ጋዜጣና መጽሔቶቻችን ከሰኞ እስከ ሰኞ – ስድስት

(ከሐምሌ 2 እሰከ ሐምሌ 8፣ 2004 – Find the original at http://zone9ethio.blogspot.ca/)
ሰለሞን ስዩም ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ላይ ‹‹የኢሕአዴግ ጥንካሬ ምን ያክል ነው?›› የሚል ርዕስ በሰጠው ሐተታው፣ ‹‹…እንቁላል በሁለቱ ጫፍና ጫፍ (በዋልታዎቹ) በመዳፍህ መካከል አይሰበርም፤ በወገቡ በኩል በመዳፎችህ መካከል ከተጫንከው ግን ፍርክሽ ይላል፡፡…›› የሚል ቀላል መልስ ሰጥቷል፡፡
** ** **
ሪፖርተር ጋዜጣ በረቡዕ እትሙ ‹‹አቶ ጁነዲን ሳዶ ስለ ኮብል ስቶን ያደረጉት ንግግር ተቃውሞ ገጠመው ›› በሚል ርዕስ ባሰፈረው ዜና ላይ የሚከተለውን አካትቷል ‹‹የቀድሞው ድምቀቱና ውበቱ በተለየው የዘንድሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ሥነ ሥርዓት ላይ፣ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ በንግግራቸው ስለ ኮብል ስቶን በማንሳታቸው ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት ገጠማቸው፡፡ አቶ ጁነዲን ባለፈው ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ንግግራቸውን ሲጀምሩ በአድናቆት ጭብጨባና በፉጨት ቢታጀቡም፣ ድንገት የንግግራቸውን አቅጣጫ ወደ ኮብል ስቶን በማዞራቸው ነበር ሳይታሰብ ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት፣ ጉርምርምታና ፉጨት ከተመራቂዎቹ የተሰማው፡፡…››
** ** **
ፍትህ ጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ የፕሮፓጋንዳ ስምምነት አለን በሚል የአልሻባብ ሰው ነኝ ከሚል የተጻፈለት ኢሜይል ተከታይ አሁንም በሌላ ሰው ተላከለት፡፡

‹‹ሰላም ተመስገን፣
ከአልሻባብ ልዑክ ጋር ችግር ውስጥ ባትገባ የተሻለ ነው፡፡ ምናልባት ያልተፈታ ችግር ካለ ለሚመለከተው ክፍል ብትተወው ይሻላል፡፡ ካንተ የሚጠበቀው በኢትዮጵያ መንግሥት እና ኢኮኖሚው ላይ የከፈትከውን የማጥላላት ዘመቻ መቀጠል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ መልኩ በደንብ አድርገህ እንድትቀጠቅጠው ያስፈልጋል፡፡
ለጀመርከው ፕሮፓጋንዳ እቅድ ዲዛይኑን በማውጣት እንዲተባበርህና ውጤታማ እንድትሆን አጋርህን ፋሲል የኔዓለምን ልታማክረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፋሲልን ሳታማክር በራስህ የምትሰራቸው ሥራዎች እንዳሉ ተረድተናል፡፡ ይሄ መልካምና የሚደገፍ ሆኖ አላገኘነውም፡፡
       ከአክብሮት ጋር
ተወልደ ኃብቴ ነጋሽ (ኮሎኔል)››
** ** **
አዲስ አድማስ በፊት ገጽ ዜናው ‹‹አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሕንፃ አፈሰሰ›› የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ ‹‹… የአፍሪካንና የቻይናን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ እንዳሸጋገረ የተነገረለለትና በቻይናውያን ተገንብቶ ለአፍሪካ ሕብረት በስጦታ የተበረከተው 200ሚ. ዶላር የወጣበት አዲስ ሕንፃ ሰሞኑን በጣለው ዝናብ ጣርያው ማፍሰስ ጀመረ፡፡…››
** ** **
ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ‹‹በአወሊያ የእስልምና ዕምነት ተከታዮችና ፖሊስ ተጋጩ›› የሚል ዜና አስነብቧል፡፡ ‹‹… ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ፌዴራል ፖሊስ ተመልሶ በመምጣት፣ የግቢውን መብራት በማጥፋትና ወደ ግቢው ዘልቆ በመግባት አስለቃሽ ጭስ በመርጨት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውል፣ ጥቂቶች ማምለጣቸውን ተናግረዋል፡፡…››

ሌላም ሌላም
 • በኢሕአዴግ ውስጥ የጎላ ልዩነት እየተፈጠረ ነው – ፍኖተ ነፃነት
  ‹‹…በሙስሊሞች የወቅቱ ጉዳይ ላይ ጥያቄ እና በዋልድባ ገዳም መደፈር ጉዳይ ላይ መንግስት እየተከለ ያለውን አቋም አምርረው የሚተቹ አባላት መበራከታቸውን በፓርቲው የጎላ ልዩነት በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አመልክተዋል፡፡…››
 • ከ200 በላይ የታክሲ ባለንብረቶች የታክሲን ሥራ ለማቆም ጥያቄ አቀረቡ – የኛ ፕሬስ
 • በዓለም ላይ 100 ሚሊዮን ጫት ቃሚዎች አሉ፤ 30 ሚሊዮን የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው – የኛ ፕሬስ
 • በኢትዮጵያ በፎቅ ርዝመቱ ቀዳሚ ሆቴል ተገነባ – መሰናዘሪያ
  ‹‹… በባሕር ዳር ጣና ሀይቅ ዳርቻ የተገነባውና ግማሽ ግንባታው በሀይቁ ላይ ያረፈው ይህ [ባለ19 ፎቅ] ሆቴል ባለ 150 መኝታ ቤቶችና ሳሎኖች፣ እያንዳንዳቸው 1299 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሦስት የመሰብሰቢያ አዳራሾ፣ የሥራ አስፈፃሚ ልዩ አዳራሾች፣ አምስት ሬስቶራንቶች፣ የመዋኛ ገንዳና ሌሎች የሆቴል አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች ያሉት ነው፡፡….››
 • በአዳማ ከተማ የተከሰተው ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰበአዳማ ከተማ የተከሰተው ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ይፋ ሆነሪፖርተር (ረቡዕ)
 • በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተቃውሞ የተሰነዘረበት የቴሌኮም አዋጅ ፀደቀ – ፍትህ
 • Ethiopia stands 100th [out of 105] in Global Food Index Report [of the Economist Intelligent Unit] – Capital
 • ከውጭ ለሠርጉ የመጣው የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር [ደረጄ ደበበ ተሰማ] ታሠረ፤ በከፍተኛ ጥበቃና ክትትል ሠርግና መልሱን አጠናቆ ወደ እስርቤት ገብቷል፡፡ – ኢትዮቻናል
መለስ የት ናቸው?
 • ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተያያዘ ለፈጠራ ባለሙያዎች ሊሰጥ የታሰበው ሽልማት ለሁለተኛ ጊዜ ተራዘመ – ሰንደቅ
 • የመለስ ህመም፣ ታክቲክ እና መፃኢ እጣ ፈንታ – ፍትህ
 • የዘንድሮው የፓርላማ አሰራር [ሰኔ 30 አለመዘጋቱን ጨምሮ] ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ አስነስቷል፤ የ2005ቱ በጀት እስካሁን አለመፅደቁም እያነጋገረ ነው፡፡ – ሰንደቅ፣ አዲስ አድማስ
 • Meles misses NEPAD meeting due to health reasonTHE Reporter
 • In the Chief’s ABSENCE – Fortune
  የፎርቹን ጋዜጠኛ ‹‹…የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝን አግኝቶ ስለመለስ ቢጠይቃቸው ‹‹አንተ ንገረኝ እንጂ!›› እንዳሉት ጠቅሶ፣ አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳሊ ግን ቅዳሜ ዕለት መለስ ሊመሩት ይገባ የነበረውን የNePAD ስብሰባ ሲመሩ መለስ የቀሩት በጤና ችግር ምክንያት እንደሆነ ገልፀው ‹‹መልካም ጤና›› ተመኝተውላቸዋል…›› የሚል ሐተታ አስነብቧል፡፡
በ‹‹አሸባሪነት›› የተከሰሱት ሰዎች ፍርድ
የኮብል ስቶን ነገር
 • ኮብል ስቶን የምህንድስና ዕውቀት ይጠይቃል ተባለ – አዲስ አድማስ
  ‹‹ማስተርስና ፒኤችዲ የያዙ ዜጎቻችን በውጭ አገር፣ በዘበኝነት ሲሰሩ፣ ጉዳዩ አጀንዳ ሆኖ አልተነሳም›› – የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
 • ‹‹…ሌሎች ባይቀጥሯችሁም ምንም አይደለም፤ ራሳችሁን መቅጠር ትችላላችሁ፡፡›› አ.አ.ዩ. በልደት አዳራሽ ለተመራቂ ተማሪዎች የተበተነ በራሪ ወረቀት ላይ በጉልህ የተጻፈ – አዲስጉዳይ
 • መድረክ ምሩቃን በኮብልስቶን ሥራ መሰማራታቸው የፖሊሲ ውድቀትን ያሳያል አለሪፖርተር (እሁድ)
ርዕሰ አንቀፅ

About Zone Nine

Zone Nine is a team of writers on Ethiopian social, economical and political situations.

Posted on July 15, 2012, in ሳምንቱን በሕትመት ውጤቶች. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: