድ ይወዳል ወይም ይገደዳል፡፡ ስለዚህ የመንግስት ህግ ማለት መንግስት ህዝብ ከራሱ የተፈጥሮ ስልጣን ቀንሶ መንግስት ለተሰኝው አካል ስለሰጠው መንግስቱ ይሄን የህዝብ አደራ ለመጠበቅ የሚቀርብ በትር ነው፡፡

በመሰረቱ የኢትዮጵያም ታሪክ በዚህ የመንግስት ህልዮት ይገዛል፡፡ ነገሩ የሚበላሸው መንግስት የተባለው አካል የህዝብን አደራ በልቶ ሌላ ዳቦ መጋገር ሲጀምር ነው፡፡ የህዝቡን ዳቦ በልቶ የራሱን ሽልጦ ሲያነጉት ነው መከራው፡፡

መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የህዝብን ሰላም እና ጥቅም ለመስጠበቅ ህግ ያወጣሉ፣ ይከለክላሉ፣ ያስጠብቃሉ፡፡ ይሄም እውነት በጠነከረ ሁኔታ አሁን ባለንባት ኢትዮጵያ ገዝፎ ይታያል፡፡

ለምሳሌ ኢህአዴግ ስልጣን ይዞ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ከፀደቀበት ህዳር 1987 ዓ.ም ወዲህ፡

– ወደ 750 የሚደርሱ አዋጆች፣
– ከ200 በላይ ደንቦች፣
– በሽዎች የሚቆጠሩ መመሪያዎች ወጥተዋል፡፡

እነዚህ ህጎች በአጠቃላይ መብትን ማስጠበቂያና ግዴታን መስጫ ናቸው፡፡ እንደ ሁሉም የህግ ባህሪያት፡፡ አስገራሚ የሚሆነው ጉዳይ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ የሚወጡ ህጎች ብርታት እና ሀይል ነው፡፡

የፕረስ ህጉ አዋጅ ቁጥር 590/2000 ፣ የሙያ ማህበራት ህግ አዋጅ ቁጥር 620/2000፣ የፀረ-ሽብር ህግ አዋጅ ቁጥር 652/2001፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ቁጥር 662/2001፣ የሊዝ ህግ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ብለን የዋነኛዎቹን ብርቱ ህጎች መዘርዘር ይቻላል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪ ደግሞ በረቂቅ ደረጃ ያለ የሁሉንም ሰው በር ሊያንኳኳ የሚችል አዲስ የህግ ረቂቅ የቴሌኮም ህግ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

እንግዲህ ለጨዋታችን ይሄን ረቂቅ ህግ ከፀረ-ሽብር ህጉ ጋር አብረን እንመልከተው፡

– ማሞ እና ብሪቱ አዲስ ሙሽራዎች ሲሆኑ የፍቅራቸው ሙቀት አልበርድላቸው ብሎ የሚያደርጉትን አሳጥቷቸዋል:: ለዚህም ይመስላል ማሞ ህዝብ ይወቀው፣ ይመልከተው ብሎ ከብሪቱ ጋር ሲቃበጡ እና የጭናቸው ፍም በጋለበት ወቅት እያደረጉት ያሉትን ድርጊት ምስል የፌስቡክ ገፁ ላይ የለጠፈው፡፡ ግማሾቹ ጓደኞቹ ምነው ማ ሞ ! ሲሉት ግማሾቹ ደግሞ ኧረ ማሚሻ ቀወጥሽው ሎል ምናምን ብውለታል፡፡

በአዲሱ ረቂቅ የቴሌኮም አዋጅ አንቀፅ 6 መሰረት ማንኛውም ሰው ፀያፍ የሆነ ነገርን ማንኛውንም የቴሌኮም መሳሪያ ተጠቅሞ ለህዝብ ያሳወቀ ከሆነ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 640 የተደነገገው ቅጣት እንዳለ ሁኖ ከ 3 – 8 ዓመት ያስቀጣል፡፡ እንግዲህ ህጉ ከፀደቀ አቶ ማሞንም መልካም የእስር ወቅት ለማለት እንገደዳለን እንዲሁም ሞቶ በክር መታሰር ነው ክፉ ስምንት ዓመት እማ ስምንት ቀን ናት ብለን ለማፅናናት እንወዳለን፡፡

– አያንቱ የዩንቨርስቲ ትምህርቷን ጨርሳ በአንድ የመንግስት ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ ለሁለት ዓመታት ካገለገለች በኋላ በአንድ የምስራቅ አውሮፓ ሀገር ነጻ የትምህርት ዕድል ታገኛለች፡፡ ማንንቷን እና የቋንቋ ችሎታዎን ለማረጋገጥ በሚል ዩንቨርስቲው አያንቱን በ Skype ለሚደረግ የ30 ደቂቃ ቃለ መጠይቅ ይጋብዛታል፡፡ አያንቱም በተቀጠረችበት ሰዓት ሰፈር ውስጥ የሚገኝ አንድ ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ተገኝታ ቃለ ምልልሱንም በድል ትወጣለች፡፡ የማረጋጋጫ ደብዳቤም ይደርሳታል፡፡

በአዲሱ የቴሌኮም አዋጅ አንቀፅ 10 ንኡስ ቁጥር 4 መሰረት ማንም ሰው እያወቀም ሆነ በቸልተኝነት በኢንተርኔት የሚደረግን የስልክ ወይም የፋክስ ጥሪ ያደረገ ከሆነ ከ3 ወራት እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ቅጣት ይቀጣል፡፡

እንግዲህ ይህ ረቂቅ አዋጅ ከወጣ እህት አያንቱ ወደ ትምህርት ከመሄድ ይልቅ ወደ እስር ቤት መሄዷ እውን ይሆናል፡፡

እሱ እንዳለው ያ ሎሬቱ <>

– ዳርጌ ፌስቡክ ላይ ነው ውሎ አዳሩ፡፡ የሆነ ቀን ነሸጥ ሲያደርገው “አልሻባብ ድሬዳዋን ተቆጣጠረ ይሄም የጫትን ዋጋ ሊያንረው ይችላል” ብሎ ይለጥፋል:: በጉዳዩ የተደናገጡት ፌስቡካዊያን ጨኸታቸውን ያሰማሉ፡፡

በፀረ ሽብር ህጉ ማኝኛውንም የሽብር ድርጅት መደገፍ እንዲሁም ህዝብን ሊያሸብሩ የሚችሉ መረጃዎችን የለቀቀ አሁን ደግሞ በረቂቁ የቴሌኮም አዋጅ ማንኛውንም የቴሌኮሚኒኬሽን መሳሪያ ተጠቅሞ አሸባሪ መልዕክት ያስተላለፈ ሰው እስከ 8 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡

እንግዲህ ዳርጌም የዚሁ አንቀፅ ተሸላሚ ነው ማለት ነው፡፡ በርግጥ ዳርጌ “ፅሁፉን የፃፍኩት ጓደኞቼን አሰደንግጨ April the Fool ለማለት ነው” እንደሚል አይጠረጠርም፡፡

Thomas Hobbes ከመቃብር ቀና ብሎ ይሄን ቢመለከት የስነ መንግስት ትንታኔውን ያሻሽለው ይሆን ወይስ  Sometimes, the state of nature can be the case even if there is a Law, since an unjust law is not a law at all” ይላል? እኛም  መንግስት ከሕዝብ ኃይል ተቀናንሶ የተሰጠውን በትር አደራውን ሳይሆን ሌላ ነገር ሲጠብቅበት ባየን ጊዜ Is Rule by law a Rule of Law? ብለን እንጠይቃለን::

Generation “?”

ትውልድ ይሄዳል የሄደውን ለመተካት ደግሞ ሌላ ትውልድ የመጣል፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ማህተም አስቀምጦ በሌላ ይተካል፡፡ በምዕራቡ አለም በተለያየ ጊዜ የሚመጡ ትውልዶች የትወልዱን ባህርያት መሰረት በማድረግ የተለያየ የጊዜ ክፍፍል እና የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ፡

The Lost Generation ፡ ይሄ ትውልድ ከ19 ክፍለ ዘመን መጨረሻ እስከ አንደኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ የነበረው ሲሆን በጦርነቱ ማብቂያ ህልውናው ያከተመ ነው፡፡

The Silent Generation፡ ይህ ዝምተኛ ትውልድ ደግሞ የአንደኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀበት እስከ ታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት (The Great Depression) ድረስ የነበረው ሲሆን በአመዛኙ ድብታ የዋጠው ነበር፡፡

The Greatest Generation: ታላቁ ትውልድ የተሰኝው ደግሞ ታላቁን የኢኮኖሚ ድቀት ተቋቁሞ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተፈትኖ ያለፈው እና እንደ ብረት የጠነከረ የተባለው ነው፡፡

Generation X፡ ይህ ትውልድ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ የ1960ዋቹን አለማቀፍ የነፃነት፣ የአንድነት እንዲሁም የፀረ-ጦርነት ሰልፎች ሲያካሂድ የነበረ እና በባህል ለውጥ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው ትውልድ ነው፡

Generation Y or The Millennial Generation:  የ Generation X ተከታይ ትውልድ ሲሆን በቴሌቪዥን እና በዲጅታል ሚዲያዎች ፍቅር የወደቀ እንዲሁም በሁሉም ነገር ለዘብተኛ ሊባል የሚችለው ትውልደ ነው፡፡

Generation Z፡ የDotcom Bubble ውጤት የWorld Wide Web ፍሬ እና ቀሰስተኛው ትውልድ ሲሆን ዘመኑም አሁን ነው ይላሉ፡፡

እነዚህን እና የመሳሰሉትን የትውልድ ተረኮች አሉ፡፡

ወደ ሀገር እኛ ሁኔታ ስንመጣ  መሰረታዊ የሆነ የትውልድ ልዩነት፣ ጊዜ እንዲሁም ስያሜ አለ ማለት ባይቻልም በተለምዶ ‘ያ ትውልድ’ እየተባለ የሚጠራው እና የኢትየጵያን አብዮት የመራው እንዲሁም ከ ሶሻሊዝም ጋር በፍቅር ያበደው ትውልድ እንደ አንድ ትውልድ ይዘን ወደፊት እና ወደኋላ መሄድ እንችላለን፡፡ Read the rest of this entry

Generation “?”

ትውልድ ይሄዳል የሄደውን ለመተካት ደግሞ ሌላ ትውልድ የመጣል፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ማህተም አስቀምጦ በሌላ ይተካል፡፡ በምዕራቡ አለም በተለያየ ጊዜ የሚመጡ ትውልዶች የትወልዱን ባህርያት መሰረት በማድረግ የተለያየ የጊዜ ክፍፍል እና የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ፡

The Lost Generation ፡ ይሄ ትውልድ ከ19 ክፍለ ዘመን መጨረሻ እስከ አንደኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ የነበረው ሲሆን በጦርነቱ ማብቂያ ህልውናው ያከተመ ነው፡፡

The Silent Generation፡ ይህ ዝምተኛ ትውልድ ደግሞ የአንደኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀበት እስከ ታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት (The Great Depression) ድረስ የነበረው ሲሆን በአመዛኙ ድብታ የዋጠው ነበር፡፡

The Greatest Generation: ታላቁ ትውልድ የተሰኝው ደግሞ ታላቁን የኢኮኖሚ ድቀት ተቋቁሞ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተፈትኖ ያለፈው እና እንደ ብረት የጠነከረ የተባለው ነው፡፡

Generation X፡ ይህ ትውልድ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ የ1960ዋቹን አለማቀፍ የነፃነት፣ የአንድነት እንዲሁም የፀረ-ጦርነት ሰልፎች ሲያካሂድ የነበረ እና በባህል ለውጥ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው ትውልድ ነው፡

Generation Y or The Millennial Generation:  የ Generation X ተከታይ ትውልድ ሲሆን በቴሌቪዥን እና በዲጅታል ሚዲያዎች ፍቅር የወደቀ እንዲሁም በሁሉም ነገር ለዘብተኛ ሊባል የሚችለው ትውልደ ነው፡፡

Generation Z፡ የDotcom Bubble ውጤት የWorld Wide Web ፍሬ እና ቀሰስተኛው ትውልድ ሲሆን ዘመኑም አሁን ነው ይላሉ፡፡

እነዚህን እና የመሳሰሉትን የትውልድ ተረኮች አሉ፡፡

ወደ ሀገር እኛ ሁኔታ ስንመጣ  መሰረታዊ የሆነ የትውልድ ልዩነት፣ ጊዜ እንዲሁም ስያሜ አለ ማለት ባይቻልም በተለምዶ ‘ያ ትውልድ’ እየተባለ የሚጠራው እና የኢትየጵያን አብዮት የመራው እንዲሁም ከ ሶሻሊዝም ጋር በፍቅር ያበደው ትውልድ እንደ አንድ ትውልድ ይዘን ወደፊት እና ወደኋላ መሄድ እንችላለን፡፡

ከ ጣሊያን ወረራ እስከ ያትውልድን ድረስ ያለውን ዘመን ‘የነፃነት ትውልድ’ ልንለው እንችላለን ህይወቱ ሁሉ በወረራው ዘመን የተቃኝ በመሆኑ፡፡ ኑሮው ሁሉ የአርበኛ እና ባንዳ ፉክክርን ያስተናገደ እንደመሆኑ፡፡ እንግዲህ በምዕራቡ አለም Generation Yዎች የ Generation X ልጆች ናቸው ካልን በኛ ሁኔታ ደግሞ ያ ትውልድ የነፃነት ትውልድ ልጆች ናቸው ማለት እንችላለን፡፡

ችግር የሚሆነው የያ ትውልድን ጊዜ ማስቀመጥ አሁን ያለውንም ትውልድ ልዩነት ማወቁ ላይ ነው፡፡ ፖለቲካል ኢኮሚውን የውልድ አባላት እስከ አሁን እንደሚያሽከረክሩት መናገሩ የተራራ ላይ ሚስጥር ነው፡፡ እና የአሁኑ ዘመን ትውልድ መለያዎችስ ምን ይሆኑ? ነገሩ ጨዋታ እንደመሆኑ ቀጣዮቹ ምልልሶች እመልከት እስኪ፡

ሊሊ እና ጄሪ

ሊሊ፡ እኔ እምልሽ Justin ፀጉሩን ተቆረጠ የሚባለው እውነት ነው?

ጄሪ፡ No way, አያደርገውም ! ይሄ ለኛ ለአድናቂዎቸ ክብር አለመስጠት ነው፡፡ ከSelinaጋር ያለውን ግንኙነት ግልፅ አለመሆን ሲገርመኝ ብሎ ብሎ ደግሞ በምንወድለት ፀጉሩ መጣ? I swear, Online petition ካለ I will do that !

ሊሊ፡ Donation ነው አሉ የሰጠው፡፡

ጄሪ፡ ኡፍፍ የዚህን ሁሉ ድሃ ሆድ የሱ ፀጉር ይሞላ ይመስል፡፡ በእውነት Lil Wayneን የምወደው ለአድናቂዎቹ ባለው ክብር ነው! Never, Babyማ ይሄን አያደርግም፡፡

ዳኒ እና ጆኒ

ዳኒ፡ የ Balotelli አይነት የፀጉር ቁርጥ ፈልጌ እዛ እነ ሚኪ ፀጉር ቤትብሄድ ገገማ ብቻ ነው የሞላበት፡፡ አንዱም እንኳን አይችሉም፡፡

ጆኒ፡ እኔ እምለው Balotelli መልበሻ ክፍል ውስጥ የሆነ ነገር ሳያደርግ አልቀረም ስልጠና ላይ ብቻውን ነበር፡፡

ፊፊ እና ቲቲ

ፊፊ፡ የKaty Perry ፀጉር Human Hair መሆኑን ትናንት ሊዮና ነግራኝ ከምር Katyን ታዘብኳት፡፡

ቲቲ፡ እንጅ እኔም ግንባሯን Botox ተሰርታለች የመል ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ Otherwise, how on earth, her skin slimmed as lip?

ባቢ እና ጃክ

ባቢ፡ Rooney ባለፈው Surgery ካደረገ በኋላ አውሮፓ ዋንጫ ላይ ከBeckham ጋር ተቀራራቢ የፀጉር ቁርጥ መቆረጡን አየህ?

ጃክ፡ አዎ ቅድም Sky Sport ላይ አይቸዋለሁ፡፡ መጀመሪውኑ በድብቅ ሰርጀሪ የተሰራ ጊዜ ነውእሱን የታዘብኩት፡፡ እሽ ለማንም ሳይናገር አንደ ነገር ቢሆን የምንጎዳው እኛ አይደለንም?

ባቢ፡ እውነትሽን እኮ ነው ጃኮ፤ ግን ፈርጊ ያስተካክለዋል ብየ አስባለሁ፡፡ ሁልጊዜም በፈርጊ እምነት አለኝ፡፡

The Lost Generation or The EPRDF Generation?

የሁለት ‘ሚኒስትሮች’ ወግ

ወግን ‹‹ሥርዐት ደንብ ወይም የተደረገውን  ታሪክ ማውጋት መተረክ ፣ ለሹሞች ለአለቃ ለቄስ ገበዝ የሚሰጥ ወይም የነፍስ አባት የሙት ልብስን አልጋን ዋንጫን መግፈፍ።›› ብሎ ከሳቴ ብረሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ይፈታዋል፡፡

እኛም ከዚህ ትርጉም  ውስጥ ‹‹የተደረገውን ታሪክ ማውጋት መተረክ›› የሚለውን ተከትለን የሁለት መሪዎችን/ጠቅላዮችን ጨዋታ እንጨዋወታለን፡፡

Twitter በተባለው የማህበራዊ ድረ ገፅ አስከ ፈረንጆቹ 2012 ድረስ ከ 140 ሚሊየን በላይ ግለሰቦች ተመዝግበው ስለተለያዩ ጉዳዮች ሃሳባቸውን ያካፍላሉ በተከታዮቻቸውም (Followers) ምላሽ እና አስተያየት ያገኛሉ እነርሱም የፈለጉትን ሰው መከተል (Follow) ይችላሉ፡፡

ከነዚህ መራጆቸ (Twitterati) መካከልም  ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ @MelesZenawi እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ @HailemariamD እንደሚገኙበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰምተናል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ Twitterን የተቀላቀሉት ከ3 ዓመት በፊት ማለትም April 9/2009 እንደሆነ የTwitter ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በመጀመሪያ ያደረጉት Tweetም “Just had some of my favorite Shiro. Thank You Chef” የሚል ሲሆን፡፡ ይህችም Tweet በተለያዩ ግለሰቦችም ዘንድ የተለያየ አንድምታ የምትፈጥር ሆናለች፡፡ Read the rest of this entry