Category Archives: ሳምንቱን በሕትመት ውጤቶች

ጋዜጦችና መጽሔቶቻችን ባሳለፍነው ሳምንት

መሰናዘሪያ ጋዜጣ በማክሰኞ፣ መስከረም 22 እትሙ፡-
ስለ የኢትዮጵያ ዲስፖራና  ፖለቲካ ተጽዕኖው፣ የመሪነት ሚናና የብሔረሰቡ ስነ ልቦና፣ በአሥር ዓመት 15 ቢሊዮን ዶላር ስለመዘረፉ፣ ከብልሀቱ ፍርሃቱ ያዘነበለው የአጃቢዎች ጋጋታ፣ የእኔነት ስሜት ይሰማን በሚል ርዕስ የቀረበው ርዕሰ አንቀጽ እና ሌላም ሌላም ጽፏል፡፡
ሰንደቅ በረቡዕ፣ መስከረም 23 እትሙ፡-
ንግድ ባንክ ለ40/60 ቤቶች ግንባታ ብድር ለመፍቀድ ሥራውን ማጠናቀቁን እንደገለጸ፣ 800ሚሊዮን ዶላር የሚፈጀው ግዙፉ የጦሳ ብረታ ብረት ፋብሪካ የግንባታ ስምምነት እንደተፈረመ፣ ስለኦህዴድ የሰላ መደባዊ ትግል፣  ሞሳድ የኢትዮጵያን አውሮፕላን ማጋየት ለምን እንደፈለገ ዊኪሊክስን አጣቅሶ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይዞ ወጥቷል፡፡ በርዕሰ አንቀጹ ‹‹ፓርላማው ጠንካራ የክርክር መድረክ እንዲሆን ከአባላቱ ብዙ ይጠበቃል፡፡›› ይላል ስለኛ ፓርላማ መሆኑ ነው፡፡  በተጨማሪም መጅሊስ ምርጫው ያለስምምነት እንደቀጠለ ነው፣ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ወደ ስርጭቱ ለመመለስ የተመልካች እርዳታ ጠየቀ፣ በሰንደቅ ቃለመጠይቅ ‹‹የፖለቲካ ለውጥ ይመጣል ብዬ የማስበው ከተቃዋሚ ሳይሆን በኢሕዴግ ውስጥ ነው›› ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ  

በጤና አምዱ ‹‹የአንጀት ካንሰር ወጣቶችን ሳይቀር ማጥቃት ጀምሯል›› ዶ/ር ዳንኤል ዘመንፈስ
‹‹ሐሳብን በነጻ በመግለጽ ነፃነት ስም እየተደፈረ ያለው የእስልምና ሃይማኖት፣
አለሙ ታዬ ‹‹የአስተሳሰብ ምጥቀት ወይም ትልቅነት በምን ይለካል›› ይለናል
ባለራዕይ የወጣቶች ማኅበር በኢህአዴግ ካድሬዎች አሁንም እየተቸገርኩኝ ነው አለ እና ሌሎችም
ሪፖርተር
ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ምን አሉ በሚል ርዕስ ከቪኦኤው ፒተር ሃይንላይን ጋር ያደረጉትን ቃለመጠይቅ አስፍሯል ፒተር ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት የሙስሊሞችን ተቃውሞ ሲዘግብ በመንግስት ኃይሎች ከአስተርጓሚው ጋር ታስሮ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ሰውዬው ገና መውጣታቸው ቢሆንም እስከመቼ ነው ስለራሳችን ከውጪ የምንቃርመው መቼ ነው ፈታ ብለን የፈለግነውን ጥያቄ የምንጠይቃቸው፡፡
‹‹ነጋዴዎች ስንባል ቀጣፊዎች ነን››፣ ‹‹መንግስት ዓይኑን ቢጨፍንልን ጥሩ ነው››፣ ‹‹መንግስት የንግዱን ነገር ለኛ ይተውልን›› ሼክ አል አሙዲ ለመንግስት ባለስልጣናት  ተፎካካሪ የሌላቸው የተረከቡትን መሬትን እንኳ አልምተው ያልጨረሱ ወይም ለቁጥር ያዳገቷቸው ባለኃብት ግለሒስ ከቀልድ ጋር አዋዝተው አቅርበዋል፡፡
የሪፖርተር ጋዜጣ የመሸጫ ዋጋ ከ 7ብር ወደ 10ብር ዛሬ (እሁድ፣መስከረም 27/2005) ገብቷል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመመሪያው ውጪ ብድር የሰጣቸው አሉ›› የሚል ዋና ርዕስ በእሁድ ዜናው አስነብቧል፡፡
‹‹ተቃዋሚ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የብቃት ማረጋገጫ ሊያሳየው ይገባል›› የሪፖርተር  የረቡዕ ርዕሰ አንቀጽ ነው፤ ጥፋቱን ሁሉ ለተቃዋሚ ያሸከመው ሪፖርተር (አማረ) ኢሕአዴግ ብቃት አለው ብሎ ይሆን፡፡
‹‹ስኳር ኮርፖሬሽን የፓኪስታኑን ፋብሪካ ከነባንክ እዳው ገዛ›› አንዲህ ነው ‹በእቅድ› መመራት!
 አቶ ጌታቸው በላይ አልተመለሱም፡፡
‹‹ከስህተቶቻችን ካልተማርን የኢትዮጵያ ዴሚክራሲያዊ ሽግግር አሁንም ሊመልጠን ይችላል›› ሰዬ አብርሃ
የሕዝብ ተራንስፖርት እጥረት ብሶበታል፤ ባለስልጣኑ ችግሩን ለመፍታት አማራጮችን እዘጋጀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ እና ሌሎችም፣
ሐሙስ መስከረም 24 የኛ ፕሬስ
ጠ/ሚ ኃይለማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞ አስተናገዱ በኒውዮርክ የነፃነት ቀንን ለማክበር ወጥተው የነበሩት ሰልፈኞች ጠ/ሚሩ ከቪኦኤው ፒተር ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ተበሳጭተው ሰልፉን ወደ ተቃውሞ እንደቀየሩት ጋዜጣው ዘግቧል፣ በርዕሰ አንቀፁ ‹‹መንግስት ለጥቅም ሽሚያ መቀነቱን ያጥብቅ›› በማለት አሳስቧል፣ የመድረክ አመራሮች በአትላንታ ስብሰባ አደረጉ፣ አዲሱ የግብፅ መንግስት ‹‹በአባይ ላይ ያለውን ፖሊሲ ወደፊት የምናየው ነው አለ››፣ አስመራ የሄዱት አቡነ መርቆርዮስ በኢሳያስ አፈወርቂ ተባረሩ›› ጋዜጣው ትግራይ ኦንላይንን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን ከሐጂ ኡምራ ጉዞ አገደች ሳዑዲም መጅሊሱን እውቅና ነሳችው ማለት ነው፣ ‹‹የእሬቻ በዓል ባእድ አምልኮ አይደለም›› የተከበሩ አቶ መሃመድ አህመድ ‹‹የጸሎት ስፍራችንን መንግስት ያስከብርልን›› አያንቱ ሄኖክ አየለ፣ ‹‹ቴሌ የሞባይል ሂሳባችንን እየሞጨለፈ ተቸግረናል›› ተጠቃሚዎች ‹‹ችግሩ እንዳለ እናምናለን›› ኤጀንሲው ግብር ከፋይ ዘራፊ መሆኑ ነው እንግዲህ፣ ‹‹ባለቤቴ ከዚህ በፊት ቀዳማይ እመቤት እንድትሆን ተጠይቃ እምቢ ብላለች›› ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ቀዳማዊ እመቤት መሆን የሚገባት ማን ነች ብለው ይጠይቃሉ ኢ/ር ዘለቀ ረዲ በፖለቲካ አምድ ስር፡፡
ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከገበያ እንዲወጣ ተገዶ የነበረው የፍትሕ ጋዜጣ በአዲስ ታይምስ ጋዜጣ በኩል መምጣቱ በሳምንቱ ከገጠሙን መልካም ዜናዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
አዲስ ታይምስ ከፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ይድረስ ለሕወሓት በሚል ጽፈዋል፣ ‹‹የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት›› በሚል ርዕስ ያሬድ ጥበቡ፣ ‹‹አማርኛ ካሳ እንዲከፍል አይገደድም›› በአሰፋ እንደሻው (ዶ/ር)፣ ‹‹ከመለስ በኋላስ 2›› በተመስገን ደሳለኝ… እንዲሁም ‹‹ቃሊቲን በጨረፍታ››፣
‹‹የሃይማኖት ነጻነትና መቻቻል›› በሚል ርዕስ ፕ/ር መስፍን ወልደማርማያም በጻፉት ላይ ስለ ሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 27/1 አንስተው ‹‹ማንኛውምሰው የማሰብ፤ የሕሊናና የሃይማኖት ነፃነት አለው፣ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ፣ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር፣ ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል›› በሚል መንደርደሪያ ስለ ሐሳብን በነፃነት መግለጽ መብት አጭር ምልከታ አድርገዋል ኃይማኖትም ቢሆን ከትችት እንደማያመልጥና ተከታዮቹን ሳንነካ ልንተች እንደምንችል አስረድተዋል፡፡ ተከታዮቹ ቢከፉም ያ ሰው ግን የራሱን ሐሳብ ወይም እውነት በመግለፁ የማንንም መብት እንዳልጣሰ ይገልጻሉ፤ ሐሳብን የመግለጽ መብት ጨዋነትን አይደመስስም መቻቻል ሰውን እንዳይናገር መገደብ አይደለም በማለት ከላይ የጠቀሱትን አንቀጽ ደጋግመን እንድናየው ይገፋፋሉ፤ ሲያጠቃልሉም፤ ‹‹ሐሳብን የሚፈራ ማኅበረሰብ እንደረጋ ውኃ ባለበት ይቀራል፤ የሚያድሰው መንገድ ሁሉ ስለተዘጋ አይታደስም፤ ከራሱ የሚተርፈውም አይኖረውምና ለማንም አይበጅም፡፡›› ይላሉ፡፡ ሙሉ ጽሁፉን ከመጽሄቱ ያንብቡ፡፡
የፍትሕ ዓምደኛው እንዳለ ጌታ ‹‹አንዳንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንዳንድ ከያኒ ስመስለው…›› በሚል ርዕስ ስለ አርቲስቶቻችን ልካቸውን ይነግርልናል፡፡ አርቲስቶቻችንን በራሱ ለዛ ባለው አቀራረብ መልሱ አልተሰጠም እንዳይከሰት ተጠንቅቆ በአምስት የከፈለልን እንዳለ ጌታ እንዲህ ይከፋፍላቸዋል ይርጋ ዱባለ፣ ሰለሞን ተካልኝ፣ እና ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የሥነ ጽሁፍ ሰዎች የሆኑት ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሓንስና ተመስገን ገብሬ ናቸው፡፡ ባለስልጣናትና ምሁራን እንዲሁም ሸላሚዎቼና አጉራሾቼ ተገድለውብኝ ዘፈኔን ደርግ መፎከሪያ ሲያደርግብኝ እነሱን የገደለ እኔንም አይምርም ብዬ ዝም አልኩ የሚሉት አርቲስቱ 10ዓመት ሙሉ አብዮት አብዮት ወደፊት እያሉ አገር ሲያካልሉ ነበር ከደርግ ጋር በመሆን በመጨረሻም ለመሰደድ ያበቃቸው የእህታቸው ልጅ መገደል ነው፡፡ እንዳለ እንደሚለው አርቲስቶቻችን ችግሩ የሚታወቃቸው በራሳቸው ሲደርስ ብቻ ነው፡፡ ሙሉውን ከመጽሔቱ ምን ዋጋ አለው እንቶ ፈንቶ የለመዱት አርቲስቶቻችን ቁምነገር የሚጻፍበት መጽሄት ማንበብ አይቀናቸውም የቻላችሁ ግን አስነብቧቸው፡፡
ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌም ‹‹ይድረስ ለሕወሓት ድርጅት›› ተተኪዎቹ ስህተት እንዳይደግሙ መልካሙን አጋጣሚ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡

የሳምንቱ ጋዜጣና መጽሔቶች ከሰኞ እስከ ሰኞ


ሰንደቅ ጋዜጣ
ሰንደቅ ጋዜጣ በዚህ ሳምንት አትሙ 2004 . ጉልህ ክስተቶች የሚል የፌት ገጽ ይዞ ወጥቶዋል፡፡የአመቱ ዋና ዋና ክስተቶች ናቸው የተባሉት መካከልም የደርግ ባለስልጣናት መፈታት፣ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ሰው አልባ ጄቶች ማኮብኮቢያ መፍቀዱዋ፣አወዛጋቢው 70/30 የበጎድራጎት ድርጅቶች ህግ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ መዘጋት እና የዳቦ ዋጋ ጭማሪ፣የአበራሽ ሃይላይ ጉዳይ እና የግብረሰዶማዊያኑ ስብሰባ በኢትዮጵያ ይገኙበታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን በእንግድነት ይዞ የመጣው ሰንደቅ ዳንኤልየሚያስጨንቀኝ ቀጣዩ ፓትሪያርክ ሳይሆን ቀጣይዋ ቤተክርስቲያን ናትማለቱን ጠቅሶዋል፡፡
አዲስጉዳይ መጽሔት
ባለፈው ሳምንት ለገበያ መብቃት ያልቻለችው አዲስ ጉዳይ መጽሔት በበኩልዋ የአመቱን አነጋጋሪ ጉዳይ ሞት በማድረግ በአመቱ በሞት የተለዩ ታላላቅ እና ታዋቂ ሰዎችን ይዛ ወጥታለች፡፡በዋና ዋና አምዶቹም
         የአዲስ ዓመት ገበያ
         ሞት የአመቱ አነጋጋሪ ጉዳይ
         መለስ ዜናዊ የአመቱ አብይ ጉዳይ
         2004 የኢትዮጵያ ፖለቲካ የተጠበቀው የቀረበት ያልተጠበቀው የመጣበት
         2004 ያልተቋጨው የህዝብ ብሶት (ከሊዝ አዋጅ እስከ ኑሮ ውድነት፣የሙስሊሙ ህብረተሰብ የመብት ጥያቄ) ሲሆኑ የተለመዱት ቋሚ አምደኞችም የተለያዩ ጽሁፎቻቸውን ይዘው ወጥዋል፡፡
አዲስ አድማስ
አዲስ አድማስ በቅዳሜ እትሙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀዛዝዋል በሚል ዜና የፊት ገጽ ዜና ይዞ የወጣ ሲሆን ዶር ነጋሶ ጊዳዳን በፓርቲው ጋዜጣ ፍኖተ ነጻነት መታገድ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አናግሮዋቸዋል፡፡አድማስ በተጨማሪም በፊት ገጽ ዜናው እና አህመዲን ጀማል /ቤቱን ይቅርታ ጠየቁ የሚል ዜና ይዞ ወጥቷል፡፡
የሙስሊም ማህበረሰብ ችግር መፍትሔ አፈላላጊ በተሰኘው ኮሚቴ ውስጥ ከሚገኙ 17 አባላት መካከል ስምንቱ በረመዳን ወቅት ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ መታሰራቸውና መከሰሳቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ተከሳሾቹ ለእስልምና ጉዳዮች /ቤት የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የኮሚቴው አባላት ከምክር ቤቱ ጋር በነበራቸው ግጭት፤ የምክር ቤት ምርጫ ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ መቆየቱን በመጥቀስ ምርጫ እንዲካሄድ መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ምርጫው እንደሚካሄድ ከተወሰነ በኋላ ምርጫ የት ይካሄድ በሚለው ጥያቄ አለመግባባት መፈጠሩ ይታወቃል፡፡ ውዝግቡ መፍትሄ ሳያገኝ በረመዳን ወቅት ወደ ግጭት እንደተሸጋገረ የሚታወስ ሲሆን፤ ከኮሚቴው አባላት መካከል ስምንቱ ታስረው ክስ እንደቀረበባቸው ታውቋል፡፡ ተከሳሾቹ የሠራነው ስራ ስህተት በመሆኑ እንደገና በመወያየት ወደተሻለና አዲስ አሠራር እንድንመጣ እንፈልጋለን በማለት ለም/ቤቱ ደብዳቤ እንዳስገቡ የገለፁት ምንጮች፤ የተከሰሱበት ክስ ቀርቶ በይቅርታ ሊፈቱ ይችላሉ በማለት ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡ የመጽሔት አዘጋጅ የሆነውን አህመዲን ጀማልን ጨምሮ በእስር በሚገኙት ስምንት አባላት ፊርማ ደብዳቤው ለምክር ቤቱ እንደደረሰም ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በቀረበባቸው ክስ /ቤት ለጥቅምት 2 ቀን 2005 . ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ብሏል አድማስ በዘገባው

አዲስ አድማስ ከዶ/ ነጋሶ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቁ በጥቂቱ
ጋዜጣችሁ አሁንም እንደታገደ ነው?
አዎ እንደታገደ ነው፡፡ ባለፈው አርብ ልዩ እትም ለማሳተም ሰዎች ልከን ክፍያ ለመፈፀም ስንል የብርሃንና ሠላም ማርኬቲንግ ሃላፊው ክፍያውን አልቀበልም አለ፡፡ ምክንያቱን ሲጠየቅ፤ በቁጥር 1 ልዩ እትማችሁ ያሳተማችሁት ነገር ቅሬታ ስላስነሳብንና የዚህን አይነት ጋዜጣ እንዴት ታወጣላችሁ ስለተባልን አናትምም ሲል መለሰ፡፡ ልዩ እትሙ የጠ/ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ የተፃፉ በርካታ ሃሳቦችን የያዘ ነበር፡፡ ከሃሳቦቹ መካከልምለፍርድ ሳይቀርቡ መሞታቸውየሚልና እኔ የፃፍኩትህገመንግስቱና /ሚኒስትሩየመሳሰሉ በርካታ በሳል ጽሑፎች አካትቷል፡፡
ሆኖም ግን ጋዜጣችሁን በተመለከተ በስልክ ቅሬታ ስለቀረበባችሁ፣ ማኔጅመንቱ ተወያይቶበት ጋዜጣው እንዳይታተም ወስነናል መባሉ ተነገረን፡፡ እኛም በማግስቱ ሃላፊ ለማነጋገር ሔድን፡፡ እኔ፣ አቶ ግርማ ሠይፉ እና አቶ አስራት ጣሴ ነበርን፡፡ ማርኬቲንግ ማናጀሩ ለኛም ያንኑ ደገመልን፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል ብለን ስንጠይቀው ሃላፊዬን አነጋግሩ አለን፡፡ ዋናዋ ስላልነበረች ምክትሉ ቢሮ ገብተን ስናነጋግረው፣ ጋዜጣችን አይታተምም የተባለው ማርኬቲንግ ሃላፊው እንዳለው ሳይሆን በሌላ ምክንያት መሆኑን ሰማን፡፡እኛ አቅም የለንም ነው ያልነው፤ ለኦሮሚያ ክልል የትምህርት መጽሐፍትን ለማተም ጨረታ አሸንፈናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለብዙ ጊዜ ደንበኞች የሆኑ የተወሰኑ ጋዜጦች ስላሉ የእነሱን ብቻ እናትማለን እንጂ የናንተን ለማተም አቅም የለንም፡፡ ማኔጅመንቱ ተወያይቶ የደረሰበት ውሳኔ ይሄ ነው፤ እናንተ አዲስ ስለሆናችሁ የናንተን ላለማተም ወስነናልአለን፡፡ ይሄኔ በጣም ተናደድኩናበምን መስፈርት ነው የእኛን አናትምም ብላችሁ የሌሎችን የምታትሙት?” ብዬ ጠየቅሁት፡፡እነሱ የቆዩ ደንበኞች ስለሆኑ ነው፤ የፈለጋችሁትን ነገር አድርጉ፤ አናትምምብሎ ድርቅ አለብን፡፡ ሆኖም እኛ በደረሰን መረጃ መሠረት፤ እዚያ ማተምያ ቤት አንድ ሰው አለ፤ ጋዜጣው ሲመጣ ምን አይነት ይዘት እንዳለው ለደህንነቱ ሃላፊዎች ደውሎ የሚጠቁም፡፡ ከዛ ጉዳዩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን /ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ጋር ይደርሳል፤ አቶ ሽመልስ ደግሞ ለም/ሥራ አስኪያጁ ደውሎ እንዳይታተም ያዛል፡፡ እንደዚያ ነው የሆነው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዓይነት የአፈናና የዲሞክራሲ መብቶች እረገጣ ነው፡፡ በመንግስት ላይ ተቃዋሚ አስተያየትና ሃሳብ የሚሰነዝሩ ግለሰቦችንና የህትመት ውጤቶችን ልሳን መዝጋት ነው፡:
የጋዜጣችንን ሥርጭት 2500 ኮፒ ጀምረን ነበር 20ሺህ ኮፒ ያደረስነው፡፡ ግን ታገደ፡፡ ብርሃንና ሰላም አላትምም ሲለን እሱን ትተን ወደ ግል ማተምያ ድርጅቶች ሄደን ነበር፡፡ አንዳንዱ አቅም የለንም ይላል፤ ሌላው ደግሞ ለማተም ይቸግረናል ይለናል፡፡ ቦሌ ማተሚያ ሆራይዘን፣ ቅድስት ማርያም ማተምያ ቤቶች ሄደናል፤ ግን ለማሳተም አልቻልንም፡፡
ከጋዜጣውን መዘጋት ጋር ተያይዞ ፓርቲው ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚጠራ ገልጿል፡፡ የሠልፍ ፈቃድ ባታገኙም በሌላ መንገድ በመጥራት እናካሂዳለን ብላችኋል፡፡ እንዴት ነው ያሰባችሁት?
በመጀመሪያ የምናደርገው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት አላትምም ያለበትን ምክንያት በጽሑፍ እንዲገልጽልን ሲሆን ከዚያ በፊት ግን እንደገና አስቦበት እንዲያትምልን ደብዳቤ ልከናል፡፡ የመንግስትና የህዝብ ተቋም ስለሆነ መንግስትም ሃላፊነት አለበት፡፡ /ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጉዳዩ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ደብዳቤ ጽፈናል፡፡ በተጨማሪ እኔ በራሴ የቦርዱ ሊቀመንበር / ብስራት ጋሻው ጠና ጋር ደውዬ ልነግራቸው ሞክሬ ነበር፤ ሆኖም አሁን እሳቸው የብአዴን ሃላፊ ስለሆኑ ባህርዳር ናቸው፡፡ ጉዳዩን አላውቀውም፤ አጣርቼ መልስ እሠጣለሁ ብለውኛል፡፡ ያንን እየጠበቅሁ ነው፡፡ ስለዚህ ዝም ብለን አንቀመጥም፡፡ ከዛ በኋላ ነው ሠላማዊ ሠልፉን የምንጠራው፡፡ የሚያስፈልገውን ሁሉ እርምጃ እንወስዳለን፡፡ የታገደውን ጋዜጣ ለማስጀመር እስከመጨረሻው እንታገላለን፡፡
አዲሱ /ሚኒስትር ቢሆኑ ብለው የሚያስቡት ወይም የሚመርጡት ሰው አለ?
ተመርጫለሁ የሚለው ኢህአዴግ ነው፤ ከዛ አንፃር የአገሪቱን ችግሮች ጠንቅቆ የሚያውቅና የሚፈታ ሰው ቢሾም ነው የሚሻለው፡፡ ለዚህ ደግሞ ብቃት አላቸው ብዬ የማስባቸውና ድሮ ከማውቃቸው መካከል … (ስልጣን ከለቀቅሁ 11 አመታት ሊሆነኝ ነው) አቶ ግርማ ብሩ ቢሆኑ ብዬ 1993 . ሃሳብ አቅርቤ ነበር፡፡ አሁን እድሜም ጨምሯል፤ ሆኖም እሱ ቢሆን ችሎታ አለው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከህወሓት ብርሃኔ /ክርስቶስ ቢሆን እላለሁ እድሜው ባይገፋ ኖሮ ስዩም መስፍንም ጐበዝ ነው፡፡ ከብአዴን ደግሞ አቶ አዲሱ ለገሠ፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሰዎች አርጅተዋል፤ መተካት አለባቸው፡፡ አዲሶቹን ወጣቶች ሊያደርጓቸው ይችሉ እንደሆነ አላውቅም፡፡ እኔ የምሻው ግን የስርአት ለውጥ መጥቶ ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ይመራኛል የሚለውን ቢመርጥ ነው፡፡
የእግርዎ የጤንነት ሁኔታ እንዴት ነው?
አሁን በጣም ጤነኛ ነኝ፡፡ የእግሬን ጉዳይ በተመለከተየስኳር በሽታ አለብኝ፡፡ በሰውነቴ ውስጥ የተከማቸ ኮሌስትሮል አለ፡፡ ለብዙ አመታት ደግሞ ሲጋራ አጨስ ነበር፤ እነዚህ ነገሮች የእግር የደም ስርን የመዝጋት ሁኔታ ፈጥረው ነበርበሁለት እግሮቼ ላይ፡ እረጅም መንገድ መሄድ አልችልም ነበር፡፡ ስለዚህ ሳልታከም ብቆይ ኖሮ አደገኛ ችግር ማስከተሉ አይቀርም ነበር፡፡ አሁን የተዘጋውን የደም ሥር ከፍተውልኛል፡፡ በሙሉ ጤንነት ላይ ነኝ፡ አንዳንድ ሚዲያዎች አጋነውት ነው እንጂ እግሬ መቆረጥ ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡
ዕንቁ መጽሔት
የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ በፊት ገጹ ይዞ የወጣው እንቁ መጽሔት እንደሌሎቹ ሁሉ የተለያዩ የአመቱን ክስተቶች እና የእንቁን እትሞችን ማጠቃለያ ይዛ ወጥታለች፡፡ዋና ዋና ጽሁፎቹም
         ሰላም ወይስ ሁከት ምርጫችን
         መለስ የጀመረው ህልም ህያው ይሁንበያሬድ ጥበቡ
         መለስ ዜናዊ እና ያላለቀው የኢትዮጵያ ዘመናዊነት ፕሮጄክት – በፕሮፌሰር መሳይ ከበደ
         የመለስ ሞት እንቆቅልሾች እና ምቹ ጊዜያትበፕሮፌሰር ቴወድሮስ ኪሮስ
አዲሱ ዓመትን አስመልክቶ በእንቁ ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
 1. ትዳር ሳይኖር ልጅ አይኖርም ስለዚህ ትዳር መቅደም አለበት እላለሁ / ሃይሉ ሻወል ከእውቀት ከስልጣን ከሃብት ከትዳር እና ከልጅ የቱን ያስቀድማሉ ተብሎ ከእንቁ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ
 2. የትራፊክ አደጋ መጨመሩ መጥፎ ነው፡፡ሌላው የክቡር /ሚር መለስ ዜናዊ መሞት በጣም አስከፊ እና አስደንጋጭ ነው፡፡በርካታ መንገዶች ተሰርተዋል ይህ ደግሞ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ዋና ሳጅን አሰፋ መዝገቡ ስለአለፈው ዓመት መጥፎ እና ጥሩ ጉዳዮች ከእንቁ ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡት መልስ
 3. ለአገሬ በአዲሱ ዓመት የምመኘው ያለ አንድ ጥይት ተኩስ ማንኛውም የመንግስት ለውጥ በሰላማዊ መልኩ እንካሄድ እና ዴምክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን ነው፡፡ ማንኛውም ሽግግር በዴሞክራሲያዊ መልክ የሚከናወን ከሆነ መጪው ትውልድ ቢያንስ ከዚህ የሚወርሰው እዳ አይኖርም፡፡ ደራሲ አያልነህ ሙላት በአዲሱ ዓመት በአገርዎ ምን ቢደረግ መልካም ይሆናል ይላሉ ለሚለው የእንቁ ጥያቄ የሰጡት መልስ
ሌሎችም
         የመጀመሪያዋ የሴት ጄኔራል ተሾሙ ሪፓርተር ጋዜጣ
         በአዲሱ ዓመት ሁላችንም ከባድ የቤት ስራ አለብን / ኤፍሬም ይስሃቅ የሃገር ሽማግሌዎች ህብረት ሊቀመንበር ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት
         ከመንግስት ሆደ ሰፊነት ይጠበቃልአቶ ተመስገን ዘውዴ አንድነት ፓርቲ የውጪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት
         ሼህ አላሙዲን ተመራቂዎች ተማሪዎች ባገኙት የስራ መስክ አገራቸውን እንዲያገለግሉ መከሩ   ሰንደቅ ጋዜጣ
ርዕሰ አንቀጾች
         በአዲስ ዓመት አዲስ መንግስትዕንቁ መጽሔት
         ፍቅሬ ፍቅሬ አይብዛ አዲስ ጉዳይ መጽሔት
         አዲሱ ዓመት ጉድለቶቻችንን የምንሞላበት ዓመት ይሁንልንሰንደቅ ጋዜጣ
         የሚታመን ውሸት ለመዋሸት ከፈለግህ፤ የማይታመን እውነት አትናገር” – የጃፓኖች አባባልእያንዳንዷ ሩዝ ላይ የሚ በላት ሰው ስም ተፅፏል!” – የህንዶች አባባል አዲስ አድማስ ጋዜጣ
         ጉዞአችን የመቀጠል ብቻ ሳይሆን የመጨመርም ይሁን ሪፓርተር ጋዜጣ

የሳምቱ ጋዜጣና መጽሔቶች ከሰኞ እስከ ሰኞ – አሥራሁለት

(ከነሐሴ 14 እስክ ነሐሴ 21/2004)
ሳምንቱ በጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ዜና የተሞላ ነበር፡፡ የሞታቸው ዜና በቲቪ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ምላሾች የተስተናገዱ ሲሆን ጋዜጦች እና ህትመቶችም የዚሁ  አካላት ነበሩ፡፡ የፓትሪያርኩና የጠ/ሚኒስትሩ ህልፈት ዜናዎች እና የሃዘን መግለጫዎች የጋዜጣዎችን ገጾች ያጨናነቁ ነበሩ፡፡
አዲስ ዘመን ጠ/ሚኒስትሩን ሲያስታውስ

በህትመቱ የፓትሪያርኩን ዜና እረፍት ሲያነሳ የነበረው አዲስ ዘመን የጠ/ሚኒስትሩን ሞት በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም “ኢትዮጵያ ታላቁን መሪ በሞት ተነጠቀች ከትላንትና ጀምሮም ብሔራዊ ሃዘን ታውጇል” ብሏል፡፡ በፊት ገጹ ሙሉውን የጠ/ሚኒስትሩን ምስል የያዘው አዲስ ዘመን በተከታታይ ሳምንታዊ እትሞቹ ሙሉውን (ገጽ 3ትን ጨምሮ) ለመለስ ማስታወሻነት እንዲውል አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፕረስ አሰሴሸን፣ ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ እና ልማት ባንክ ሃዘናቸውን ለመግለጽ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ አዲስ ዘመን ሳምንቱን ሙሉ የተለያዩ አካላት የሃዘን መግለጫ ሲያስተናግድ ከርሞአል፡፡ “የህዳሴው መሪ” “ለትውልዱ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም” የሚሉ የተለያዩ ጽኁፎችን በፎቶ አጅቦ ያስተናገደው አዲስ ዘመን ምርጥ የጠ/ሚኒስትሩ ንግግሮችን አቅርቦአል፡፡የተወሰኑትን እነሆ፡-
 • የግሌም ሆነ የድርጅቴ አቋም ህገ በመንግስቱ ሊሻሻል የሚችል ምንም አንቀጽ የለውም የሚል ነው፡፡ መለስተኛ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ ይደረግ ቢባል ግን የሚያበሳጭ አይደለም፡፡
 • የመበታተን እና የመበጣጠስ አደጋ ጠፍቶ አሁን የፊዴራሊዝም ስርአት ሰፍኖ የብሄር የብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች መብትና እኩልነት መረጋገጡን ሳይ ደስታ ይሰማኛል፡፡በሃገራችን እየታየ ያለው የልማት እንቅስቃሴ እኛ ብቻ ሳይሆን በውጪ የሚገኙት መንግስታት ለስራም ሆነ ለስብሰባ ሲመጡ ከአመት አመት እየታየ ያለውን ለውጥ በማየት ይገርማቸዋል፡፡
 • ኢትዮጲያ ፌደራሊዝም ስርአቱን የጀመረችው ከቅርብ አመታት ወዲህ በመሆኑ የፊደራል ስርአትን አስቀድመው ከጀመሩ የምትማረው ብዙ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ኢትዮጲያ በስርአቱ ዙሪያ ለተቀሩት ሃገራት የሚተርፍ መልካም ተሞክሮ ያላት ሃገር ሆናለች፡፡
አዲስ ዘመን ከጠ/ሚኒስትሩ ሞት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባለው እትሙ በገጽ ሶስት እትሙ ማህበራዊ ድህረ ገጽ መረጃዎች ተአማኒነት እና አጠቃቀማቸው በሚል ርእስ የማህበራዊ ድህረ ገጾች መረጃዎች ለአመኔታ እንደማይበቁ የሚዳስስ ጽሁፍም አቅርቦ ነበር፡፡

ፍኖተ ነፃነት በልዩ እትም

አርብ እለት በልዩ እትም የወጣችው ፍኖተ ነጻነት በአብዛኛው ከጠ/ሚኒስተሩ ጋር የተያያዙ ዜናዎችን ይዛ ገበያ ላይ ውላለች፡፡የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን መታሰር በፊት ገጽ ላይ የተዘገበ ሲሆን የአንድነት ፓርቲ የሃዘን መግለጫም ተሳካቷል፡፡ የመለስ ዜናዊ ሁለቱ ገጾች በሚል ሰፊ ፍኖተ ነፃነት አራት የተለያዩ ሰፋፊ ጽሑፎችን አስነብባለች፡፡የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
 • መለስ ዜናዊ እና ሕገ መንግስቱ
 • አወዛጋቢው የመለስ ‹‹ጀግንነት››
 • የመለስ ዜናዊ ቅይጥ ትዝታዎች (ከዞን ዘጠኝ ተከታታይ ብሎጎች ለጋዜጣ እንዲመች ሆኖ የተዘጋጀ)
 • ከጠ/ሚኒስተር መለስ ሞት ጋር በተያያዘ የአንድነት አባላት እየታሰሩ ነው
ሪፓርተር በረቡዕ እና በእሁድ እትሞቹ
ሙሉ እረቡ እትሙን በአቶ መለስ ሞት ዙሪያ ያደረገው ሪፓርተር በፊት ገጹ የጠ/ሚኒስትሩ ፎቶ ይዞ የወጣ ሲሆን በቁጥራቸው በዛ ያሉ የሙሉ ገጽ የሃዘን መግለጫዎችን ሪፓርተር አስተናግዷል፡፡ በእሁድ እትሙ ደግሞ ሳያርፍ ያለፈው መለስ በሚለው ሰፋ ያለ ፅሁፍ ሪፖርተር ያልተሰሙ የመለስ ታሪኮች በሚል ርእስ ስር የሚከተለውን አስነብቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በሽግግሩ ዘመን በሰጡት አንድ መግለጫ ላይ ባንዲራ ጨርቅ መሆኑን መግለጻቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ ንግግራቸውም በርካቶች መለስ የአገር ፍቅር እንደሌላቸውና ባንዲራውን እንዳዋደቁት ቆጥረዋቸው ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ስለዚህ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ተጠይቀው፣ ይቀርፃቸው የነበረውን ካሜራ አስጠፍተው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ ይህ በሁሉም ሰው የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ባንዲራ ጨርቅ ሆኖ ሳለ መለስ ሲለው ጨርቅ አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ብለዋል፡፡  
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ብዙ ጊዜ ሲስቁ ስለማይታዩ፣ ለምን? እንደማይስቁ ተጠይቀውለምን እስቃለሁበማለት ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል፡፡እኔ ቢሮ ውስጥ ሆኜ በየቀኑ የማነባቸው ደብዳቤዎች በሰቆቃ የተሞሉ ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት በደል ደርሶብኛል፣ ፍትሕ አጣሁ፣ ያሰርካቸውን ሰዎች ፍታ፣ የሚሉ በርካታ ይህን መሰል ደብዳቤዎች ይደርሱኛል፡፡ አብዛኞቹም ሁሉን ነገር የማደርገው እኔ እንደሆንኩ የሚገልጹ ደብዳቤዎች ናቸው፡፡ በአገሪቷና በአካባቢው ያሉትን በርካታ ችግሮች ለመፍታት በየጊዜው እታገላለሁ፡፡ ታዲያ ምን የሚያስቅ ነገር ኖሮ ነው የምስቀው፤ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ
ሚኒስትር መለስ በሕይወታቸው አሳዛኝ ስለሚሏቸው ገጠመኝ ተጠይቀው ሦስት ነገሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡የመጀመሪያው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የቀረበለትን የሰላም ሐሳብ አልቀበልም፣ አሻፈረኝ በማለቱ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የተሰው ዜጐች ሁሌም ያሳዝኑኛል፡፡ ሁለተኛው በምርጫ 97 ጊዜ በተፈጠረው ግርግር ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎች ናቸው፡፡ በወቅቱ እኔ እንደ ግለሰብ ብሞት እንኳን ምንም አይሰማኝም፡፡ ሆኖም እኔ የአገር መሪ እንደመሆኔ መጠን በሰላም ሳይሆን በእንደዚያ ዓይነት ግርግር ሥልጣን ብለቅ አገሪቱ ወደማትወጣው አዘቅት ውስጥ ልትገባ ትችል ነበር፡፡ በመሆኑም ውሳኔ ቢያሳዝነኝም ማንም በእኔ ቦታ ቢሆን የሚያደርገው ነገር ነበር፡፡ ሦስተኛ የሚያሳዝነኝ ጉዳይ የሕክምና ትምህርቴን ስከታተል አውቀው የነበረው አንድ ሻይ ቤት ከሰላሳ ዓመት በኋላ ተመልክቼው ምንም ዓይነት ለውጥ ባለማየቴ በጣም አዝኛለሁ፡፡ አገሪቱን ለመለወጥ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተረድቼ የበለጠ ለመሥራት ወስኛለሁ፤ብለዋል፡፡

ሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ቋሚ አምዶቹን በሙሉ በማጠፍ ሙሉውን መጽሄቱን አቶ መለስን የተመለከቱ የተለያዩ ጽሁፎችን አስተናግዷል፡፡ በጥቁር የሽፋን ገጽ አቶ መለስን ፎቶ ይዞ የወጣው አዲስ ጉዳይ በመጨረሻ ገጹ ብቻ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ማናቸው የሚል አንድ ገጽ ጽሑፍ ከማስነበቡ ውጪ ሙሉውን አቶ መለስን በሚዘክሩ ጽሁፎች ነበር እሁድ እለት ገበያ ላይ የዋለው፡፡

ሀተታ ወ መለስ – የአቶ መለስን ታሪክ የዳሰሳ ጽሑፍ
ስለመለስ ከአራቱም ማእዘናት – የአቶ መለስ ሞት እና የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ዳሰሳ ጽሁፍ ሲሆን አብዛኛውን ጠንካራ ጎናቸውን ያወሱ ሚዲያዎችን ሪፓርት አካተዋል፡፡
የመለስን ጉዳይ መደበቅ ደግ ነበር ፓርቲውስ ከዚህ በኋላ አመኔታ ያጣበታል – የአቶ መለስን ህመም በተመለከተ ፓርቲው ያሳየውን ድብቅ ባህሪያ በዚህ ጽሑፍ በስሱ ተተችቶአል፡፡ በተጨማሪም፡-
·         የጥምረት መንግስት ቢቋቋም የተሻለ ነው – አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
·         አቶ መለስን የማገኛቸው ፓርላማ ውስጥ ነበር – ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (የአንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር)
·         መልካም አስተዳደር ሊኖር የሚችልባቸው መንዶች ቢመቻቹ ጥሩ ነው – የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ (የመድረክ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ)
·         አትሌቱን በመሸኘት እና በመቀበል ከፍተኛ የማበረታታት ስራ ሰርተዋል – አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ
 

አዲስ አድማስ በፊት ገጹን ሩብ የሚሸፍን የጠ/ሚኒስተሩን ፎቶግራፍ ይዞ ለንባብ የበቃ ሲሆን ለፓትያርኩ ቀብር ከሌሎች የህትመት ውጤቶች በተሻለ ሽፋን ሰጥቷል፡፡

ጋዜጦች እና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ (አሥራአንድ)

(ከነሐሴ 7 እስከ ነሐሴ 14፤ 2004)
የኛ ፕሬስ ጋዜጣ ሲፒጄ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጅ የሱፍ ጌታቸው ይፈታ ማለቱን እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ድንጋይ ይጥረቡ መባሉ እንዳሳዘናቸው ዘግቧል፡፡
ፍኖተ ነፃነት በቃለ መጠይቅ አምዱ (/) ክቡር ገናን ይዞ ወጥቷል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ተግዳሮቶች እና እንቅስቃሴዎች አወያይቶዋቸዋል፡፡ አቶ ክቡር ገናም ‹አንድ ህዝብ ዝም ብሎ ተኝቶ ሲረገጥ አይውልም፤ ድንገት ይነሳል› ማለታቸውን በፊት ገጹ አስፍሯል፡፡
በዚህ ሳምንት አቶ ክቡር ገና ከሰንደቅ ጋዜጣም ጋር ቆይታ ነበራቸው፡፡ በተመሳሳይ የሲቪል ማህበራት ጉዳዮች ዙሪያ ለሰንደቅ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል፡፡
የጠ/ መለስ ነገር
ከፓትሪያርኩ ዜና እረፍት በፊት የወጡት ጋዜጦች  ሁሉም በፊት ገጻቸው የጠ/ሚኒስትሩን መጥፋት ሽፋን ሰጥተውታል፡፡
የኛ ፕሬስ በፊት ገጹ የጠ/ሚኒስተር መለስ ጉዳይ እያወዛገበ ነው ሲል የተለያዩ ተቋማት ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጡትን ዘገባ አስነብቧል፡፡

መለስ ወደ ስልጣናቸው አይመለሱም ዘጋርዲያን
ከአዲስ አመት በፊት ስራቸውን ይጀምራሉ አቶ በረከት
የጠ/ሚሩ የግል ተተኪ አለመኖር አሳስቦናል የኬንያው /ሚኒስተር
ከታቦ ኢንቤኪ ጋር በጉዳዩ እተማከሩ ነው ፋይናንሺያል ታይምስ
ከአሁኑ ስልጣን ለመያዝ እርስበርስ እየተሻኮቱ ነው ሀይሉ ሻውል

ሰንደቅ በፊት ገጹ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋጋሪነት ቀጥሏል ያለው ሰንደቅ ድንገት መሰወራቸው ግብጾችን አሳስቧል ሲል የአሜሪካንን ዝምታ አሳሳቢነት እና የእንግሊዝ ጋዜጦችን ተደጋጋሚ የዜና ሽፋን በጠ/ሚው የትካዜ ፎቶግራፍ አጅቦ አውጥቶአል፡፡
ፍኖተ ነፃነት በበኩሉ አቶ መለስ ከያራ የማዳበሪያ አምራች ፋውንዴሽን ያገኙት ሽልማት በሙስና የተገኘ ነው መባሉን በፊት ገጹ አስፍሯል፡፡ በተያያዘ ዜና የአቶ መለስ ጉዳይ አለየለትም በማለት የአቶ መለስን አለመኖር አስመልክቶ የተለያ አካላትን ሃሳብ ይዞ ወጥቷል፡፡
የፓትሪያርኩ ህልፈት
አዲስ ጉዳይ እና እንቁ መጽሄቶች በፊት ገጻቸው የፓትሪያርኩን ፎቶግራፍ ይዘው የወጡ ሲሆን አዲስ ጉዳይ በፓትሪያርኩ ሕይወት ላይ ያተኮረ ረዥም ጽሁፍ አስነብቧል፡፡ እንቁ በበኩሉ የሞታቸው ምክንያት ከእግራቸው ህመም ጋር የተያያዘ ነው ሲል አዲስ አድማስ ጋዜጣ ደግሞ የህልፈታቸው ምክንያት ስኳር በሽታ መሆኑን ገልጧል፡፡
ሌላም፣ ሌላም
 • ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ተጎጂዎች ቁጥር አሻቀበ ሰንደቅ እና አዲስ አድማስ
 • የኢትዮጵያ መንግስት የትጥቅ ትግል ከሚያደርግ ድርጅት ጋር ዛሬ ይፈራረማል/ተፈራረመ ሰንደቅ እና አዲስ አድማስ
 • ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው ፍኖተ ነፃነት
 • የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲለቀቁ ሙስሊሞች ጠየቁ ፍኖተ ነፃነት
 • ከሚስቱ የተጣላው አትሌት ውሎው ሺሻ ቤት ሆኖዋል፡፡ ፊቱ ላይ ተስፋ መቁረጥ እና ራስን መጥላት ታይቶበታል የኛ ፕሬስ ተባራሪ ወሬ
 • የወረዳው ስራ አስፈጻሚ ስልጣናቸውን ለሚስታቸው አደራ ሰጡ የኛ ፕሬስ ተባራሪ ወሬ
 • ሚኒስትር ጂነዲን ማንን ምይቅርታ አልጠይቅም አሉቆንጆ መጽሄት
ርእሰ አንቀጾች
 • ከአፍንጫ አርቆ ማሰብ የተሳነው አትሌቲክስ ፊዴሬሽን የኛ ፕሬስ
 • በጥቂት አትሌቶች ዋጋ የተሸፈነ አስተዳደር ሊፈርስ ይገባዋል ሰንደቅ
 • ኢህአዴግ ነጻውን ፕሬስ ለማጥፋት የጀመረውን ዘመቻ ባስቸኳይ ያቁም ፍኖተ ነፃነት
 • ሜዳው ላይ እንተያይ!” አትሌት ጥሩዬ አዲስ አድማስ
የሳምንቱ ምርጥ ንግግር
‹‹አስራ አምስት አመት የሚያሳስረኝ ከሆነማ ይህች ሃገር የኔ አይደለችም ማለት ነው፡፡››
(ሳምሶን ማሞ
ለየኛ ፕሬስ ጋዜጣ በክሱ ዙሪያ ከተናገረው)

ጋዜጦች እና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – አሥር

(ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 6፣ 2004)
Capitalጋዜጣ “Golden Girls” በሚል ርዕስ በፊት ገጹ ላይ ባስነበበው ዜና ኤድናሞል ላይ በተሰቀለው ስክሪን የዓርብ ዕለቱን ሩጫ ሲመለከቱ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መሰረት ደፋር በሚበሩት እግሮቿ የመጨረሻውን መስመር ስትረግጥ በሐሴት እንደተጥለቀለቁ ጽፏል፡፡ Fortune ጋዜጣም በተመሳሳይ ዜና ኢትዮጵያውያን በሙሉ ወርቁ የኢትዮጵያ እንደሆነ በርግጠኝነት ተማምነው፣ ሲጠብቁ የነበሩት ከመሰረት እና ከጥሩነሽ ማን ያመጣዋል በሚል እንደሆነ ዘግቧል፡፡
** ** **
‹‹ዳግም የተወለደችው መሠረት ደፋር›› የሚል ዜና ያስነበበን ደግሞ ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡ ‹‹“የአምስት ዓመት ልጄን በስልክ አግኝቻት ነበር፡፡ እርሷም ‹ማሚ እባክሽ የወርቅ ሜዳሊያውያን አሸንፊ› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ ቃል ገብቼላት ነበር፤ ቃሏን በመጠበቄ ኮርቻለሁ በቃ፣ ዛሬ እንደገና የተወለድሁ ያህል ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፤” …››
** ** **
‹‹…አቃቤ ሕግ በተመስገን ደሳለኝ ላይ ሦስት ክሶችን የመሰረተ ሲሆን ፥ ክሶቹም 1ኛ ወጣቶች በአገሪቱ መንግስትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርአቱ ላይ እንዲያምጹ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር፣ 2ኛ የሀገሪቱን መንግስት ስም ማጥፋት እና የሀሰት ውንጀላ እንዲሁም 3ኛ የሀሰት ወሬዎችን በማውራት ሕዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ የሚሉ ናቸው። …››

 ** ** **
‹‹…በተለይ የአገሪቱ ትልቁ የንግድ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞቹ ሌተር ኦፍ ክሬዲት መክፈት ሲያቆም፣ ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአገሪቱ የሦስት ወራት የውጪ ንግድ ከመቀነሱ ጋር በተያያዘ ነው የሚል መልስ እየሰጠ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ …››
** ** **
አዲስጉዳይ መጽሔት ‹‹ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብኛል አለ›› የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ ‹‹በዜድ ፕሬስ ፕሮሞሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሥር እየታተመ በየሳምንቱ ለንባብ ይቀርብ የነበረው ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ንግድ ፈቃድ ባለማደስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ከህትመት ውጪ እንደምትሆን የኢትዮቻናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ለአዲስጉዳይ ተናግሯል፡፡…››
** ** **
ሌላም፣ ሌላም
ርዕሰ አንቀጾች
የሳምንቱ ጥቅስ

‹‹15 አመት እንደምታሰር እያሰብኩ ጋዜጣ ልሠራ አልችልም›› – ሳምሶን ማሞ (ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጠው ቃለ ምልልስ)

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – ዘጠኝ

(ከሐምሌ 23 እስከ 29፣ 2004)
አቶ ጁነዲን ሳዶ ኢትዮ-ቻናል እና ለሰንደቅ ጋዜጣ ያወሩብኝ ‹‹ከሰሞ የሐይማኖት ችግሮ ጋር በፍፁም የማይያያዝና ተጣሞ የቀረበ ነው›› የሚል ደብዳቤ ለጋዜጦቹ ልከዋል፡፡ በደብዳቤያቸው ባለቤታቸው ይዘውት ተገኙ የተባለው ገንዘብ የሚኒስትሩ እናት ሲሞቱ በተናዘዙት መሰረት እንደግለሰብ ከሳዑዲ መንግስት ለማሰሪያ ድጋፍ ጠይቀው ላስጨረሱት መስጊድ የሰደቃ ፕሮግራም የታሰበ ነበር፡፡
** ** **
Capital ጋዜጣ “Hard currency shortage” በሚል ርዕስ ምንጮቹን ጠቅሶ ባስነበበው ዜና በተለይም የንግድ ሰዎች የውጭ ንግዳቸውን የሚያካሂዱበት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠማቸው አትቷል፡፡
** ** **
Fortune ጋዜጣም “Saudi Star begins to spit the advance for Abebo” የሚል ዜና በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል፡፡ በዝርዝሩም ሳውዲ ስታር Abeboን ለመግዛት ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መክፈል ከሚጠበቅበት 40.5 ሚሊዮን ብር የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ 32 ሚሊዮን ብሩን ጁላይ 18 ከፍሏል፡፡ Abebo በጋምቤላ 3000 ሄክታር መሬት ያለው ሲሆን 65000 ሜትር ስኩዌሩ የጥጥ ተክል ልማት ጀምሯል፡፡
** ** **
ሪፖርተር ጋዜጣ በእሁድ እትሙ ‹‹ጋምቤላ የመሸገውን የደቡብ ሱዳን አማፂ ኃይል ለመቆጣጠር ኢትዮጵያ ጦ አሰማራች›› ይላል፡፡ በዝርዝሩም ‹‹… አማፂ ቡድኑ ሰርጎ ገብቷል የተባለው በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ሲሆን፣ ቡድኑ የደቡብ ሱዳንን መንግሥት ለመውጋት የጋምቤላን ወጣቶች  እየመለመለ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
ይህንን አማፂ ቡድን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለደቡብ ሱዳን መንግሥት ለማስረከብ  የጋምቤላ ክልል ከፌደራል መንግሥት ጋር በጋራ  እየሠራ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ …››
በተጨማሪም ሪፖርተር ‹‹የኢትዮጵያ ድል በንግሥቷ ወርቅ ተጀመረ›› ይለናል፡፡

ተመስገን ደሳለኝ ስለ ፍትሕ ጋዜጣ መታገድ
የፍትሕ ጋዜጣ መታገድን አስመልክቶ፣ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አቶ ተመስገን ደሳለኝ ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር ቃለምልልሶችን አድርጓል፣
 • እኛ ሥራችንን ጨርሰናል፤ ከዚህ በኋላ ኃላፊነቱን መወጣት ያለበት ሕዝቡ ነው!ፍኖተ ነፃነት
  ‹‹… እስከዛሬ 140 ክሶ በላይ ተከስሻለሁ፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ፀረ ሽብር ግብረኃይል ጠርተው ደብድበውኛል፣ በቪዲዮ ቀርፀውኛል፣ ከዚህ በኋላ በሚል ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውኛል፣ ይህን እስከዛሬ አልተናገርኩም፣….››
 • ጥያቄያችን መልስ እስኪያገኝ ድረስ ማንኛውንም ሕጋዊና ሰላማዊ መስመሮችን በመጠቀም እንታገላለን –  ዕንቁ መጽሔት
 • ፍትህ ጋዜጣ በመጪው አርብ ገበያ ላይ ትውላለች – አዲስጉዳይ መጽሔት
 • ጋዜጣ ላይ ብንጽፍም ባንጽፍም ስጋቱ አለአዲስ አድማስ
 • ፍትህ ጋዜጣ ወደህትመት እንዲመለስ መድረክ ጠየቀሪፖርተር
ሌላም፣ ሌላም
ርዕሰ አንቀጾች

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – ስምንት

(ከሐምሌ 16 እስከ ሐምሌ 22፤ 2004)
Capital ጋዜጣ ‹‹Counting 20›› በሚል ርዕስ ባስነበበው የሽፋን ገጽ ታሪክ ላይ አቡነ ጳውሎስ የጵጵስና ‹‹ስልጣን›› የያዙበትን 20ኛ ዓመት አከባበር ይተርካል፡፡ በዓሉ በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲከበር የተለያዩ ሃይማኖት አባቶች፣ የቢዝነስ ሰዎች እና የፖለቲካ ሰዎች ተገኝተዋል – ከነርሱም ውስጥ ቴዎድሮስ አድሃኖም እና ኃ/ማርያም ደሳለኝ ይገኙበታል፡፡
** ** **
Fortune  ጋዜጣ “Fineline” በተሰኘው የሚስጥር አምዱ ላይ ሰማሁ ብሎ ካንሾካሾካቸው ምስጢሮቹ ውስጥ መለስ ጁላይ 20 አዲስ አበባ ስለመግባታቸው፣ በርሳቸው ስም ተፈርመው የወጡ ዶክመንቶች ስለመኖራቸው እና እረፍታቸው ለአንድ ሳምንት ያህል የሚቀጥል መሆኑን ተናግሯል፡፡
** ** **
አዲስጉዳይ መጽሔት ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ ከፖለቲካ ሳይንስና የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ይዞ ወጥቷል፡፡ ከቃለምልልሱ ውስጥ የተቀነጨበውን እነሆ፡-

‹‹…በእኔ አስተያየት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሉ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ድምጻቸው ጠፍቷል፡፡ አይታዩም፡፡ ግን አለን ይላሉ፡፡››
‹‹…እኛን ከሶቪየት ህብረትና ከዩጎዝላቪያ ጋር ማወዳደር ግድ ይሆንብኛል፡፡ በሁለቱም አገሮች የፌዴራል ስርዓቱ የተሳሰረው ከአውራው ፓርቲና ከአንድ ግለሰብ መሪ አውራነት ጋር ነበር፡፡ ሁሉቱም (ፓርቲውም አውራ መሪውም) ከስልጣን ሲወገዱ በሁለቱም አገሮች ፌዴሬሽኑ ፈራረሰ፡፡…››
‹‹…ሙስና ለእኔ ዋናው በሽታ ሳይሆን የበሽታው አንድ ምልክት ነው፡፡ ችግሩ (በሽታው) የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር መምከን፣ ስልጣን በአንድ ፓርቲ መዳፍ ውስጥ መግባት ነው፡፡››
‹‹…ህዝቡ በፍርሃትና በተለያዩ ምክንያቶች ዝም ሲል እንደተስማማ አድርጎ መቁጠር ስህተት ነው፡፡ ከሚጮህ ዝም ያለ ሕዝብ አደገኛ ነው፡፡…››
ሌላም ሌላም
ርዕሰ አንቀጾች
የሳምንቱ ጥቅስ
       ‹‹አጠገቡ ካሉ ሰዎች እንደምሰማው ጤንነቱ በፍጥነት እየተሻሻለ ነው፡፡››
አቦይ ስብሓት ነጋ ለአዲስ አድማስ 
ጋዜጣ ስለመለስ ጤንነት ከተናገሩት!

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – ሰባት

(ከሐምሌ 9፣ 2004 እስከ ሐምሌ 15፣ 2004)
ሪፖርተር  በረቡዕ ዕትሙ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ተሰማ›› የሚል ዜና አስነብቦናል፡፡ ‹‹በ21 ዓመታት የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤንነት ችግር በ19ኛው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ያልተሳተፉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የውጭ ሕክምና ክትትላቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ …››
** ** **
‹‹የሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ገንዘብ ይዘው ሲወጡ ተያዙ›› የሚል ዜና ያስነበበን ሰንደቅ ጋዜጣ ነበር፡፡ ‹‹…[ወ/ሮ ሃቢባ ሐምሌ 10፣ 2004] …ግምቱ ከሃምሳ ሺ እስከ መቶ ሺ ብር የሚገመት የታሰረ ገንዘብ እና በዓረብኛ የተጻፉ መጽሐፍት ይዘው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡…››
** ** **
ፍትህ ጋዜጣ ከጋዜጦች ሁሉ ተለይቶ በዚህ ሳምንት አልወጣም፡፡ የጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ችግሩ ከአሳታሚው አለመሆኑን እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ ‹‹ዛሬ አርብ ነው፤ ፍትህ ግን አንባቢያን ጋር አልደረሰችም፡፡ በእርግጥ ትላንት የጋዜጣው የሽያጭ ሰራተኛ ብርሃና ሰላም ማተሚያ ቤት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ተገኝቶ ለ30 ሺህ ኮፒ 80385 (ሰማኒያ ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ አምስት) ብር ከፍሏል፡፡ የፍትህ ህትመት ክትትልም እኩለ ሌሊት ላይ ማተሚያ ቤት ቢደርስም የህትመት ክፍል ሀላፊው ‹‹ፍትህን እንዳታትሙ ተብለናል›› በሚል ጋዜጣዋ ሳትታተም አደረች፡፡

‹‹በዛሬው ዕለትም የማተሚያ ቤቱን ምክንያት ለማወቅ ወደ ብርሃና ሰላም ከጥቂት ባልደረቦቼ ጋር ሄድኩኝ፡፡ ሆኖም ምክትል ስራ አስኪያጁ ከሌሎች የድርጅቱ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ስብሰባ ቢጤ አድርገን እንድንወያይ ጠየቁን፡፡ ተወያየን፡፡ በፊት ገፅ ላይ ያለ አንድ ዜና ማንሳት እንዳለብን ከመጠቆም ባለፈ እዚህ ጋር የማልገልፀውን እጅግ አሰፋሪ የሆነ መደራደሪያ አቀረቡ፡፡ እኛም የሀገሪቱን ህግ ጠቅሰን ተከራከርን፡፡ ያለስምምነት ከሰዓት 8፡30 ላይ ተወያይተው ውሳኒያቸውን ሊያሳውቁን በቀጠሮ ተለያየን፡፡ ቀጠሮውንም ተቀብለን ስንወጣ ከተሰበሰብንበት የም/ስራ አስኪያጁ ትንሿ አዳራሽ በር ላይ የፍትህ ሚንስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ዓቃቢ ህግ ተቀምጠው አየናቸው፡፡ በር ላይ ደግሞ በመልክ የምናውቃቸው በርከት ያሉ የፀጥታ ሰራተኞች እንደተለመደው አጀቡን፡፡ ይህንን በዕምሮአችን ይዘን ወደቢሮአችን ተመለስን፡፡ ሰዓቱ እስኪደርስ ለምሳ ወጣን፡፡ ምሳ ለመብላትም ካሳንችስ አካባቢ አንድ ምግብ ቤት ገባን፡፡ ተመግበን ስንወጣም አደባባይ ላይ የመኪናዬ ጎማዎች ፈንድተው አገኘን፡፡ ከዛም ከሰዓት በኋላ በቀጠሮአችን ሰአት ም/ስራአስኪያጁ ቢሮ ስንደርስ ‹‹እንዲታተም ተፈቅዷል›› የሚል መልስ ተሰጠን፤ እናም ጋዜጣዋ አሁን እየታተመች ነው፡፡ ነገ ጠዋት ትወጣለች ብለንም እንጠብቃለን፡፡››
ተመስገን እንዲህ ቢልም ፍትህ ጋዜጣ ቅዳሜም ገበያ ላይ አልዋለም፡፡ ይህንንም ተከትሎ ተመስገን ይህንን ጽሁፍና የደብዳቤ ኮፒ አያይዟል፡፡ ‹‹በትላንትናው ዕለት ለስርጭት መብቃት የነበረባት ፍትህ የጠቅላይ ሚንስትሩን መታተም ተከትሎ በተፈጠረው የስልጣን ትግል እያሸነፈ በመጣው አክራሪ ሀይል ተስተጓጉላ የነበረ ቢሆንም በማግስቱ እንድትታተም ተፈቅዷል ተብሎ ታተመች፡፡ ትላንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይም ሙሉ በሙሉ ታትማም አለቀች፡፡ ነገር ግን አንባቢያን እጅ ልትደርስ አልቻለችም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ (በዛው ኃይል ትዕዛዛ ይመስለኛል) በአቃቢ ህግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ ‹‹ለሀገር ደህንንት የሚያሰጋ ዘገባ በጋዜጣው ላይ መታተሙ መረጃ ስለደረሰን እንዲታገድ ወስነናል›› በሚል የተፈረመ የዕግድ ደብዳቤ ማተሚያ ቤቱ እንደደረሰው ገለፀልን፡፡ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ሰዓት 30 ሺህ የፍትህ ጋዜጣ እትም በብርሃና ሰላም ማተሚያ ቤት ተቆልፎበት ይገኛል፡፡
…እንዴት ነው ነገሩ? ‹‹ትሻልን ፈትቼ ትብስን አገባሁ›› እየሆነ ነው? ይህ ሁኔታ ወደስልጣን እየመጣ ያለው ሀይል የባሰ እንደሆነ ምልክት እያሳየስ ይሆን? ለማንኛውም መጨረሻውን አይተን የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን፡፡ (ማተሚያ ቤቱ ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል የላከውን ደብዳቤ እዚህ ይመልከቱ)››
— — —
በተያያዘ ዜና፣ ‹አልቁዱስ› የተባለው የሙስሊሞች ጋዜጣ የሚታተምበት ማተሚያ ቤት በመታሸጉ ‹ዘገነርስ› የተባለው የአርብ ስፖርት ጋዜጣም ሳይታተም ቀርቷል፡፡ አርብ ዕለት ይወጣ የነበረው ‹ነጋ ድራስ›ም በዚህ ሳምንት ገበያ ላይ አልዋለም፡፡
** ** **
አዲስ አድማስ ጋዜጣ በፊ ገጹ ‹‹አዲሱ የመንግስት ቤቶች የመሸጫ ዋጋ ይፋ ሆነ›› ይላል፡፡ አነስተኛ ገቢ ያቸው ዜጎች በ26ሺ ብር የቤት ባቤት ይሆናሉ፣ በቀጣዩ ዓመት 10ሺ ቤቶች ይገነባሉ፡፡ ‹‹… በነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለመታቀፍ የቤቱን ሽያጭ ዋጋ 40 በመቶ በመቆጠብ 60 በመቶውን ከባንክ በሚገኝ ብድር የቤት ባለቤት ለመሆን እንደሚቻልም ሚኒስትሩ ተናግረዋል…››
** ** **
‹‹Meles Back in Town›› (መለስ ወደከተማ ተመልሰዋል) የሚል የፊት ገጽ ዜና ያስነበበን Fortune ነው፡፡ በዝርዝሩም፣ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ በተሰጠ ማግስት (አርብ ዕለት) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደአዲስ አበባ መግባታቸውንና የጤንነታቸውም ሁኔታ በጣም እየተሻሻለ መምጣቱን ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ ዘግቧል፡፡
ሌላም፣ ሌላም
 • ኢትዮጵያን አይዶል ክብሩን ያጣ ፕሮግራም ነው፣ ባለሙያዎቹ ምንም ነገር የማያውቁ ናቸው ተብያለሁ – አቶ ይስሐቅ ጌቱ (የኛ ፕሬስ)
 • የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መራራ የዕድገት ሽሙጦች፤ 140 ሺ ቶን ጫት በየዓመቱ ይቃማል፣ 7 ቢሊዮን ብር ለጫት ፍጆታ ይውላል – መሰናዘሪያ
 • አንድነት በሰላማዊ ትግል ለሚመጣ ችግር ኃላፊነቱን እወስዳለሁ አለ፤ ለጠ/ሚስትሩ መልካም ጤንነት ተመኝቷል፡፡ – አዲስ አድማስ
 • ከኮሌስትሮል ነፃ የሚባለው የፓልም ዘይት ነፍሰገዳይ መሆኑን ያውቃሉ? – ኢትዮ ቻናል
 • ንግድ ባንክ የሚድሮክ የሚድሮክ ኩባንያዎችን በ942 ሚሊዮን ብር ብድር አንበሸበሸሪፖርተር (እሁድ)
ርዕሰ አንቀጾች

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – ስድስት

(ከሐምሌ 2 እሰከ ሐምሌ 8፣ 2004 – Find the original at http://zone9ethio.blogspot.ca/)
ሰለሞን ስዩም ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ላይ ‹‹የኢሕአዴግ ጥንካሬ ምን ያክል ነው?›› የሚል ርዕስ በሰጠው ሐተታው፣ ‹‹…እንቁላል በሁለቱ ጫፍና ጫፍ (በዋልታዎቹ) በመዳፍህ መካከል አይሰበርም፤ በወገቡ በኩል በመዳፎችህ መካከል ከተጫንከው ግን ፍርክሽ ይላል፡፡…›› የሚል ቀላል መልስ ሰጥቷል፡፡
** ** **
ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ እትሙ ‹‹አቶ ጁነዲን ሳዶ ስለ ኮብል ስቶን ያደረጉት ንግግር ተቃውሞ ገጠመው ›› በሚል ርዕስ ባሰፈረው ዜና ላይ የሚከተለውን አካትቷል ‹‹የቀድሞው ድምቀቱና ውበቱ በተለየው የዘንድሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ሥነ ሥርዓት ላይ፣ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ በንግግራቸው ስለ ኮብል ስቶን በማንሳታቸው ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት ገጠማቸው፡፡ አቶ ጁነዲን ባለፈው ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግራቸውን ሲጀምሩ በአድናቆት ጭብጨባና በፉጨት ቢታጀቡም፣ ድንገት የንግግራቸውን አቅጣጫ ወደ ኮብል ስቶን በማዞራቸው ነበር ሳይታሰብ ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት፣ ጉርምርምታና ፉጨት ከተመራቂዎቹ የተሰማው፡፡…››
** ** **
ፍትህ ጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ የፕሮፓጋንዳ ስምምነት አለን በሚል የአልሻባብ ሰው ነኝ ከሚል የተጻፈለት ኢሜይል ተከታይ አሁንም በሌላ ሰው ተላከለት፡፡

‹‹ሰላም ተመስገን፣
ከአልሻባብ ልዑክ ጋር ችግር ውስጥ ባትገባ የተሻለ ነው፡፡ ምናልባት ያልተፈታ ችግር ካለ ለሚመለከተው ክፍል ብትተወው ይሻላል፡፡ ካንተ የሚጠበቀው በኢትዮጵያ መንግሥት እና ኢኮኖሚው ላይ የከፈትከውን የማጥላላት ዘመቻ መቀጠል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ መልኩ በደንብ አድርገህ እንድትቀጠቅጠው ያስፈልጋል፡፡
ለጀመርከው ፕሮፓጋንዳ እቅድ ዲዛይኑን በማውጣት እንዲተባበርህና ውጤታማ እንድትሆን አጋርህን ፋሲል የኔዓለምን ልታማክረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፋሲልን ሳታማክር በራስህ የምትሰራቸው ሥራዎች እንዳሉ ተረድተናል፡፡ ይሄ መልካምና የሚደገፍ ሆኖ አላገኘነውም፡፡
       ከአክብሮት ጋር
ተወልደ ኃብቴ ነጋሽ (ኮሎኔል)››
** ** **
አዲስ አድማስ በፊት ገጽ ዜናው ‹‹አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሕንፃ አፈሰሰ›› የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ ‹‹… የአፍሪካንና የቻይናን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ እንዳሸጋገረ የተነገረለለትና በቻይናውያን ተገንብቶ ለአፍሪካ ሕብረት በስጦታ የተበረከተው 200ሚ. ዶላር የወጣበት አዲስ ሕንፃ ሰሞኑን በጣለው ዝናብ ጣርያው ማፍሰስ ጀመረ፡፡…››
** ** **
ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ‹‹በአወሊያ የእስልምና ዕምነት ተከታዮችና ፖሊስ ተጋጩ›› የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ ‹‹… ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ፌዴራል ፖሊስ ተመልሶ በመምጣት፣ የግቢውን መብራት በማጥፋትና ወደ ግቢው ዘልቆ በመግባት አስለቃሽ ጭስ በመርጨት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውል፣ ጥቂቶች ማምለጣቸውን ተናግረዋል፡፡…››

ሌላም ሌላም
 • በኢሕአዴግ ውስጥ የጎላ ልዩነት እየተፈጠረ ነው – ፍኖተ ነፃነት
  ‹‹…በሙስሊሞች የወቅቱ ጉዳይ ላይ ጥያቄ እና በዋልድባ ገዳም መደፈር ጉዳይ ላይ መንግስት እየተከለ ያለውን አቋም አምርረው የሚተቹ አባላት መበራከታቸውን በፓርቲው የጎላ ልዩነት በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አመልክተዋል፡፡…››
 • ከ200 በላይ የታክሲ ባለንብረቶች የታክሲን ሥራ ለማቆም ጥያቄ አቀረቡ – የኛ ፕሬስ
 • በዓለም ላይ 100 ሚሊዮን ጫት ቃሚዎች አሉ፤ 30 ሚሊዮን የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው – የኛ ፕሬስ
 • በኢትዮጵያ በፎቅ ርዝመቱ ቀዳሚ ሆቴል ተገነባ – መሰናዘሪያ
  ‹‹… በባሕር ዳር ጣና ሀይቅ ዳርቻ የተገነባውና ግማሽ ግንባታው በሀይቁ ላይ ያረፈው ይህ [ባለ19 ፎቅ] ሆቴል ባለ 150 መኝታ ቤቶችና ሳሎኖች፣ እያንዳንዳቸው 1299 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሦስት የመሰብሰቢያ አዳራሾ፣ የሥራ አስፈፃሚ ልዩ አዳራሾች፣ አምስት ሬስቶራንቶች፣ የመዋኛ ገንዳና ሌሎች የሆቴል አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች ያሉት ነው፡፡….››
 • በአዳማ ከተማ የተከሰተው ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰበአዳማ ከተማ የተከሰተው ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ይፋ ሆነሪፖርተር (ረቡዕ)
 • በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተቃውሞ የተሰነዘረበት የቴሌኮም አዋጅ ፀደቀ – ፍትህ
 • Ethiopia stands 100th [out of 105] in Global Food Index Report [of the Economist Intelligent Unit] – Capital
 • ከውጭ ለሠርጉ የመጣው የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር [ደረጄ ደበበ ተሰማ] ታሠረ፤ በከፍተኛ ጥበቃና ክትትል ሠርግና መልሱን አጠናቆ ወደ እስርቤት ገብቷል፡፡ – ኢትዮቻናል
መለስ የት ናቸው?
 • ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተያያዘ ለፈጠራ ባለሙያዎች ሊሰጥ የታሰበው ሽልማት ለሁለተኛ ጊዜ ተራዘመ – ሰንደቅ
 • የመለስ ህመም፣ ታክቲክ እና መፃኢ እጣ ፈንታ – ፍትህ
 • የዘንድሮው የፓርላማ አሰራር [ሰኔ 30 አለመዘጋቱን ጨምሮ] ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ አስነስቷል፤ የ2005ቱ በጀት እስካሁን አለመፅደቁም እያነጋገረ ነው፡፡ – ሰንደቅ፣ አዲስ አድማስ
 • Meles misses NEPAD meeting due to health reasonTHE Reporter
 • In the Chief’s ABSENCE – Fortune
  የፎርቹን ጋዜጠኛ ‹‹…የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝን አግኝቶ ስለመለስ ቢጠይቃቸው ‹‹አንተ ንገረኝ እንጂ!›› እንዳሉት ጠቅሶ፣ አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳሊ ግን ቅዳሜ ዕለት መለስ ሊመሩት ይገባ የነበረውን የNePAD ስብሰባ ሲመሩ መለስ የቀሩት በጤና ችግር ምክንያት እንደሆነ ገልፀው ‹‹መልካም ጤና›› ተመኝተውላቸዋል…›› የሚል ሐተታ አስነብቧል፡፡
በ‹‹አሸባሪነት›› የተከሰሱት ሰዎች ፍርድ
የኮብል ስቶን ነገር
 • ኮብል ስቶን የምህንድስና ዕውቀት ይጠይቃል ተባለ – አዲስ አድማስ
  ‹‹ማስተርስና ፒኤችዲ የያዙ ዜጎቻችን በውጭ አገር፣ በዘበኝነት ሲሰሩ፣ ጉዳዩ አጀንዳ ሆኖ አልተነሳም›› – የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
 • ‹‹…ሌሎች ባይቀጥሯችሁም ምንም አይደለም፤ ራሳችሁን መቅጠር ትችላላችሁ፡፡›› አ.አ.ዩ. በልደት አዳራሽ ለተመራቂ ተማሪዎች የተበተነ በራሪ ወረቀት ላይ በጉልህ የተጻፈ – አዲስጉዳይ
 • መድረክ ምሩቃን በኮብልስቶን ሥራ መሰማራታቸው የፖሊሲ ውድቀትን ያሳያል አለሪፖርተር (እሁድ)
ርዕሰ አንቀፅ

ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – አምስት

(ከሰኔ 25፣ 2004 እስከ ሐምሌ 1፣ 2004)

‹‹በኢትዮጵያ ሊትሩ 135ሺህ ብር የሚሸጥ ዘይት ሊመረት ነው›› የሚል ዜና ይዞ የወጣው መሰናዘሪያ ጋዜጣ ነው፡፡ ‹‹…ቴራ የተባለ የጀርመን ካምፓኒ [ባሕርዳር] ከነሐሴ ወር ጀምሮ ሊትሩ 7,500 ዶላር የሚሸጥ ዘይት እያመረተ ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡….››

** ** **
‹‹ዲግሪ ያላቸው ዜጎች የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል››  የሚል አስደንጋጭ መርዶ ያስነበበው ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ እትሙ ነው፡፡ ‹‹ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የማስተርስና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ዜጎች አዲስ አበባ ውስጥ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ሆነው መገኘታቸው ተጠቆመ፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ… የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ወደ መልካም ሕይወት ለመመለስ፣ … በማድረግ ላይ ባለው እንቅስቃሴ መምህር፣ ነርሶችና በተለያዩ ሙያዎች የተመረቁ ዜጎች የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ሆው መገኘታቸውን አረጋግጧል….››

** ** **

‹‹ይቅርታ›› የኢሕአዴግ ቃጭል? ወይስ… ያለው ተመስገን ደሳለኝ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ነው፡፡ ‹‹…እነሆም ማሰር፣ ከአሰሩ በኋላ በይቅርታ መልቀቅ፣ ከለቀቁ በኋላ ደግሞ ይቅርታን አንስቶ መልሶ ማሰር…‹በይቅርታ ተቀባዩ አንገት ላይ ተንጠልጥሎ ቀሪ ዘመንን በሞላ ‹ኪሊ፣ ኪል…› የሚል ‹ቃጭል› ነው›…››


** ** **

አዲስጉዳይ መጽሔት ‹‹ኮንደሚኒም የማን ነው?›› በሚል ርዕስ፣ ነጋድራስ ጋዜጣም በበኩሉ ‹‹ኮንዶሚኒየሙ የማን ነው? የሚል ተመሳሳይ ርዕስ ያለው ሐተታ ይዘው ቀርበዋል፡፡ ነጋድራስ ኮንዶሚኒየም ዝቅተኛና መካለኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ዕጣው ቢወጣላቸውም እንኳን የመጀመሪያውን ክፍያ ለመሸፈን ስለሚያከራዩት አይኖሩበትም ብሏል፤ አዲስጉዳይም ይህንኑ ሲያጠናክር ‹‹ቤቶቹን ባለቤቶቻቸው አያውቋቸውም›› ብሏል፡፡ አዲስጉዳይ ሐተታውን ሲደመድም ‹‹…ለመሆኑ ኮንደሚኒየም ቤቶች የተገነቡት ለማነው? ለነጋዴው? አነስተኛ ገቢ ላለው ህብረተሰብ? ለመንግስት ባለስልጣናት ወይስ ለሕዝብ?›› የሚሉ ጥያቄዎችን አንስቷል፡፡

** ** **

ከእሁዱ የሪፖርተር ትኩረት የሚስቡ ዜናዎች መካከል፣ ‹‹የንግድ ባንክ ጐተራ ቅርንጫፍ የዘረፋ ሙከራ ተደረገበት››‹‹የገቢዎችና ጉምሩክ ኦዲተሮች 100 ሺሕ ብር ጉቦ ሲቀበሉ ተያዙ›› እና ‹‹የመጀመሪያው የአየር ትራንስፖርት ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጀ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ዝርዝሩን የተሰመረበትን የድረ ገጹን ትይይዝ ጠቅ በማድረግ/በመከተል ማግኘት ይቻላል፡፡

ሌላም፣ ሌላም

 • አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማ ራይትስ ዎችና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አነዱዓለም አራጌ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ – የኛ ፕሬስ
 • ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤና አስተማማኝ ባለመሆኑ የፓርላማው መርሃ ግብር ተራዘመ››
  ‹‹ይሄ የኢሳትና የእሳት ወሬ ነው›› – አቶ ሽመልስ ከማል (ፍኖተ ነፃነት)
 • መድረክን ወደ ግንባር ከፍ ለማድረግ ሥራ አስፈፃሚው እየመከረ ነው፤ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ ገና አልተወሰነም – ሰንደቅ
 • ሐዋሳ ከተማ ወደ ፌዴራል አስተዳደር አትገባም፤ በከተማዋ ግጭት ለማቀጣጠል ሕገ-ወጥ ወረቀት ተበትኗ – ሰንደቅ
 • ከፖለቲካ ወገንተኝነት ያልፀዳው የስፖርት ውድድርሪፖርተር (ረቡዕ)
  ‹‹…ጉዳዩን ጠለቅ ብለው የሚያውቁ ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የስፖርት ማኅበር አመራሮች መካከል የለው ልዩነት ጎልቶ የወጣው በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ምክንያት ቢሆንም፣ ከዚያ በፊት ሥልጣን በሌላቸው መሥራቾችና በአመራሮች መካከል ከባድ የሆነ የውስጥ ትግል ነበር፡፡ ዋናው ችግራቸውም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነበር፡፡…››
 • ተስፋዬ ገብረአብ ከሚበጀው የሚፈጀው – አለማየሁ ገላጋይ (ፍትህ)
  ‹‹… ተስፋዬ ጅል አይደለም፡፡ ውጤቱን እየገመተ ብቻ ሳይሆን እያወቀ የሚያደርግ ለመሰሪነት የቀረበ ሰው ነው፡፡ …››
 • በእነአንዱዓለም አራጌ መዝገብ ነፃ የተባሉ በይግባኝ ተፈረደባቸው፤ ከ10 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ተበይኖባቸዋል – አዲስ አድማስ
 • አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ የኢትዮጵያ ሴት የምግብ ዋስትና ጀግኖች አምባሳደር ሆና ተመረጠች – ኢትዮቻናል
 • ‹‹…ፀጥ በማለትና በደህንነት መካከል ያለውን ቅራኔ ለማስታረቅና ለማመቻመች የሚደረገው ጥረት አዲስ ዓይነት የስነግጥም ዘይቤ ፈጥሯል፤ ይህ ስመ ጥሩውና ‹ሰምና ወርቅ› የሚባለው ዘይቤ ነው…›› ለፖኦትሪ ፐርነሰስ (በዕውቀቱ ስዩም) – ኢትዮቻናል
 • በጫት ላይ ኤክሳይዝ ታክስ የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ወጣ፤ ለአገር ውስጥ ገበያ በሚቀርበው ጫት ላይ በኪ.ግ 5 ብር ቀረጥ ያስከፍላል – አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር (እሁድ) ኮሎምቢያ ጫት ገበያውን እያነቃቃ ነው – Fortune

ርዕሰ አንቀጽ